BATI Barking News

BATI Barking News ኢትዩጵያ የፍቅር አገር

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገአዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ...
07/01/2025

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በላከው መረጃ መሰረት÷ ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ተወስኗል።

በዚሁ መሰረት አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር፣ አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር፣ አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር፣ አንድ ሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር፣ አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር እንዲሁም አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር ሆኖ እንዲሸጥ መወሰኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ፓሊስ መረጃ  ታህሳስ 8/2017ዓ/ም (ከባቲ)🚦 ✍️✍️✍️  🚘🏍🚲 ✍️✍️✍️ 🚦👉 ለባቲ ከተማ አሽከርካሪዋች በሙሉ 👈ነገ ማለትም እሮብ ታህሳስ 9/2017ዓ/ም  #በከተማ አስተዳደራችን ለሚ...
17/12/2024

ፓሊስ መረጃ ታህሳስ 8/2017ዓ/ም (ከባቲ)
🚦 ✍️✍️✍️ 🚘🏍🚲 ✍️✍️✍️ 🚦
👉 ለባቲ ከተማ አሽከርካሪዋች በሙሉ 👈
ነገ ማለትም እሮብ ታህሳስ 9/2017ዓ/ም #በከተማ አስተዳደራችን ለሚካሄደዉ የድጋፍ ሰልፍ ያለምንም የፀጥታ ችግር እና የትራፊክ ፍሰት እንዲከናወን ለማስቻል ብሎም ለማስተባበር እንዲያመች ሲባል "ከጧቱ 12:00 ሰአት ጀምሮ ሰልፉ እስከሚያልቅ ሰአት ድረስ"
1ኛ, ባለ3 እግር ባጃጅ
2ኛ, ባለ 2 እግር ምተር ሳይክል 🏍🏍 ተሽከርካሪዋች
3ኛ, ባለ 2 እግር ፔዳል ሳይክል 🚴‍♀️🚴‍♂️ እና
4ኛ, ጋሪን ጨምሮ
በከተማ አስተዳደሩ ዉስጥ ተሽከርካሪን ፈፅም ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስም ሆነ ማሽከርከር 🚫🚫🚫 የማይቻል መሆኑን የከሚሴ ከተማ ፓሊስ ጽ/ቤት ገልፃል።
🔗🔗🔗🔗🔗🔗🔗🖇🖇🖇🖇🖇🖇🖇
የከተማችን ማህበረሰቦች እንዲሁም የከተማችን ወጣቶች ከፀጥታ መዋቅሩ (ሀይሉ) ጎን በመሆን የተለመደዉ ትብብራችሁ እንድታደርጉ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን።
"የባቲ ከተማ ፓሊስ ጽ/ቤት"

ሰበር ዜና...... ለመላው ለኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ህዝብ በሙሉ እንኳን ደስ አላቹሁ።ለተርጋ፣ለቦሎ፣ለመንጃ ፍቃድ፣ለመርሃግብር፣ለስም ዝውውርና የተለያዩ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ደሴና...
16/11/2024

ሰበር ዜና......
ለመላው ለኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ህዝብ በሙሉ እንኳን ደስ አላቹሁ።
ለተርጋ፣ለቦሎ፣ለመንጃ ፍቃድ፣ለመርሃግብር፣ለስም ዝውውርና የተለያዩ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ደሴና ደብረብርሃን እየሄድን ምንያክል ለሙስና ስንጋለጥ እንደቆየን በበጃጅና በመኪና ስራ ላይ ያላቹሁ ሰዎች በደንብ ያውቁታል።ጊዜና ሁኔታዎች የማይቀይረው ነገር የለም ዛሬ በኛው ዞን ከሚሴ ከተማ ላይ ስራ መጀምሩን ስሰማ በጣም ደስ ብሎኛል።
እንኳን ደስ አላቹሁ በድጋሚ❤

BAGA GAMADDAN..❤

Eebbifame!
Eeyyamni konkolaachisummaa sadarkaa godina keenyaatti akka kennamuuf guyyaan har,aa bakka bulchaan godina saba oromoo obbo Ahmed Ali abbafuroo fi gahee qabeessonni hundi argamanitti eebbifameera. Dhugaa dubbachuuf hojiin kun akka milkaahuuf Ahmed Hasuu fi Abdalla sheh Ahmed gahee leencaa taphataniiru.

23/08/2024
ጉድ ተመልከቱ ውሸት ተጫወቱብኝ ‼️የዛሬ አመት የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ በጀት የወጣበትን እዩ ፣  የሀይል መቆራረጥና መዋዠቅን ለመቀነስ ትራንስፈርመር መልሶ ግንባታና  መቀዬር በመሰራት ላይ...
28/06/2024

ጉድ ተመልከቱ ውሸት ተጫወቱብኝ ‼️

የዛሬ አመት የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ በጀት የወጣበትን እዩ ፣ የሀይል መቆራረጥና መዋዠቅን ለመቀነስ ትራንስፈርመር መልሶ ግንባታና መቀዬር በመሰራት ላይ ይገኛል ይላል ...!

ለደሴ / ለሀይቅ / ለባቲ ከተሞች የተበጀት ሲሆን ፣ ደሴ ና ሀይቅ ከተሞች ሙሉ ለሙሉ የመብራት መቆሬረጥ ተቀርፎላቸው ፣ በተለይ ሀይቅ 33ሺkv ተደርጎላት ችግሩ ተቀርፏል ።

ሞኙ የባቲ ህዝብ ላይ ግን ቀለዱበት 😥 የትራንፈርመር ፖል ቀየሩና ራንሰፈርመሩ ግን በአለበት ሳይቀየረ ቀረ ፣ ለምን ጠያቂ የለማ ? አመሩራም አፋጦ አይጠይቅ ፣ መብራት ሃይል ሀላፊውም እንደዚሁ ፣ ደሴ ድስትሪክትም ለባቲ ከተማ የማይጨነቁ ናቸው። 58 ሚሊዮን 385 ሺ ሀያ አምስት ብር ተመድቦ በጀቱ ያለቀው ደሴ ና ሃይቅ ላይ ነው ።

እሺ ተሰራ ይበሉ የታሉ ሀይል ና መቆራረጡ ? መች ቀረ ጭራሽ ባሰበት መጥፋቱ ሳይጠፋ ውሎ አያቅም ፣ በሳምንት 2 ግዜ ብቻ እሚበራው ፣ በዚህ ጉዳይ የባቲ ልጆችን መብራት ሃይል እሚሰሩትን ጠይቁማ ፣ ውስጣቸው ተቃጥሏል በባቲ መብራት ጉዳይ ።

እድሜ ልካችንን በማብራትና በውሃ ምክንያት መጫወቻ መሆናችን እጅጉን ያሳዝነኛል

አስከ አሁን ባለው ጊዜ ብዙዎቹ በቀዳሚነት  #ባቲን የመሩ መሪዎች ለአገራችን ለከተማችን ለህዝባችን ተጠቃሚ የሚያደርግን ነገር ከማሰብ ሌሎች ነገሮች እንቱፈንቱዎች ያሳስቧቸዋል በዚህ ምክንያት...
28/06/2024

አስከ አሁን ባለው ጊዜ ብዙዎቹ በቀዳሚነት #ባቲን የመሩ መሪዎች ለአገራችን ለከተማችን ለህዝባችን ተጠቃሚ የሚያደርግን ነገር ከማሰብ ሌሎች ነገሮች እንቱፈንቱዎች ያሳስቧቸዋል በዚህ ምክንያት እስከ ዛሬዋ ቀን የመሩን መሪዎች በጣም የሚገርመኝ ነገር የተመሳሳይ ባህሪ ባለቤት መሆናቸው ነው !

ተመሳሳይ ባህሪያቸው/የመሪነት ጥበብ በባቲኛ ከብዙ ጥቂቱ 😋

-ቃል ይገባሉ ቃሉ ግን ተግባራዊ ሲሆን አናይም ቃሉ ተፈጻሚ የሚሆነው ጅቡቲ ይሁን የት ይሁን ዋቃ ይወቀው

- የተማረ ልምድና እውቀት ያካበቱ ልጆችን አቅርቦ አያማክሩም አያሰሩም የተበለጡ ስለሚመስላቸው

- የተሻለን ሰው አያዳምጡም እኔ ያልኩት ካልሆነ እንጂ በሚል የበታችነት ኢጎ በፈሳሽ መልክ ጠጥተው ሰክረዋል

- ዞን ያሉ አመራሮችን ባለሙያዎችን ጭምር እንደ ጦር ፈርተው መጠቀሚያ ይሆናሉ በተጨማሪ እንደ ባቲነታችን ጭምር ያስነቃሉ ያስኮሰምናሉ/የመንግስት አሰራር እንዳለ ሆኖ

- ሀሳብ አይገዛቸውም የጋራ ብለህ፣ ለአገር ብለህ የምታነሳውን ነገር አጥሞና አጣሞ በሌላ አሉታዊ ነገር መፈረጅ ይቀናቸዋል

- ከአገራዊ እድገት ለውጥ ከህዝብ ጥያቄ በተሻለ ሴራ ነገር ተንኮልና ሃሜት ያሳስባቸዋል እንቅልፍ ይነሳቸዋል

- እንደ መንግስት እንደ ፓርቲ የሚሰጥን ተልእኮ ከመፈጸም የግለሰብን የዞን አመራርን ቃል ትዕዛዝ መስማትና መፈጸም ትልቁ ግብና አላማቸው አድርገው ያስባሉ/የመንግስት አሰራርና አካሂድ እንዳለ ሆኖ አሁንም

- በትንሽ ስራ መደሰት ያበዛሉ አገር ያሳደገ በመሰረታዊነትም ይሁን በተወሰነ ደረጃ የህዝብን ጥያቄ የመለሱ መስሏቸው በአጫፋሪ እስክስታ መውረድ የደስታቸው ጥግ አድረገው በውሻሸት ጭብጨባ ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ገብተው ይጠፋሉ

- ሀሳብን በመፍራት አስረሀለው እንደዚክ አደርጋሀለው በሚል ማስፈራራት ማሸማቀቅ ማሰርን እንደ ጀብዱ አድርገው ያስባሉ

- ባልተሰራ ስራ መመስገን መወደስን አልፎም ካባ እንዲያጠልቁላቸው አብዝቶ መፈለግን Birth dayያቸው አድርገው ይቆጥራሉ

- ቡድን በመፍጠር አንዱን በ አንዱ ላይ ወንድም በ ወንድም ላይ ቂም ጥላቻ እንዲይዝ አልፎም አሳልፎ በመስጠት ቀን ከሌት ይደክማሉ

- ትንሽ ለአገሩ የሚሰራን አካል በተለያየ መንገድ ጠልፎ መጣልና እስከነ ተሰዶና ላይመለስ አድርጎ ማባረርን ዝና አድርጎ መቁጠርን ስኬት ነው ብለው ያስባሉ

-ስልጣን እኔ እንደምወደው በለው ወጥ አጥብቀው ይወዳሉ ለዚህ ደግሞ የማይከፍሉት መስእዋትነት የለም አንድ በታሪክ የማውቀው ሰው ለስልጣን ብሎ እናቱን ተኩሶ እንደገደለው 😥
ይሄ ሁሉ የኛ አገር የመሪነት ባህሪ ጥበብ እስከ አሁን በመሩን መሪዎች ላይ የነበረና አሁንም የቀጠለ ነው።ሁሉ ነገር ተሳክቶ ከተማችንን የምትፈልገውን ነገር አሟልተው የህዝቡን ጥያቄ መልሰው ለከተማችን የሚገባትን ስራ ጨርሰው መሆኑ ደሞ ለየት ያደርጋቸዋል አትሉም 😀

ስለዚህ ከዚህ በፊትም ዛሬም የመሩን መሪዎች ያኔም ዛሬም ስራ ላይ ናቸው ስለ አንተ መብራት ውሃ ችግርና ሌላ ተጨማሪ ፍላጎቶች ለማሰብ ጊዜ አልነበራቸውም ነበር ዛሬም የላቸውም ነገ የሚመጡትም የላቸውም !!

መሪነት ህእ 😊

Note: እንደ መሪ እንደ ህዝብ መሪ እንደ እኔ መሪ ስለመሪነታቸው ባህሪ መናገሬ መግለጼ እንጂ ፐርሰናሊትን/የግልን ማንነት ባህሪን መሰረት ያደረገ አይደለም በጣም ልዩነት ስላለው ምክንያቱም መሪ ባይሆኑ ይሄን ሁሉ ባህሪ አያሳዩንም እኔን የሚመሩ ባይሆኑ ኖሮ እኔም አልናገርም 🙌

🤝በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላኛውን በመሪነታቸው የሰሩትን መልካምና የሚሻገር ስራቸውን እናወሳለን !

ሰላም ለአገራችን ሰላም ለባቲያችን !

Address

ደሴ
Dessi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when BATI Barking News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share