
31/08/2025
ግእዝ ባንክ ከአንበሳ ባንክ ጋር እንዲዋሀድ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ሰጠ
በምስረታ ሂደት ላይ የነበረው ግእዝ ባንክ አክሲዮን ማኅበር፣ ከአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር እንዲዋሃድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ፈቃድ መስጠቱ ተጠቁሟል።
ይህ ውሳኔ የተሰጠው የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የአክሲዮን ማኅበር አባላት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።
በውህደቱ ምክንያት የግእዝ ባንክ መስራች አባላት በፈቃደኝነት ወደ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ቤተሰብ እንዲቀላቀሉ ዕድል ተሰጥቷቸዋል።
ባንኮቹ በሰጡት መግለጫ፣ ውህደቱ የአክሲዮን ባለቤቶችን እሴቶችና እምነቶች የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም፤ ይህ ውህደት አዳዲስ እድሎችን ከመፍጠር በተጨማሪ፣ ለደንበኞች የሚሰጡትን የፋይናንስ አገልግሎቶች ተደራሽነትና ጥራት እንደሚያሳድግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
-Capital-