Eng'r MohammedJewad- ኢ/ር መሃመድ ጀዋድ

Eng'r MohammedJewad- ኢ/ር መሃመድ ጀዋድ ነፃ፣ ፍትሃዊ ሃሳብ

27/05/2025

"በህይወቴ የሚፀፅተኝ ነገር ቢኖር ከብልፅግና ጋር መቆሜ ነው ... አንድም ቀን ቢሆን እራሱ ፅዋው መራራ ነው"... መሳይ መኮንን ከብልፅግና ጋር በድጋሚ አብሮ እንዲሰራ በሜጀር ጀነራል ተስፋይ አያሌው ሲጠየቅ የሰጠው ምላሽ ነው 😀

ሰው በዚህ ልክ ብልፅግናን የሚጠየፍበት ጊዜ ላይ ደረሰን። ኢህአዴግ እንደዚህ ቢባል ኖሮ .."በስብሰናል ፣ ሬት ሬት ብለናል" ... ብሎ በቅፅበት ግምገማ ማድረግ ይጀምር ነበር።

ብልፅግና ግን ለውጡ ፣ እድገቱ ያመጣው በጎ ተፅዕኖ ነው ብሎ በለመደው የፕሮፓጋንዳ ማጀብያ ጭፈራ መወራጨቱን ቀጥሏል 😀

 INSA- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር   በዘርፉ ተሰጥኦና ፍላጎት ያላቸው ታዳጊ ወጣት ተማሪዎችን በክረምት/ሰመር ትሪፕ ለማሰልጠን ይፈልጋል።ፍላጎቱ ያላችሁ ቀጥሎ ባለው Link...
27/05/2025



INSA- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በዘርፉ ተሰጥኦና ፍላጎት ያላቸው ታዳጊ ወጣት ተማሪዎችን በክረምት/ሰመር ትሪፕ ለማሰልጠን ይፈልጋል።
ፍላጎቱ ያላችሁ ቀጥሎ ባለው Link በመግባት በፍጥነት መመዝገብ ትችላላችሁ።

https://talent.insa.gov.et/?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR5o32GAV-zSO4pk2NwL3Asz_1pNn5edHzBfZ1HYrAx2AUYaEAWT_b86cCKWZA_aem_N_l7t3f7HXx2yV08-LxJnw

ወላጆች ፍላጎት ያላቸውና በዘርፉ ላይ ሆቢ ያላቸው ልጆቻችሁን ፍላጎት ካላቸው አግዟቸውና እንዲመዘገቡና እንዲመረጡ ርዷቸው።

02/06/2023

በታላቁ አንዋር መስጂድ በሰላማዊ ምእመናን ላይ የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ከሚመለከተው የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ጋር የተፈጠረውን ቀውስ ለማረጋጋት እና ባስቸኳይ የተጎዱትን ለማትረፍ በሚቻልበት መንገድ ላይ እየተነጋገሩ ቆይተዋል::

በተፈፀመው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ወንድሞቻችን የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ አምቡላስ ወደ ቦታው እንዲደርስ እያደረጉ ይገኛሉ::

ታላቁ ኣንዋር መስጂድ ከውጥረት ነፃ እንዲሆን ፣በመስጂዱ ውስጥ የሚገኙ ምዕመናንም በሰላም ወደቤታቸው እንዲገቡ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼይኽ ሱልጣን አማንን ጨምሮ ሶስት ከፍተኛ አመራሮች ከመጅሊሱ ተወክለው ወደ ቦታው በማምራት ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ይህን ተፈፃሚ እንዲሆን እየሰሩ ይገኛሉ::

ከሁሉም ነገር በፊት ሰብኣዊነት መቅደም ስለሚኖርበት የተጎዱትን ወደ ህክምና ቦታ ለማድረስ እና በመስጂዱ ያሉ ምዕመናን በሰላም ወደቤታቸው እንዲገቡ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በአንዋር መስጂድ እና በዙርያው ያለው የፀጥታ ኀይሉም ይህ ተፈፃሚ እንዲሆን የበኩሉን ሓላፊነት እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን::

Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር

 || የኢማም አህመድ ልጆች!!ምንም እንኳ የፍቅር፣የመቻቻልና የአብሮነት ተምሳሌት ቢሆኑ  የኢማም አህመድ ልጆች በእምነታቸው የመጣን የሚችሉበት ትከሻ የሚታገሱበት ልብ የላቸውም!!ሀረሬወች በ...
02/06/2023

|| የኢማም አህመድ ልጆች!!

ምንም እንኳ የፍቅር፣የመቻቻልና የአብሮነት ተምሳሌት ቢሆኑ የኢማም አህመድ ልጆች በእምነታቸው የመጣን የሚችሉበት ትከሻ የሚታገሱበት ልብ የላቸውም!!

ሀረሬወች በዛሬው ዕለት" ከእምነታችን የምናስቀድመው ምንም ነገር የለም!" በማለት ድምፃቸውን አሰምተዋል

02/06/2023

እርዳታ እስክታገኙ መስጂድ ያላችሁ ይሄን መንገድ ተጠቀሙ
1. የተጎዳው ቦታ ላይ በእጃችሁ ተጨጫኑት
2. ያገኛችሁትን ጨርቅ ነገር በመጠቀም ተጨማሪ ደም እንዳይፈስ ቁስሉን ሸፍኑት
3. እንደ ቀበቶ ያለ ነገር በመጠቀም ቁስሉን እሰሩት

ከዛም ተጨማሪ ሙቀት እንዲያገኙ የሚደረብ ነገር ደርቡላቸው.. ሊያስመልሳቸው ካለ ሰውነታቸውን አንቀሳቅሱት .. አላህ ይርዳን

መግደሉ አንሷቸው የቀሩትን ዘግተው ቆይተው አፍሰው ወስደው ለማሰር አውቶብስ አምጥተዋል።ያ ጀማዓ የንቄታቸው ጥግ እዚህ የደረሰበት የኛስ ዝም ማለት ከምን የመጣ ይሆን? አሁን አንዋር መስጅድ ...
02/06/2023

መግደሉ አንሷቸው የቀሩትን ዘግተው ቆይተው አፍሰው ወስደው ለማሰር አውቶብስ አምጥተዋል።

ያ ጀማዓ የንቄታቸው ጥግ እዚህ የደረሰበት የኛስ ዝም ማለት ከምን የመጣ ይሆን?
አሁን አንዋር መስጅድ የዘጉባቸውን አፍሰው ለመውሰድ አውቶብስ አምጥተዋል‼

22/03/2023

በላይ ነህ ክንዴ 10 ሚሊዮን አውጥቶ ሲገዛ ወርቁ አይተነው ደግሞ አክቲቪዝሙን ተያይዞታል😂

22/03/2023

ዘመነ መሳፍንት እና አንዳንድ ነገሮች
-
👉 አገር የተከፋፈለበት እና እርስበርስ ጦርነት✖️
👉 የማዕከሉን ስልጣን ለመያዝ ፉክክር የጦፈበት✔️

ዘመነ መሳፍንት
-
👉 ነገሥታቱን በመግደልና በማዋረድ በየአካባቢው መሳፍንቱ እየገነኑ እንዲሄዱ ያስጀመረው ራስ ሚካዔል ስሁል ነው።
-
👉 አገር እንዲያረጋጋ ዘጠኝ የአካባቢ መሳፍንቶች ደጃዝማቾች ተስማምተው የመረጡትና የራስ ሚካዔል ስሁልን ልጅ በጦርነት በመግደል የሁሉም የአካባቢ መሳፍንቶች የበላይ በመሆን ሚካዔል ስሁል ያዳከመውን ማዕከላዊነት እንደገና ነፍስ የዘራበት ራስ ቢትወደድ ቀዳማዊ ዓሊ ጓንጉል (ታላቁ ዓሊ) ነው። የበጌምድር ወይዛዝርት በወቅቱ ዓጼ ተክለ ጊዮርጊስ አንገፍግፏቸው
ዓሊ ና ፣ ዓሊ ና፣ ዓሊ ና በሞቴ
ተክለ ጊዮርጊስን ሰለቸው አንገቴ
በማለት ስንኝ ቋጥረዋል።
-
👉 ይህ ዘመን የርስበርስ ጦርነት የነበረበት የሚባለው ማስረጃ የሌለው ጥቅል ስሁት ድምዳሜ ነው። በአንጻራዊነት ከዘመነ መሳፍንት በፊት ከነበረው ከእነ ዓፄ ኢዮአስም ሆነ ከሚካዔል ስሁል አገዛዝ ዘመን እንዲሁም ከዘመነ መሳፍንት በኋላ ከመጡት ከዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ዘመን አንጻር ዘመነ መሳፍንት ጦርነት ጋብ ያለበት እና ማዕከሉን ለመያዝ ከሚደረግ ዝግጅትና ፉክክር በቀር በአንጻራዊነት ጦርነት የበረደበት ጊዜ ነው።
-
👉 በ70 ዓመታት የዘመነ መሳፍንት ጊዜ ውስጥ የተካሄደው ጦርነት ብዛት በዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ የ13 የአገዛዝ ዓመታት ከተካሄደው ጦርነት አንጻር በቁጥር ያንሳል። የጦርነቶችን ብዛት እስከ ቦታቸው ድረስ ማስቀመጥ ይቻላል።
-
👉 የዳግማዊ ዓጼ ምኒልክ ዜና መዋዕል ጸሀፊ ጸሀፈ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ በዚያ ዘመን የበላይ ስለነበሩት የእቴጌ ጣይቱ ብጡል አያቶችና ቅድመ አያቶች ሲያወሱ ዘመኑ የተድላ፣ የፌሽታ፣ እህልና መጠጥ ሞልቶ የተትረፈረፈበት ዘመን እንደነበር ይገልጻሉ። በአንጻሩ የቀዳማዊ ዓጼ ኃይለ ሥላሴ ባለሟል ብላቴንጌታ ህሩይ ወ/ሥላሴ በእሳቸው ዘመን በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እንደ ዓጼ ቴዎድሮስ የአገዛዝ ዘመን ዓይነት ወቅት እንዳይመጣ በቅዳሴ ሳይቀር ይቀደስ እንደ ነበር በመጽሀፋቸው አስቀምጠዋል።
-
👉 ከዳግማዊ ዓጼ ቴዎድሮስ በፊት የነበረው ራስ ቢትወደድ ዳግማዊ ዓሊ ከምጽዋ እስከ እናርያ ድረስ ያለውን አገር ሁሉ ያስተዳድር እንደነበር ፈረንሳዊዩ ዲባዲ እና ሌሎችም ጽፈዋል። ባለ ራዕዩ ዳግማዊ ዓጼ ቴዎድሮስ ራዕዩ ያልገባቸው ባለባቶች ጋር እየተዋጋ በጌምድር፣ ሸዋ፣ ወሎና ጎጃምን እንኳን ሙሉ ለሙሉ ማስተዳደር አልቻለም። ዳግማዊ ዓጼ ቴዎድሮስ ዘመን ተሻጋሪ ህልምና ራዕያቸውን በግሌ ታላቁ መሪ እንድላቸው ያስገድደኛል ግን ነባራዊ ሁኔታው አልፈቀደላቸውም።ራዕያቸው ቢሳካ ልክ እንደ አውሮፓውያን የምንሆን ይመስለኛል።
-
👉 “ዘመነ መሳፍንት” የሚባለው መጠሪያ ስያሜ አሁን በ1960ዎቹ በታሪክ ሙህራን ከብሉይ ኪዳን የአይሁድ ታሪክ ጋር እንዲመሳሰል ለማድረግ የሰጡት ስያሜ እንጂ ከዚያ በፊት በየትኛውም የታሪክ መዛግብት የሌለ ሰያሜ ነው። የብሉይ ኪዳኑ ዘመነ መሳፍንት ደግሞ ከኢትዮጲያው ታሪክ ሁኔታ ጋር ፍጹም የማይገናኝ ነው።
-
👉 በኢትዮጲያ ታሪክ ውስጥ “ዘመነ መሳፍንት” የሚባለው ታሪክ መጠሪያ ስያሜው “ዘመነ ወረሴኸ” ቢባል የሚቀርብና የተሻለ ስያሜ ነው።
-
👉 የኢትዮጲያ ዘመናዊ ታሪክ ጸሀፊወች ወረሴኾችን “የየጁ ኦሮሞዎች” እያሉ ለብሄር ብሄረሰብ ታሪክ መዋጮ ለማድረግ የሚሰጡት ሀተታ እጅግ የተዛባና አናዳጅ ነው። ወረሴሆች የአረብ፣ የኦሮሞ እንዲሁም የአማራ ዝርያ ያላቸው፣ በአማርኛ ቋንቋ የሚናገሩና አፋቸውን የፈቱ፣ ከክርስትያን እና ሙስሊም ማህበረሰብ የወጡ እና የሁለቱንም እሴት የያዙ ናቸው። ኢህአዴግ በተከለው በዛሬው ዘመን የብሄር አመዳደብ “አማራ” ተብለው በቀዳሚነት የሚቀመጡ ናቸው።
-
👉ወረሴኾች የግድ ወሎየወች ብቻ ናቸው ማለት አይደሉም፤ ወረሴኽ ሲባል አካባቢን አይገልጽም። የጎንደር ወረሴኾችም አሉ። ወረሴሆች ጎንደሬም ፣ ወሎዬም ሌላም ሊሆኑ ይችላሉ (የጎጃም እና የትግራይ ወረሴኾችም አጋጥመውኛል)፤ እንዲሁም ክርስትያንም እስላምም ሊሆኑ ይችላሉ መደላደያ መነሻቸው ግን የየጁ፣ ላስታ፣ አምባሰል፣ ዋድላ እና ራያ አካባቢወች ናቸው። ከዚያ ደግሞ የታሪካቸው ከፍታ የሚገኘው እና የታየው በጌምድር ነው።
-
👉 ዘመነ መሳፍንት ✖️
👉 ዘመነ ወረሴኽ ✔️
ጋሽ Andargachew Tsegeን ጨምሮ ጸሀፊወችና ተንታኞች የጽሁፋችሁ እና የትንታኔ ማድመቂያችሁ በማድረግ በተደጋጋሚ ለአሉታዊ ምሳሌነት የምትጠቀሙትን ነገር እንደገና ብታዩት እወዳለሁ።

Brook Abegaz

22/03/2023

በቴምር ማፍጠር ሱና እንጂ ግዴታ አይደለም፣ ከ25 ኮንቴነር በላይ ቴምር ከሳምንት በኋላ ይገባል፣ ስግብግብን ትቶ መቅጣት ነው።

21/03/2023

አብዱ ኤቢ
ዘመን ተሻጋሪው
አሊ ወሎ
Birhan Nega
Temr Hassen
Leila Yimam Ayalew
Seyoum Ahmed Seid
Ahmed Jemal
Yishak Zewdu

እንኳን ለ1444 ዓመተ ሂጅራ የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ፣
📌ፆማችሁ መቅቡል የሚሆንበትን የጥራት መንገድ አላህ ይወፍቃችሁ‼
📌 የህይወት ምዕራፍ ለውጥ የምታገኙበት ወር ይሁንላችሁ፤ ወሩ የረህመት ወር ነዋውና አላህ ቀናውን መንገድ ይምራን 👏👏👏👏

20/03/2023

አብዱ ኤቢ የምትባል 1 ሜትር ከሱሙኒ የሆንክ ደላላ የግል ስር ቤት እፈልጋለሁ፣ በጣም አዋጭ ስለሆነ በአስቸኳይ አፈላልግና አቅርብልኝ‼

ሙያ ያኮራል!!!ከተጣበቁበት የለያያቸውን ዶ/ር ለማመስገን ከዮርዳኖስ  ሳኡዲ የመጡት ህፃናት!የሳኡዲው ዶክተር Dr. Abdullah Al-Rabiah ተጣብቀው ተወልደው በቀዶ ጥገና በሰላም የለ...
20/03/2023

ሙያ ያኮራል!!!
ከተጣበቁበት የለያያቸውን ዶ/ር ለማመስገን ከዮርዳኖስ ሳኡዲ የመጡት ህፃናት!

የሳኡዲው ዶክተር Dr. Abdullah Al-Rabiah ተጣብቀው ተወልደው በቀዶ ጥገና በሰላም የለያያቸው መንታ ልጆች ጋር ድጋሚ ተገናኘ።

ዶክተሩ ተጣብቀው ተወልደው የነበሩትን ሁለቱን የዮርዳኖስ መንታ ህፃናት ውጤታማ በሆነ ቀዶ ጥገና በሰላም ለያይቷቸው ነበር። ከ 12 አመት በኋላ ልጆቹ አድገው ካሉበት ዮርዳኖስ ተነስተው ምስጋና ለማቅረብ ሳኡዲ ድረስ በመምጣት ዶክተሩን ቤቱ ድረስ ሄደው በማግኘት ምስጋናቸው አቅርበዋል።
viaነጋሪት

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eng'r MohammedJewad- ኢ/ር መሃመድ ጀዋድ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share