ወሎ ደሴ

30/11/2025

ወሎ😍

የጁ ነሽ ራያ ባቲ ነሽ ከሚሴ፤ከቴ መነን ሀገር እንገናኝ ደሴ።❤❤❤ወሎ ደሴ
29/11/2025

የጁ ነሽ ራያ ባቲ ነሽ ከሚሴ፤
ከቴ መነን ሀገር እንገናኝ ደሴ።
❤❤❤
ወሎ ደሴ

29/11/2025

ሀዋዋ😍

መገን አፈጣጠር መገን አንቺ ሆየእንዴት አድርጎ ነዉ የሰራሽ ጌታየሁሉም ሸጋ ሸጋ ከወዲያ እስከወዲህልቤን አፍዛችሁ እረፉት እንግዲህ እኔም እግሬ ሲሮጥ ከጎጃም ተነስቶከሞጣ ባህርዳር ጋሸና እና...
29/11/2025

መገን አፈጣጠር መገን አንቺ ሆየ
እንዴት አድርጎ ነዉ የሰራሽ ጌታየ
ሁሉም ሸጋ ሸጋ ከወዲያ እስከወዲህ
ልቤን አፍዛችሁ እረፉት እንግዲህ
እኔም እግሬ ሲሮጥ ከጎጃም ተነስቶ
ከሞጣ ባህርዳር ጋሸና እና እስታይሽ ሁሉን ተመልክቶ
በወልዲያ ዙሮ በ መርሳ ዉርጌሳ
በዉጫሌ እና ሀይቅ ደሴ ላይ ተመርቶ
አደንዝዞኝ ቀረ በወሎዎች ሽቶ
ይህ አልበቃዉ ብሎ በፀሎት ብመለስ ወደ ሀገሬ ሞጣ
ቶሎ ድረስ ብሎ መልክት እየመጣ
አላስችለኝ ብሎ ወሰንኩኝ ልመጣ
እናማ ቆንጅየ መገን የወሎ ልጅ
ሳላይሽ አልቀርም የፈጀዉን ቢፈጅ
ብየ ወሰንኩኝ እና በአንድ ልብ ሁኜ
በ መርጦለማርያም በአባይ በበርሃዉ
ጉዞየን ጀምሬ ገና በማለዳዉ
አንቺን ለማየት አይኔ እንዳማተረ
እንደ አሰበ አልቀረም ይኼው ተጀመረ
ከመካነ ሰላም ገና ከመድረሴ
አሁን ለምን ይሆን ከንፈሬን መላሴ 😂
ይህ አልበቃኝ ብሎ ዶባን አቋርጨ በገራዶ በኩል ገባሁኝ ከደሴ
ከደሴ ገብቸ አይኔ እያማተረ በየ መስመሩ ዳር ያቆመኝ ጀመረ
አቤት ምን አይነት ነው ደሴ ገራ ገሩ
ከእዚህ ላይ አስቀሪኝ ይፈፀም ነገሩ።
ሙሉጌታ አበበ
ወሎ ደሴ

የሸሆቹ ልጅ ናት የላይኛዉ ገታ፣እሷ ብቅ ስትል፣ጥሎኝ ኮበለለ የያዘኝ በሽታ።😍😍😍  መገን ወሎ! ወሎ ደሴ
29/11/2025

የሸሆቹ ልጅ ናት የላይኛዉ ገታ፣
እሷ ብቅ ስትል፣
ጥሎኝ ኮበለለ የያዘኝ በሽታ።
😍😍😍

መገን ወሎ!
ወሎ ደሴ

ስማቸው አርጎባ ቤታቸው ታች ቃሉ ፤እንደ ምንጭ ጅረት ፤በፍቅር ሙሃባ ሃየ በል እያሉ ይፍለቀለቃሉ ።ዛውያቸው ቃሉ ዱኣቸው ሳልመኒ ፤ጨዋታ ፍቅራቸው ፤ግመጡኝ ያሰኛል ፤እንደ ሃርቡ ባኒ ።የሸሆ...
29/11/2025

ስማቸው አርጎባ ቤታቸው ታች ቃሉ ፤
እንደ ምንጭ ጅረት ፤
በፍቅር ሙሃባ ሃየ በል እያሉ ይፍለቀለቃሉ ።
ዛውያቸው ቃሉ ዱኣቸው ሳልመኒ ፤
ጨዋታ ፍቅራቸው ፤
ግመጡኝ ያሰኛል ፤እንደ ሃርቡ ባኒ ።
የሸሆቹ ልጅ ናት የላይኛው ገታ ፤
እሷ ብቅ ስትል ፤
ጥሎኝ ኮበለለ የያዘኝ በሽታ ።
እሱ ጃውሳ ነው እሷ ባለጉፍታ ፤
አስገባቸው አሉ ፤
ቃሉና ከሚሴ ከዱበርቴው ገብታ ።
ከነ ጦልሃ ሃገር ቃሉ ተወልደሽ ፤
አጃኢብ ያሰኛል ፤
መገን አቀራርሽ አከታተምሽ ።
የአርጎባ ነጋዴ ይሄዳል በግመል ፤
በዱኣ ታልሆነ ፤
እንዴት ይዘልቁታል ፤ የሂስደኛን ቁጣ ፤የጃሂልን አመል ።
በሃርቡ ገበያ ፤
ታቹን ከሜዳው ላይ ከመዳላድሉ ፤
እኒህ አርጎባዎች ፤
በአይናማው ጥርሳቸው ፤ አያል ሰው ገደሉ ።
የነቢን አደራ ፤
የሂጅራን ሃቂቅ ፤ እኔ መች አውቄ ፤
ኪታቡን አገኘሁ ፤
ሃርቡ መቃኛው ላይ ፤ አርጎባ ዘልቄ።
ጃውሶች በደቦ ፤
ጢነኛ ወዳጃ ተቃቅፈው ሲዉሉ ፤
በዱበርቴው ጀማ ፤
እርፎ ሲባልለት ከጨፋ እስከ ቃሉ ፤
ለካስ ያ ሰውየሽ ፤
ካልጋ የወደቀው በአንቺ አሮ ነው አሉ ።
አርጎባ ሲነካ ደሴ አረገረገ ፤
የሃቁን ነው እንጅ ታዲያ ምን አረገ !?
ጃኖ መንግስቱ ዘገየ
ወሎ ደሴ

ከአምባሰል ሰንሰለታማ ተራሮች ግርጌ የሚገኘው  የጎልቦ ሐይቅ በደቡብ ወሎ ዞን ከሚገኙ 4ቱ ሃይቆች/  #የሎጎ ሃይቅ፣  #አርዲቦና  #ማይባር ሐይቅ ወስጥ አንዱ ሲሆን ለአምባሰል ወረዳ ብቸኛ...
29/11/2025

ከአምባሰል ሰንሰለታማ ተራሮች ግርጌ የሚገኘው

የጎልቦ ሐይቅ በደቡብ ወሎ ዞን ከሚገኙ 4ቱ ሃይቆች/ #የሎጎ ሃይቅ፣ #አርዲቦና #ማይባር ሐይቅ ወስጥ አንዱ ሲሆን ለአምባሰል ወረዳ ብቸኛው የተፈጥሮ ሐይቅ ነው።

ሐይቁ ከደሴ በስተሰሜን አቅጣጫ በ53 ኪሎ ሜትር ርቀትና ከአምባሰል ወረዳ ርዕሰ ከተማ ውጫሌ በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ነው። በተጨማሪም ከደሴ ወልዲያ የአስፓልት መንገድ ወደ ግራ ገባ ብሎ በወረዳው 04 ቀበሌ ጎልቦ ይገኛል።

የጎልቦ ሐይቅ ስፋቱ 7 ነጥብ 5 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ሲሆን ከዋናው መንገድ ገባ ብሎ የሚገኝ ከመሆኑም በተጨማሪ ከይስማ ንጉስ የቱሪዝም ማዕከል አቅራቢያ በመሆኑ ለቱሪስቶች ምቹ እና የመስህብ ሐብት እንዲሆን አድርጎታል።
@ የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ
ወሎ ደሴ

 #ከደቡብ ወሎ ፀጋዎች አንዱ የሆነው  አርዲቦ ሐይቅ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ከሚገኙ 4 ሐይቆች መካከል አንዱ ነው፡፡ ከሐይቅ ከተማ 17 ኪ.ሜ ላይ የሚገኘው አርዲቦ ሐይቅ የተሁለደሬ...
29/11/2025

#ከደቡብ ወሎ ፀጋዎች አንዱ የሆነው
አርዲቦ ሐይቅ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ከሚገኙ 4 ሐይቆች መካከል አንዱ ነው፡፡ ከሐይቅ ከተማ 17 ኪ.ሜ ላይ የሚገኘው አርዲቦ ሐይቅ የተሁለደሬ እና ቃሉ ወረዳዎች ያዋስኑታል፡፡ ከደሴ ከተማ በስተሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል። የሐይቁ አማካኝ ጥልቀት 65 ሜትር ሰፋቱ 21 ስኩየር ኪሎ ሜትር ሲሆን ከመሬት ወለል በላይ 1 ሸህ 890 ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡
አርዲቦ ለቱሪዝም ልማት፣ ለአሳ እርባታ እና ለመስኖ ልማት ፍፁም የተመቸ ሐይቅ ነው፡፡
@ የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ
ወሎ ደሴ

ደሴ ❤ ሰኞ ገበያ መስጅድ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በአንድ መንደር የሚገኙ የእስልምና እና ክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች የእምነት ቦታዎች ናቸው። ሰኞ ገበያ መስጅድ ታላላቅ አሊሞችን...
28/11/2025

ደሴ ❤ ሰኞ ገበያ መስጅድ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

በአንድ መንደር የሚገኙ የእስልምና እና ክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች የእምነት ቦታዎች ናቸው። ሰኞ ገበያ መስጅድ ታላላቅ አሊሞችን በማፍራት ይታወቃል። የደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከ100 ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረ ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን በአሁን ሰዓት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በመሆንም አገልግሎት ይሰጣል።
@ Tesfa Vlogs
ወሎ ደሴ

28/11/2025

የአባተ ሀይሉ አገር
ታች የጁ እንደት ነው
❤❤❤
ወሎ ደሴ

28/11/2025

😍😍😍

በተንታ ወረዳ የሚገኘው ታሪካዊው መቅደላ አምባና አካባቢው😍@ ተንታ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽንወሎ ደሴ
28/11/2025

በተንታ ወረዳ የሚገኘው ታሪካዊው መቅደላ አምባና አካባቢው😍
@ ተንታ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን
ወሎ ደሴ

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወሎ ደሴ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share