04/06/2025
ጤነኛ እና በእድሜ ሽማግሌ ያልሆነ/ያልሆነች ወይም ከባድ የማይድን በሽታ የሌለው/የሌላት አቅሙ/አቅማ ላይ ተመርኩዞ/ዛ የማንም ሰው ሸክም ሳይሆን/ሳትሆን መኖር ይችላል/ትችላለች::
የማንም ሸክም መሆን የለብንም::
ልመና መልኩን ቀይሮ ሲመጣ ማበረታታት የለብንም። ዋና ስራ ካለን እና ገቢው በቂ ካልሆነ እጃችን ላይ ምን ልንሸጠው የምንለው ክህሎት አለን? ሁሉም ዩንቨርስቲ ገብቶ መማር የለበትም ጥሩ ኑሮ ለመኖር
Based on my observation wanted to share my lived experience! I hope you will get something out of this post!
እኔ ስራ የጀመርኩት ልጅ እያለሁ ማትሪክን ስወድቅ ቁጭ ከምል ገጠርም ቢሆን እሄዳለሁ ብዬ የመጀመርያ ትምህርት ቤት አስተማሪ በመህን ነው። በዛን ወቅት የነበረኝ የትምህርት ውጤት ዩንቨርስቲ ስላላስገባኝ
እናም ከማገኘው ይ305 ብር ደሞዝ እቆጥብ ነበር።
እናም መፅሃፍቶችን ገዝቼ ስራ ከጀመርኩበት ወር አንስቶ በትርፍ ሰዓቴ ማትሪክን በፕራይቬት ለመፈተን አጠና ነበር። በዚያንወቅት አብረውኝ አስተማሪ የነበሩት ብዙዎቹ ይስቁብኝ ነበር።
እግዚአብሄርም ረድቶኝ ዩኒቨርስቲ ገባሁ። እየሰራሁ ስማር ስለነበር የማንም ሸክም አልነበርኩም። ሁለተኛ ድግሪዬን ልማር ስራ ሳቋርጥ ሶስት አመት በገጠር ልማት እና የሰባት አመታት የከተማ ልማት ላይ የስራ ልምድ ነበረኝ።
ሶስተኛ ድግሪዬን ተምሬ ስመለስ በልምድ በስራ ቦታ ያወቅሁትን ሳይንሳዊ ለማድረግ አልከበደኝም። ምርምርም መፃፍ እና በተለየ መልክ ፖሊሲ መተንተን ጥሩ ሆነልኝ።
ከ 19 አመቴ ጀምሮ እስከ 38 አመቴ ስማር (TTI, BA,MA, PhD) እናም ስሰራ ቆየሁ። አሁንም እየሰራሁ ነው። በአቅሜ እኖርም ነበር። ሰርግ መደገሻ ብዙ ብር ስላልነበረን ድግስ አልደገስንም። ሰርጋችን ፐብሊክ ቦታ ነበር እናም there were only snacks and drinks😀😀
ለምንድን ነው ይህን መፃፍ ያስገደደኝ??
አሁን አሁን መለመን ሌላ መልክ ይዞ መታል። ሰዎች ከገቢያቸው በላይ ስለሚያወጡ ብክነት እና እዳ ላይ የተመሰረተ ኑሮ ተለምዳል። አንዳንዱ ከሰው ለምኖ እና ተበድሮ ሊዝናና ሌላ ሃገር ይሄዳል። ይህ በእውነት ሁሌ ይገርመኛል።
ልጄን ልድር ነውና ገንዘብ ስለማይበቃኝ እርዱኝ የሚል አባት የባንክ ቁጥሩን ፅፎ በምንሰራበት ብታ ሲጠይቅ አይቻለሁ።
ኑሮ ከባድ ነውና ደምዜ አልበቃኝም እና ....የመሳሰሉ ጥያቄዎች አያለሁ ይደርሱኛልም። እናም ልምድ ለማካፈል ነው የወደድኩት ሰዉ እንዲጠቀምበት።
ያኔ የእኔ ደሞዝ በቂ አልነበረም ስለዚህ ወጭዎቼን ከገንዘቤ ጋር አመዛዝኜ የምፈልገውን ሳይሆን የሚያስፈልገኝን ብቻ ነበር የምገዛው።
ጤነኛ የአበላል ስርዓት ዘርግቼ ነበር። እንደውም ከዛችው ደሞዝ ቤተሰብ እረዳ ነበር።
ውጭ ለትምህርት በነበርኩበት ግዜ ገቢዬ ስለማይበቃኝ ለብቻዬ ቤት አልንተከራየሁም። ቤት ተከራይተው ክፍላቸውን ከሚያከራዩ ጋር የክፍሉን ከፍዬ ነበር የምማረው። ምክንያቱም ኪችን የጋራ ስለሆነ ለጥናት ባይመችም ላይብረሪም ነበር የማጠናው።
እና ታድያ የእኛ አገር ከተማዎች ባለ ሁለት ሶስት ክፍል አፓርታማ ስላላቸው ደሞዛቸው የማይበቃቸው በጋራ ተከራይተው ኪችን እና ሳሎን በጋራ እየተጠቀሙ የኪራይ ወጭያቸውን ለምን እንደማይቀንሱ አይገባኝም
ብዙ ሰው ውጭ ይመገባል ገቢው ትንሽ ከሆነ ቤት መስራት ብዙ ስለሚያተርፍ ለዚያውም ጤነኛ ስለሆነ ውጭ መብላትን ለምን አየተውም?? በትንሹ 600 መቶ ብር የሚያስከፍል ጥብስ ውጭ ከመብላት በ500 ብር ግማሽ ኪሎ ስጋ በመግዛት ከአትክልት እና ሽሮ ጋር ለ 4 ግዜ የሚሆን ምግብ መስራት ይቻላል።
ደሞ ወንዶች ማብሰል ስለማንችል ነው እንዳትሉኝ😂😂 በአለም ላይ የታወቁ ሼፎች (ምግብ አብሳዮች ) ወንድች ናቸው። እኛም ሃገር በጣም ውዱ ሬስቶራንት ባለቤት ወንድ ነው።
ከዩቱይብ ላይ እያያችሁ ራሳችሁን ምግብ ማብሰል አስተምሩ! ራሳችሁን ቻሉ😀😀 ገንዘባችሁን ቆጥቡ
ነውራችን የህይወት ክህሎት ስልጠና በመውሰድ እናም የMindSet-ማይንድሴት ለውጥ በማምጣት ሃላፊነትን በመውሰድ መቀየር እንችላለን።
ልመና ሰርቶ መኖር ለሚችል ሰው ነውር ነው። ሰጭዎችም ችግሩን እንዲባባስ አትተባበሩ!!
ተጻፈ
በዶ/ር መሰረት ካሳሁን