
20/08/2025
አዲስ አበባ ነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ማሳሰቢያ!...
***
የተፈቀደው አዲሱ የደመወዝ ስኬል ይሄን ይመስላል የሚሉ ሃሰተኛ መረጃዎች በሶሻል ሚዲያ እየተለጠፉ ይገኛል።
እነዚህን የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ስኬል በሚል በአንዳንድ በማህበራዊ ሚዲያዎች አሁን ላይ የሚናፈሱ አሳሳች መረጃዎች ሀሰተኛ መሆናቸውን ኮሚሽኑ ይገልፃል።
በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አማካይነት ብቻ የሚለቀቁ መረጃዎች በመንግስትና በተቋሙ የሚተገበሩ መረጃዎች መሆኑን መገንዘብ ጥሩ ነው።
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ