Bishoftu Multi Media

Bishoftu Multi Media About different activities in Bishoftu city

05/01/2022

የቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎች የበጎ አድራጎት ህብረት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ 40 የዘማች ለቤተሰቦች 25 ኪ.ግ ጤፍ, 3ሊትር ዘይት,300ብር እና የተለያዩ አልባሳትን በመለገስ አለኝንታነቱን ገለፀ።

 # ስለ ቢሾፍቱ ለትዉስታ...Magaalaan Bishooftuu kan hundeeffamte bara 1917 ta'us,kan Mana Qopheessaatiin buluu eegalte bara 1943...
05/01/2022

# ስለ ቢሾፍቱ ለትዉስታ...
Magaalaan Bishooftuu kan hundeeffamte bara 1917 ta'us,kan Mana Qopheessaatiin buluu eegalte bara 1943 irraa eegale akka ta'e seenaan ni ibsa.
Haaluma kanaan bara 1943-2013tti muudamtootaa fi kantiiboota 22tiin bulte jirti.
Sadarkaa guddina kallatti maraan agarsisaa jirtuu keessatti gahe mataa isaanii taphachaas turan,Muudamtoonni fi kantiiboonni kunneen.

ቢሾፍቱ ከተማ በ 1917 ዓ.ም የተቆረቆረች ብትሆንም በመዘጋጃ ቤት መተዳደር የጀመረችዉ ከ1943 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ።

በዚሁ መሰረት ከ1943-2013 ዓ.ም ድረስ በ 22 ሹሞችና ከንቲባዎች ስትተዳደር ቆይታለች።

ለዛሬዋም ቢሾፍቱ እድገትና ልማት የበኩላቸዉን አስተዋፆ ያደረጉና አሁን ለደረሰችበትም የእድገት ጎዳና መሰረት መሆን ችለዋል።

አመራሮቹን በቅደም ተከተል ለመመልከት:
1943-አቶ ካሳ ተገኝ, - አቶ ብርሃኑ ድፋዬ, - አቶ አስራት ሃ/ማርያም, - አቶ ሃ/ማርያም መንገሻ,1958-1967 ቀ/ገብረክርስቶስ መኮንን,1967-1971 አቶ አበበ ፅጌ,1972-1976 ማ/ቴ ወርቅነህ ወልደየስ,1977-1983 ማ/ቴ ሀሰን አብዲ 1983- 1985 አቶ ግርማ እሸቴ, 1985-1986 አቶ አበበ ሽብሩ, 1986-1992 አቶ አለማየሁ አብዲ, 1992-1993 አቶ መለሰ አለሙ, 1993-1994 አቶ ቦኬ ሚደግሳ, 1995-1996 አቶ ሳሙኤል ጉርሜሳ, 1996-1997 አቶ ደሳለኝ ረጋሳ,1997-1999 አቶ ስለሺ ጎዴ,1999-2003 አቶ ድሪባ ቱራ,2003-አቶ ከፍያለዉ አያና,-ዶ/ር ዳዲ ወዳጆ,- ወ/ሮ ገነት አብደላ, - ወ/ሮ አለም ፀሃይ ሽፈራዉ ሲሆኑ በአሁን ስዓት ከተማዋን በመምራት ላይ የሚገኙት ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ ይሰኛሉ።

04/01/2022

...የቢሾፍቱ ከተማ አመሰራረት...

የቢሾፍቱ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ 47ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምስራቅ ሸዋ ዞን የምትገኝ ውብ ከተማ ናት።
ከተማዋ የተቆረቆረችዉ በ1917 እ.አ.አ ሲሆን ለንስረታዋም ታሪካዊ አጋጣሚ ሊሆን የቻለዉ ጅቡቲንና የሚያገናኘዉ የባቡር ሀዲድ መንገድ መዘርጋት ነበር።
ይኸዉም በድንጋይ ከሰልና በዉሃ እንፋሎት ሃይል ይጓዝ የነበረዉ ባቡር ግለቱን ለማቀዝቀዝ በየጣቢያዉ ከ 2 እስከ 3 ስዓት በሚቆይበት ጊዜ ነዋሪዉ ህዝብ ለተጓዡ መንገደኛ እንደ ህብስት፣ቅቅል ስኳር ድንጅ፣ትርንጎና ሸንኮራ አገዳ እንዲሁም ጠላና ብርዝ ወዘተ መሸጥ ተለማመድ።
ከዚያም ቀስ በቀስ በባቡር ጣቢያዉ ዙሪያ ገብ እየተቀለሱ የነዋሪዉም ብዛት እየጨመረ በመሄዱ የቢሾፍቱ ከተማን መቆርቆር እዉን አደረገዉ።
ከተማዋ ቢሾፍቱ የሚለውን የሚለዉን ስያሜዋን ያገኘችዉ በከተማዋና አካባቢዋ ከሚገኙት ለዘመናት መገለጫዋ ሆነዉ ከዘለቁት ድንቅ ተፈጥሮአዊ ሀይቆች ሲሆን ስያሚዉም በአፋን ኦሮሞ አጠራር ቢሻኖፍቱ ከሚለዉ ነዉ፣ ትርጓሜዉም የዉሃ ምድር የሚለዉን የአማርኛ ቃል ይወክላል።

ከ1947ዓ.ም ጀምሮ በንጉሰ ነግስት አፄ ኃ/ሥላሴ ደብረዘይት ተብላ ብትሰየምም የገጠሩ ነዋሪ ግብ በተጓዳኝነት በጥንት ስሟ ቢሾፍቱ የሚለዉን ስም ይጠቀም ቆይቷል።
ከ1984ዓ.ም በኋላ ግን ደብረዘይት የሚለዉ ስሟ በቀድሞ ስሟ በቢሾፍቱ መጠራት ጀመረች።
የከተማዋ ማዘጋጃ ቤትም በ1943ዓ.ም ከግለሰብ በተከራየዉ ቤት ውስጥ ስራዉን አንድ ብሎ ጀመረ።
ከዚያም የአደአ ወረዳ ዋና ከተማ በመሆን በተለያዩ የከተማ ሹሞች ስትተዳደር ቆይታ ከ1996ዓ.ም ጀምሮ በአዲሱ የከተማ ሪፎርም ዉስጥ በመግባት የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በመባል በከንቲባ በመተዳደር ላይ ትገኛለች።

Address

Debre Zeyit

Telephone

+251910267005

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bishoftu Multi Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Bishoftu Multi Media:

Share