Niguss Teklehaymanot Sub City Addministration Communication

Niguss Teklehaymanot Sub City Addministration Communication ይህ ፔጅ የንጉስ ተክለሃይማኖት ክፍለ ከተማ ማህበራዊ ድህረ ገፅ ነው ላይክ ሼር ኮሜንት በማድረግ የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ !!!

06/07/2025
06/01/2025
"ሰላም ለሁሉም፤ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ቃል በንጉስ ተክለ ሃይማኖት ክ/ከተማ ከቀበሌ 16 (ወንቃ) የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተካሄደ። በደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳድር በንጉስ ተክለ ...
18/11/2024

"ሰላም ለሁሉም፤ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ቃል በንጉስ ተክለ ሃይማኖት ክ/ከተማ ከቀበሌ 16 (ወንቃ) የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተካሄደ።

በደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳድር በንጉስ ተክለ ሃይማኖት ክፍለ ከተማ ቀበሌ 16 (ወንቃ) ቀበሌ ከሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

የውይይት መድረኩን የክፍለ ከተማው የፖለቲካ እና የፀጥታ አመራሮች ሲሆኑ ውይይቱ አሁን ያለውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግና ህዝቡን ባለቤት ለማድረግ፣የትምህርት ስራዎችን ለማስጀመር እና መንግስታዊ አገልግሎቶችን ለማስቀጠል ያለመ ነው።

የቀበሌው አርሶአደሮች በበኩላቸው በነበረው ግጭት ተጎጂ መሆናቸውን ጠቅሰው መንግስት በዘላቂነት ሰላምን እንዲያረጋግጥና በቀበሌያቸው መማር ማስተማር እንዲጀመር ለዚህም ከመንግስት ጎን በመሆን እንደሚሰሩ ጠይቀዋል።

•~••~•~•
🕊ሠላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

"የጣና ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•

•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።

ፌስቡክ፦👇
https://www.facebook.com/dmprosperity

ዩቲዩብ :-👇 https://www.youtube.com/channel/UCUxX68uNGl-c8Z5hGOOLjsA

ትዊተር :- 👇 https://twitter.com/PpPartyDM?t=3tp3l-iT-HNar9UdeQKOVw&s=35

ቴሌግራም:-👇
https://t.me/+URqQUcKoEIw3ODhk

ቲክቶክ፦ 👇
tiktok.com/

18/11/2024
13/10/2024
ወጣቶች ለሰላም መረጋገጥና ለአገር ግንባታ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡***********************ጥቅምት 3/2017ዓ.ም(ደብረ ማረቆስ ኮሚኒኬሽን)፡ በደብረ...
13/10/2024

ወጣቶች ለሰላም መረጋገጥና ለአገር ግንባታ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
***********************
ጥቅምት 3/2017ዓ.ም(ደብረ ማረቆስ ኮሚኒኬሽን)፡ በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ንጉስ ተክለ ሃይማኖት ክፍለ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ከአስተዳደሩ ጋር የምክክር መድረክ አካሂደዋል፡፡

ከክፍለ ከተማው የተውጣጡ ወጣቶች በተሳተፉበት በዚህ የውይይት መድረክ በሰላም፣ በልማት እና በአገራዊ መግባባት ዙሪያ ስላላቸው ሚና ምክክር ስለመደረጉ የገለፁት የክፍለ ከተማው ወጣቶች ሊግ ኃላፊ አቶ ንብረት መላክ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ እንዲሳተፉና በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይሰራል ብለዋል፡፡

የወጣቶች አቅም ለሁለንተናዊ ልማትና ብልጽግና ምንጭ ስለመሆኑ የገለፁት የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ የስነመግርና ኢንስፔክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ያየህይራድ ይህንን አቅም በማጠናከር ወጣቶች በሰላምና በአገር ልማት ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የፀጥታው ሁኔታ በስራ እድል ፈጠራ ስራው ላይ ተፅኖ በመፍጠሩ ግንባር ቀደም ተጎጅዎች እኛ ወጣቶች መሆናችንን አይተናል ያሉት የምክክር መድረኩ ተሳታፊ ወጣቶች ሰላም እንዲመጣ የስራ ግንኙነታችንን በማጠናከር የሚጠበቅብንን ለመወጣት እንሰራለን፤እንዲህ አይነት ውይይቶች ቀጣይነት ሊኖርቸው ይገባል ብለዋል፡፡

የንጉስ ተክለ ሃማት ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አደራየ አሳየ ወጣቶች ለሰላም መረጋገጥ ወሳኝ ኃይል መሆናቸውን ገልጸው፣ ከአፍራሽ ተልኮዎች ራሳቸውን በማራቅ ለከተማዋ ብሎም ለክልላችን ሰላም መረጋገጥ የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ በክፍለ ከተማው ተጨባጭ ውጤቶች ስለመመዝገባቸው የተናገሩት ምክትል ስራ አስፈፃሚዋ ወ/ሮ አደራየ እነዚህን ስኬቶች አጠናክሮ ለማስቀጠልና የወጣቶች የአገር ግንባታ ተሳትፎ እንዲያድግ አስተዳደሩ በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

ለሰላም መረጋገጥ ወጣቶች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከደብረ ማርቆስ ኮሚኒኬሽን ለማግኘት ሊንኩን በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቲይብ፡https://youtu.be/Y0jeSQNM4o8
ቴሌግራም https://t.me/debremarkoscommunication
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php id=100064865823018...

13/10/2024

መደመር ከነጠላ ቡድናዊ እውነት ወጥተን ወደ ሁለንተናዊ የወል እውነቶቻችን የምንሻገርበት ድልድያችን ነዉ፡፡
የመደመር ትዉልድ መደመርን ሁለንተናዊ በሆነ አኳኋን የሚፈጽም፣ ኢትዮጵያን ከዕዳ ወደ ምንዳ ማሸጋገር የሚችል ትውልድ ነው፡፡

07/10/2024

#መደመር በለውጥ መንገድ ላይ የተወለደ የአተያይ ፓራዳይም ነው ። ቁስሎች እንዲጠገኑ ፣ ህመሞች እንዲድኑ ፣ ችግሮች እንዲፈቱ ፣ ፈተናዋች እንዲታለፉ ፣ ያለፈውን ጉዟችንን መመልከቻና የቀጣይ ጉዟችን ጠቋሚ ፣ አዲስ የእሳቤ ማዐቀፍ ነው ።

07/10/2024

"ሀገርን ለማዳን የምንሠራቸው ሥራዎች ብርሃናቸው ቦግ ብሎ ዛሬ ላይበራ ይችላል፡፡ ለሁሉም እኩል ላይታዩ ይችላሉ፡፡ ካለፈው የችግር ጊዜ እየወጣን መሆኑ፣ ወደ አዲስ ሀገራዊ ሁኔታ እየተሻገርን መሆኑ ለጊዜው ላይታወቅ ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ትንሣኤና ሕዳሴ ለሁሉም ግልጽ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል፡፡"

Address

Debre Markos
Debra Markos

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Niguss Teklehaymanot Sub City Addministration Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Niguss Teklehaymanot Sub City Addministration Communication:

Share