Sebililah tube

Sebililah tube Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sebililah tube, Media, Dessie.

27/06/2023
የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ስብዕና             ክፍል 2  የዚህ እንግድነት ስሜት ውጤት የሆነው ለአይን የሚዘገንን ለጆሮ የሚከብድ ስቃይና መከራ ግፍና በደል ለመዝነብ አፍታም አላስፈለገው። ...
28/10/2022

የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ስብዕና

ክፍል 2
የዚህ እንግድነት ስሜት ውጤት የሆነው ለአይን የሚዘገንን ለጆሮ የሚከብድ ስቃይና መከራ ግፍና በደል ለመዝነብ አፍታም አላስፈለገው። ጥርሳቸው ን ነቅለው ባደጉበት በገዛ ቄያቸው ከሶሐባቻቸው ጋር አብረው ሁነው ላመኑበት ነገር ፍፁም ወደኋላ ሳይሉ የመከራን ፅዋ ተጎነጩ። ነገር ግን ድል ከትእግስት ጋር ደስታ ከችግር ጋር አስቸጋሪ ሁኔታም ከጥሩ ውጤት ጋር መሆኑን በመንገዘባቸው በአላህ እርዳታ በመታገዝ እልህ አስጨራሽ የሆነ ትግል ኢስላምን የበላይ አደረጉ። የታሪክ ማህደራት አይተዉት የማያውቁትን ክስተት በጥቂት አመታት ውስጥ ለዉጤት አብቅተው የኢስላም መልዕክት በመላው አለም ተሰራጨ ። የዚህ አስደናቂ ገድል ባለቤት ስለሆኑት ሰው ስብዕና በጥቂቱ ማንሳት ምናልባትም ይህንን ታሪክ ለማመን ያዳገታቸው ካሉ አጣጥመውም ባይሆን እንዲውጧት በማወራረጃነት ትጠቅም ይሆናል። በባህሪያቸው ፍፁም እዉነት ተናጋሪ ቃልኪዳንን አክባሪ ፣አመለ ሸጋ፣ ተግባቢ ፣ዕይታ ቁጥብ፣ አስተዋይ፣ ታማኝና አንደበተ-ርቱዕ ነበሩ። የተላኩበትን ግዴታ የተወጡ አዛዣቸዉን ከማንምና ከምንም በላይ የታዘዙ ዐዋቂ ፣አዛኝ፣ ትሁት ታማኝ ፣ታጋሽ ፣ብዙ ንግግር የማያበዙ መናገር ሲፈልጉ ፈገግታቸዉን የሚያስቀድሙ አጥፊዎችን በሰው ፊት የማይገስፁ ፣ከተቃዉሞ የራቁ ከሀሜት የፀዱ ሙስሊምም ይሁን ካፊር ሲታመም የሚጠይቁ ነበሩ እኚህ ታላቅ የአለማችን እንቁ ሰው ናቸው።

ይቀጥላል...

የYoutube channel subscrib በማድረግ
ይከተሉን

https://youtube.com/channel/UCNPwXat7C-QN6XJhj9kqQzg

የ telegram channel share ያድርጉ
https://t.me/Alqurankerimchannel

# quran and hadis

26/10/2022

ቁርአን የቀልብ መድሃኒት ነው።

የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ስብዕና       ክፍል 1   ወደ ጨለማው አለም ነበር የተላኩት ።ግድያና ዝርፊያ ድግምት እና መጠጥ እንደ በጎ ተግባር የሚወደስበት የሰው ልጅ ምንነቱ ተዘንግቶ እንደ እ...
25/10/2022

የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ስብዕና

ክፍል 1
ወደ ጨለማው አለም ነበር የተላኩት ።ግድያና ዝርፊያ ድግምት እና መጠጥ እንደ በጎ ተግባር የሚወደስበት የሰው ልጅ ምንነቱ ተዘንግቶ እንደ እንስሳ የሚታይበት ጣዖታት ከጭቃና ድንጋይ ተቀርፀው የሚመለኩበት ድቅድቅ ጨለማ ነበር።
በዛ ጊዜ የነበሩ የአረብ ሙሽሪኮች እንስሳዊ የሰው ልጅ ባህሪ አይሎባቸው ፍፁም በጭፍን ስጋዊ ፍላጎት ሲመሩ የማህበራዊ ኑሮ የአስተሳሰብና የሰብአዊነት ሞራላቸው ዘቅጦ ማሰቢያቸው ስራ አጥቶ ሲያዛጋ ስሜታቸው እጅጉን ቢዚ ሆኖ ለአፍታ ማረፊያ ጠፍቶት ሲባዝን የነበረበት ወቅት ነበር።
በዛ ጊዜ እና ሁኔታ ላይ ነበር የአለማት እዝነት የሆኑት ሰው ከዛው ማህበረሰብ ዉስጥ የፈለቁት። ሰዎች ሁሉ ተገርመው እንደነሱ አባባል ስለ አዲሱ ሃይማኖት ብዙ አወሩ ተነጋገሩም ።ከራሳቸው የሆነ ሰው ለዘመናት ሲከተሉት የነበሩትን የ አባቶቻቸውን አማልክት መከተል አደገኝነት ሲነገራቸው ስለ እዉነተኛው ፈጣሪ እያወሳ ሲያስጠነቅቃቸው እጅግ ተደነቁ ። ትናት መጥቶ አማልክቶቻቸዉን ወደ አንድ መቀነስ አነጋጋሪ ሆነባቸው።
ይቀጥላል...
የYoutube channel subscrib በማድረግ
ይከተሉን

https://youtube.com/channel/UCNPwXat7C-QN6XJhj9kqQzg

የ telegram channel share ያድርጉ
https://t.me/Alqurankerimchannel

# quran and hadis

10/12/2021

ፊዳከ ሩሂ አቢ ወኡሚ ያረሱለላህ

09/12/2021
02/10/2021

Address

Dessie

Telephone

+251963615656

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sebililah tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category