28/02/2025
ምኒልክ ያችን ሰዓት
(ጋሻው ደበበ አለሙ )
የካቲት 23/ 1888 ማለዳ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት እምዬ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ አድዋ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ያረጉት ፀሎት
……………….
መነሻ ሐሳብ- ማስረሻ ፈጠነ (ፕሮፌሰር)
አርትኦት ፡-አሰግደው ሸመልስ
……………………
ስብሐት ለእግዚአብሔር- ኅያው በመንበሩ
ሰላም ለዛቲ -ሃገሪትነ ቅድስት
ወሰላም ለህዝብየ- ዘይሔሉ ለምድሩ
ዘይመውት -ለክብሩ ፡፡
ምስጋና ለሕያው አግዚአብሔር
ሰላም ለዚህች -አንድ ቅድስት አገር
ሰላም ለደጉ ህዝቤ-አፈሬን ብሎ ለሚኖር
ክብር ላንተ-ሰማዕቱ የናት ያባቴ ታቦት
ጊወርጊስ መመኪያዬ-እንግዴህ ከፊቴ ዝመት
መንገድ ጥረግ ፈረሰኛው -ቀዳማዊው ሰራዊት
ተማርኩ ያለ አገር ሊዘርፍ-ውል አዛንፎ በለበጣ
የነገር ፈሩን ስንጨብጥ -ለሴራው ብልሐት ሲያጣ
ለጦር ልቡ ሸፍቶ -ዳር ድንበር ጥሶ ከመጣ
ፈርሐ-እግዜር የሌለው ጣሊያን -ህዝቤን በጅምላ ሲወር
በህዝቤ ተደምስሶ -አደዋ አረህ ውስጥ ሲቀር
በሟጥሽ ስር ተበትኖ -በአጋም ስራስር ሲሰባበር
እለቱ በደም ታፍኖ-ሰልስቱን በአሞራ ሲያከብር
ኪደነ-ምህረት ገሰሶ-ምንድብድብ ሸዊቶ ሜዳ
እማርክ ብሎ የመጣ -ሞቱ በአፍታ ቢረዳ
እኔ ክፉ እማይደለሁ -ልቤን ቅር እንዳይለው ነገር
መቼም ነፍሰ-እግዚሃር ነውና…
ክብር ለሃያሉ አምላክ -ቃሌን ቀድሜ ልናገር ፡፡
ቴወድሮስ ይሙት! ቃሌ ነው!!
እኔ ምኒልህ …
አይኑን ለጨፈነ ጠላት -እዝኑን ለደፈነ ጦረኛ
መልህቅ ቢያነሳ ብዬ እንጂ -ይሔ ነጭ ነውረኛ
አወድመው እንደሳት ሰደድ -እመታው እንደመጋኛ፡፡
አዬ ያገሬ ጀግና
አንጀተ ፅኑው ገበሬ
በማርያም መማፀኔን -ያገር አዋጄን ሰምቶ
ከመናገሻ እስከ ሀረር በጌምድር ተጠራርቶ
የአራት ማዕዘን -ጀግና ድፍን ኢትዮጵያ ተነስቶ
በሮቹን ባለህ ባይ ሳይኖር -ዝሪቱን ለተባይ ትቶ
ወንጭፉን ከማማ ሰቅሎ -ጦርና ጋሻ አንግቶ
ምኒልህ ጠራኝ ብሎ -በጭብጦ ተሸኝቶ
በእፍኝ ጥሬ-ከቤት ወጥቶ
ላመልታህል በኮዳ ውሃ-ከምንጭ በቅል ጠጥቶ
ለእግሩ ከለላ ሳይኖረው -አሜካላውን ጥሶ
ጫካውን በግር በፈረስ -ዥው አርጎት እንደኮሶ
ላገር ሟቹ ቃል ጠባቂው ይሔው አደዋ ከተመ
ለነፃነቱ እልፍ ሆኖ -ለክብሩ በአንድ ተመመ
የአብሮነት ቃልኪዳኑን -በባንዲራው ስም አተመ፡፡
እና ከዚህ በላይ -ምን ደስታ አለ?
ከህዝብና ከክብሩ- ሰው ካገሩ ከዋለ
እምነትና ጀብዱን ታጥቆ -አገሩን ብሎ ለመጣ ሰው
እስከ አፅናፍ የሚነገር -ድል ነው ፀዲቅ የሚቆርሰው፡፡
እንደ ቤተ-መቅደሱ -እንደ ሞገሩ ሽታ
እንደ ነጋሪቱ ድምፅ -መለከትና እምቢልታ
ተመስገን ያባቴ አምላክ -ልቤ ሃሴት ተሞልቷል
ሰማዕቱ በእለተ ቀንህ -ክንዴ እልፍ ጦር አንግቷል
ህዝቤ -አፎቱን ከፍቷል፡፡
ያባቴ ታቦት ….
ብቻ ህልም አየሁ በሰመመን…
አንጎለላ ኪዳነምህረት -ከደጅሽ የወይራ አፀድ
በቀስተዳመና ተከቦ- አንዱ ክንፍ ተቆርጦ ሲወርድ
ይሔ ሃሞተ መራር-ይሔ ልበ ተራራ
የሰው ምክር ግድ የለው-ትንሽ ለነፍሱ አይፈራ
ቀኝ እጄን እንዳላጣው- ክንዴን ገበየሁን አደራ
ስብሐት ለእግዚአብሔር- ኅያው በመንበሩ
ሰላም ለዛቲ -ሃገሪትነ ቅድስት
ወሰላም ለህዝብየ- ዘይሔሉ ለምድሩ
ዘይመውት -ለክብሩ ፡፡
ምስጋና ለሕያው አግዚአብሔር
ሰላም ለዚህች -አንድ ቅድስት አገር
ሰላም ለደጉ ህዝቤ-አፈሬን ብሎ ለሚኖር፡፡
ክብር ለአያቶቼ
ኢትዮጵያን ከነ-ስሟ -ከነ ክብሯ ላኖሯት
ጣሊያን ጉድጓዱ ይገባል -ዛሬም ማንም አይደፍራት
የካሳ እልፍኝ ይታዘበኝ -ጦር ሰልጥኜ ያደኩበት
ልበ-ባህሩ