14/11/2025
የአማራ ክልሉ ጦርነት ብዙ ሀገር ተረካቢዎችን እየበላ ነው። በዚህም በዛም እየተሰዋ ያለው የክልሉ አምራች ኃይል ነው። እንደ ዋዛ ሁለት አመት ያለፈው ጦርነት ብዙ መቶ ሺዎችን አሳጥቶናል። በሁለት ጎራ ተካፍሎ ሰው የድል ዜና እያለ ያቀርባል። ለኔ ግን ድል አይደለም። ክስረት ነው። ቆም ብሎ ማሰብ ቢቻል መልካም ነው።
የመጀመሪያ ኃላፊነቱ የመንግስት ነው። ቀስ ሽማግሌ ከሚልክ ፎርማል ድርድር ጥያቄ ማቅረብ ያለበት መንግስት ነው። አጉል ጀብደኝነት ከመንግሥት አይጠበቅም። የሀገር ዜጋን ደምስሰው የሚያገኙት ስኬት ፈፅሞ አይኖርም። ይልቅ ዝቅ ብሎ መደራደር አለበት። በጉልበት ብቻ ሁሉም ነገር አይፈታም።
ሁለተኛው የፋኖ ኃይሎች ናቸው። ግትር ከማለት የመደራደሪያ ነጥቦችን አስይዘው መደራደር አለባቸው። ለድርድር ዝግጁ መሆን አለባቸው።