
07/10/2025
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የገጠር ኢኮኖሚ ከላስተር አስተባባሪ እና ግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) የተሳተፉበት ጉብኝት በደብረ ብርሀን ከተማ በሚገኘው የብራዉን ፉድ ኢንደስትሪ ተከናወነ፤
ስለ ፋብሪካው ፋይዳ ገለጻ የሰጡት የብራውን ፉድ ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ አብርሃም በሰጡት ማብራሪያ ከ5.6 ቢሊየን ብር በላይ እየተገነባ የሚገኘው ፋብሪካው አስፈላጊውን የማሽነሪ ተከላ ሒደት በማጠናቀቅ በቅርቡ ወደ ማምረት ምዕራፍ እንደሚሸጋገር ገልጸዋል።
ፋብሪካው ሲጠናቀቅ ሊሰጣቸው የሚችሉ የምርት አይነቶችን ያብራሩት ስራ አስኪያጁ በቫይታሚን የበለጸገ ዱቄት፣ የህጻናት አልሚ ምግብ፣CDB+ ፣ለቢራ ፋብሪካ ገብስን የሚተካ የበቆሎ ብቅል፣ የእንስሳት መኖ ተረፈ ምርት የሚያመርት መሆኑን ገልጸዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የገጠር ኢኮኖሚ ከላስተር አስተባባሪ እና ግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉ(ዶ/ር) ከለውጥ አመታት ወዲህ የደብረ ብርሀን ከተማ የኢንደስትሪ መዳረሻ ከመሆኗ ባሻገር ሀገራችን ለተለመችው ሁለንተናዊ ብልጽግና መሰረት የሚጥል ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
በዛሬው እለት በጉብኝታቸው የተመለከቱት የብራዉን ግድ ፋብሪካ የሚጠቀማቸው ግብዓቶች ሙሉ በሙሉ በሀገራችን የሚገኝ በመሆኑ ግብርናውን ከኢንደስትሪው ጋር የማስተሳሰር ግባችንን እውን የሚያደርግ እንደኾነ ገልጸዋል።
በጥቅሉ የተገነቡ የሚገኙ ተስፋ ሰጪ ፋብሪካዎች የከተማ አመራሩ ለኢንቨስትመንት የሰጠው ትኩርተ ከፍተኛ እንደሆነ አመላካች መሆኑን ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ገልፀዋል።
በጉብኝቱ የደብረ ብርሀን ከተማ ተከዳሚ ከንቲባ የተከበሩ በድሉ ውብሸት የደብረ ብርሀን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ጌታቸው፣ የሰሜን ሸዋ ብልፅግና ፖርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ አበበ ጨምሮ ሌሎች የከተማው አስተዳደር እና የዞን አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።