
17/06/2025
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ያዘጋጀው የ2017 ዓ/ም የፓለቲካና የንቅናቄ ስራዎች ዓመታዊ ማጠቃለያ ኮንፈረንስና የ2018 ዕቅድ ኦረንቴሽን ዞናል መድረክ ተካሂዷል።
ሰኔ 10/2017 ዓ/ም
በመድረኩ የዞኑ ጠቅላላ አመራሮችና በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የሰባቱም መዋቅሮች የፓርቲ አመራሮች በተገኙበት የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የ2017 ዓ/ም የፓለቲካና የንቅናቄ ስራዎች ዓመታዊ አፈፃፀም ሪፓርት እና የ2018 ዕቅድ፤ እንዲሁም የዞኑ የብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን የ2017 ዓ/ም ሪፓርት በፅ/ቤቱ ኃላፊ በወ/ሮ ጀሚላ ጎሳ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪና የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ጫካ እንዳሉት በዓመቱ ውጤታማ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን በመፈፀም ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ የቻልንበት ዓመት ነውና ለዚህ ውጤት የሀሉም መዋቅር አስተዋጽኦ ከፍተኛ የነበረ በመሆኑ ሁሉም መዋቅራችን ከፍተኛ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።
ኃላፊው አቶ መሰለ አክለውም እንዳሉት የአመራራችን የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ይበልጥ የማጠናከር፣ ብልሹ አሰራሮችን ፈጥኖ የማረም፣ ተቋማዊ አሰራርን ተክሎ ተግባር መፈፀም፣ የብልፅግና ቤተሰብ እና ህብረቶችን ማጠናከርና አባልን የመገንባት፣ አባል የማፍራት፣ የፀጥታ ስራን በትኩረት መምራት፣ ሚዲያ ላይ ንቁ በጎ ተሳትፎ ማድረግ እንዲሁም በትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች ያሉን የተሻሉ አፈፃፀሞችን በቀጣይም በዘጠና ቀን ዕቅዳችን ብሎም በ2018 ዓመታዊ ዕቅድ ላይ አካተን በላቀ ደረጃ በመፈፀም የህዝባችንን ተጠቃሚነት ማሳደግ ብሎም ሀገራዊ ሁለንተናዊ ብልፅግናችን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊኖረው በሚችል መልኩ በርትተን መስራት ይገባናል በማለት ካስገነዘቡ በኋላ በሌሎችም ተያያዥ ተግባራት ላይ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ረዳት የመንግስት ተጠሪና የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሰረት ሽፋ በበኩላቸው እንዳሉት በዓመቱ በርካታ ውጤታማ ተግባር መከናወኑን ገልፀው በቀጣይም ተግባራትን በአደረጃጀት መምራት፣ ፓለቲካሊ የተተነተነ መረጃ መስጠት፣ አደረጃጀቶችን ማጠናከርና የአባላት ጥራት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ካሉ በኋላ በንቅናቄ የሚመሩ ተግባራት ላይ የተሰራው ውጤታማ ስራ በቀጣይ ዘጠና ቀናትም አጠናክሮ ማስቀጠል እና ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ጉዳይ ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል በማለት አስገንዝበዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ረዳት የመንግስት ተጠሪና የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አህመድ ኑሪ በሰጡት አስተያየት እንዳሉት አደረጃጀቶችን ከማጠናከር አኳያ በትኩረት መስራት፣ ብልፅግና ፓርቲያችን የህዝባችንን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ያለበትን ሁኔታ በተገቢው የፓለቲካ ስራ በመስራት ፓርቲያችን በህዝቡ ዘንድ ያለውን ቅቡልነት ለማሳደግ መስራት ይገባናል ብለዋል።
በውይይቱ በተለይም የ2017 በጀት ዓመት በቀረበው ሪፓርት ላይ የውይይቱ ተሳታፊ አመራሮች በሰጡት አስተያየት እንዳሉት የተገባደደው የ2017 የስራ ዘመን በፓርቲ መደበኛ ተግባራትም እንዲሁም በፓርቲ መሪነት በተከናወኑ የንቅናቄ ተግባራት ላይ ምንም እንኳ በቅርቡ የተደራጀ ዞን ቢሆንም ዋና ዋና የህዝብን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት የስራ ዓመት እንደነበር ከእያንዳንዱ አጀንዳ አኳያ በዝርዝር አስተያየት የተሰጠ ሲሆን፤ ከብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን አኳያም አደረጃጀቱን ከማጠናከር ባለፈ በፓርቲ ዲሲፕሊን የፓርቲ ተግባር እንዲፈፀምና ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የተሰሩ ተግባራት ውጤታማ እንደነበሩ አስተያየት ተሰጥቷል።
ከዚህ ባሻገርም በውስን ጉዳዮች በሚፈለገው ልክ ውጤት ያልመጣባቸው ተግባራት ላይ በቀጣዩ የስራ ዓመት የሚክስ ተግባር ለመፈፀም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ከ2017 የስራ ዓመት አፈፃፀም አኳያ ለነበሩ የተሻሉ አፈፃፀሞች ለወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የዕውቅናና የምስክር ወረቀት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባው የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ነው።