ደሴ ሚዲያ ኔትወርክ -Dessie Media Network

  • Home
  • ደሴ ሚዲያ ኔትወርክ -Dessie Media Network

ደሴ ሚዲያ ኔትወርክ -Dessie Media Network የፍቅርና የመተሳሰብ ከተማ ደሴ

የምትመለከቷት ወፍ  Fire Hawks ትባላለች። አደገኛ ወፍ ናት። እንደአካሏ ማነስ እንዳትመስላችሁ። በሚሊየን ዶላር የሚገመት ንብረት በዚች ሚጢጢ ፍጥረት በየአመቱ ይወድማል። ስራዋ ማጥፋት...
27/06/2025

የምትመለከቷት ወፍ Fire Hawks ትባላለች። አደገኛ ወፍ ናት። እንደአካሏ ማነስ እንዳትመስላችሁ። በሚሊየን ዶላር የሚገመት ንብረት በዚች ሚጢጢ ፍጥረት በየአመቱ ይወድማል። ስራዋ ማጥፋት ነው። ከየትም ፈልጋ የተቀጣጠለ እንጨት ሰወች ሳያጠፉ የጣሉት ሲጋራ ታነሳና ደረቅ ጫካ ፈልጋ ትጥለዋለች ....እሳት ይነሳል። አንዳንዴ መንደር ወይም ለዘመናት የተጠበቀ ደን ይወድማል፣ ብርቅየ እንስሳት ይሞታሉ ይሰደዳሉ። ይሄን ሁሉ የምታደርገው ለምን ይመስላችኋል? ለሆዷ! ጫካው ውስጥ የተደበቁ በረሮወችና ትናንሽ ነፍሳት እሳቱን ፈርተው ሲውጡ እየለቀመች ትበላለች በቃ! ለዚሁ ነው አገር የምታወድመው!!

(አሌክስ አብርሀም)

 #ሰበር ዜና ኢራን🇮🇷እስራኤል ለኮሰችው፤ አሜሪካ አቀጣጠለችውበቃ አለም ገላጋይ አጥቶ ወደ ከፋዉ እየተሸጋገረ ነዉ ።ኢራን በኳታርና ኢራቅ በሚገኙት የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ማጥቃቷ  ተገለፀ ።...
23/06/2025

#ሰበር ዜና ኢራን🇮🇷

እስራኤል ለኮሰችው፤ አሜሪካ አቀጣጠለችው

በቃ አለም ገላጋይ አጥቶ ወደ ከፋዉ እየተሸጋገረ ነዉ ።

ኢራን በኳታርና ኢራቅ በሚገኙት የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ማጥቃቷ ተገለፀ ።
የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ በፌስቡክ ገፁ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ ከደቂቃዎች በፊት በኳታር የሚገኘውን የአሜሪካ የጦር ሰፈር ስድስት ባላስቲክ ሚሳኤሎች በማስወንጨፍ መደብደቡን ገልጿል ።

ይህም ዋሽንግተን በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ላደረሰችብኝ ጥፋት ምላሽ ነዉ ጀምርን እንጂ ገና አልጨረስንም ያለ ሲሆን ኢራቅ ባህሬን ኩዌት የሚገኙ ቀጣይ ኢላማወቹ መሆናቸው ከመግለፅ ዉጭ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

ጦርነቱ አድማሱን እያሰፋ ሀገራችን በጎራ አለያይቶ አለምን ወደከፋዉ እንዳይወስዳትም ተሰግቷል ።

የውሃ አገልግሎት መቋረጥን ስለማሳወቅ፡- ===============                                የተከበራችሁ ደንበኞቻችን ከ እሮቢት ድልድይ እስከ ወሎ ባህል አምባ ድረስ ...
23/06/2025

የውሃ አገልግሎት መቋረጥን ስለማሳወቅ፡- =============== የተከበራችሁ ደንበኞቻችን ከ እሮቢት ድልድይ እስከ ወሎ ባህል አምባ ድረስ በሚሰራው የመንገድ እና ኮሊደር ልማት ምክንያት ከፍተኛ የውሃ መስመር በአዲስ የመቀየር ስራ ከነገ ሰኔ 17/2017 ጀምሮ ይከናወናል ። በዚህም ምክንያት ካራጉቱ የውሃ ማጠራቀሚያ ጋን ላይ ውሃ ስለማይገባ ከካራጉቱ ውሃ የምታገኙ ደንበኞች ማለትም አሬራ፣ ዳወይሜዳ፣እሮቢት ገበያ ፣ስላሴበር፣ ቧንቧውሃ፣መገናኛ ፣ተስፋ ድርጅት ፣ መናፈሻ እና አካባቢ ነዋሪዎች ውሃ አገልግሎት የሚቋረጥ መሆኑን እያሳወቅን ስራው ተጠናቅቆ አገልግሎት እስከሚጀምር ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን። =================== የደሴ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት።

በኢራን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ*********************በኢራን ሴምናን ከተማ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 5.2 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተገልጿል።የኢራኑ ታስኒም የ...
21/06/2025

በኢራን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
*********************

በኢራን ሴምናን ከተማ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 5.2 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተገልጿል።

የኢራኑ ታስኒም የዜና ወኪል የመሬት መንቀጥቀጡን መጠን 5.2 እንደሆነ ሲያሳውቅ፤ የአሜሪካ የጂኦሎጂ ጥናት ማዕከል (USGS) በበኩሉ ክስተቱ 5.1 በሬክተር ስኬል መመዝገቡን አስታውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከሴምናን ከተማ በስተደቡብ ምዕራብ 37 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተ ሲሆን፤ 10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት እንዳለው ታውቋል።

የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሰውና በንብረት ላይ ስላደረሰው ጉዳት እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

ኢራን በጂኦሎጂያዊ እንቅስቃሴ በሚታወቀው የአልፓይን-ሂማሊያን ላይ የምትገኝ በመሆኗ በዓለም ላይ ለመሬት መንቀጥቀጥ በጣም ከተጋለጡ ሀገራት አንዷ ነች።

እንደኢኮኖሚክ ታይምስ ዘገባ ኢራን በዓመት በአማካይ 2ሺ 100 የመሬት መንቀጥቀጦችን የምታስተናግድ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ከ15 እስከ 16 የሚሆኑት ከባድ የሚባሉ ናቸው።

የሠራተኞች መነሻ የደመወዝ ወለል ከ8 ሺህ ብር በላይ እንዲሆን ተጠየቀወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ8 ሺህ 384 ብር የሆነ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን...
19/06/2025

የሠራተኞች መነሻ የደመወዝ ወለል ከ8 ሺህ ብር በላይ እንዲሆን ተጠየቀ

ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ8 ሺህ 384 ብር የሆነ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ለመንግሥት ጥያቄ
ማቅረቡን ገለጸ።

የገንዘብ ሚኒስቴር ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በሥራ ላይ ቆይቷል የተባለውንየገቢ ግብር አዋጅ 979/2008ን ለማሻሻል ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ከተባሉ ባለድርሻዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።

በዚህ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እስከ ሁለት ሺሕ ብር የሚከፈላቸው ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ተደንግጓል።

የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንዳሉት እስከ 8 ሺህ 384 ብር ድረስ የሚከፈላቸው ተቀጣሪዎች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ለገንዘብ ሚኒስቴር በደብዳቤ ጠይቀናል ብለዋል።

መንግስት በሰረተኞች ገቢ ግብር ዙሪያ ያዘጋጀው ማሻሻያ ውይይት እየተደረገበት ሲሆን በቅርቡ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የላከው መልዕክት ****************************ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እየተባባሰ የመጣውን የእስራኤል እና ኢራንን ጦርነት...
17/06/2025

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የላከው መልዕክት
****************************

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እየተባባሰ የመጣውን የእስራኤል እና ኢራንን ጦርነት አስመልክቶ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የ5 ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሀገራቱ መካከል ያለው ውጥረት እንዲረግብ ሰላም ለዓለም የሚል መልዕክት ማስተላለፉ ይፋ ሆኗል፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ጨዋታ ለሰላም” የሚል ያልተጠበቀ ስጦታ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ እንደተላከላቸውም አሳውቀዋል፡፡

ሮናልዶ የፈረመበትን የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን መለያ ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አንቶኒዮ ኮስታ እጅ የተረከቡት የሪፐብሊካኑ ተወካይ በአሁኑ ሰዓት ለቡድን ሰባት ስብሰባ ካናዳ ይገኛሉ፡፡

እስራኤል ጥቃት ፈፀመች ! የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በቴህራን የሚገኘውን የኢራን መንግስት ብሮድካስት (IRIB) ዋና መሥሪያ ቤትን ማዉደሙ ተነገረ ።የእስራኤል አየር ሀይል የጦር አውሮፕ...
16/06/2025

እስራኤል ጥቃት ፈፀመች !

የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በቴህራን የሚገኘውን የኢራን መንግስት ብሮድካስት (IRIB) ዋና መሥሪያ ቤትን ማዉደሙ ተነገረ ።

የእስራኤል አየር ሀይል የጦር አውሮፕላኖች ጥቃቱን ያደረሱት በአካባቢው የሚገኙ የኢራን ነዋሪዎች አካባቢዉን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ካስተላለፉ ከሰዓታት በኋላ ነው።

የእስራኤል መከላከያ ኃይል የኢራንን የአየር ክልል መቆጣጠሩ በኢራን ውስጥ ጥቃት ለመሰንዘር ከፍተኛ እገዛ አድርጎለታል የተባለ ሲሆን የኢራን መንግሥት ብሮድካስቲንግ ዜና አቅራቢ የሆነው ፔይማን ጃቤሊ በደም የተጨማለቀ የዜና ስክሪፕት ይዞ ታይቷል።

በተያያዘ ዜና የኢራን መንግሥት በማህበራዊ ትስስር ገፁ የእስራኤል ዜጎች ቴላቪቭን ለቀው እንዲጡ ጥሪ አስተላልፏል ።

15/06/2025

🆕

ካለፈው ከአርብ ጀምሮ ለሦስተኛ ቀን የቀጠለው የእስራኤል እና የኢራን ጦርነት እየተባባሰ ነው።

ዛሬ በሁለቱም ወገኖች ጥቃቶች እየተፈጸሙ ናቸው።

በእስራኤል የተፈጸሙ ጥቃቶች ፦

- እስራኤል በኢራን ውስጥ የሚገኙ ዒላማዎችን መምታቷን ቀጥላለች፤ የእስራኤል የመከላከያ ኃይል እንዳለው በዛሬው ዕለት 250 ዒላማዎችን መትቷል።

- የኢራን የመገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት አስከ ቅዳሜ ዕኩለ ቀን ድረስ 128 ሰዎች ሲገደሉ 900 የሚደርሱት ደግሞ ተጎድተዋል። ከሟቾች መካከል በርካታ ህጻናት ይገኙበታል።

በኢራን የተፈጸሙ ጥቃቶች ፦

° ኢራን ሌሊት ላይ በእስራኤል ላይ የሚሳዔል ጥቃቶችን የፈጸመች ሲሆን፣ በዚህም 6 ሰዎች ከቴል አቪቭ በስተደቡብ በምትገኘው ባት ያም በምትባል ቦታ እንዲሁም 4ቱ በሰሜናዊቷ ታምራ ከተማ አጠቃላይ 10 ሰዎች ተገድለዋል። ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የእስራኤል ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

° ዛሬ እሁድ ከሰዓት በኋላ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሚሳዔሎችን ወደ እስራኤል በማስወንጨፍ ጥቃት ሰንዝራለች። የእስራኤል ጦር ሠራዊት እንዳለው አብዛኞቹ ሚሳዔሎች የከሸፉ ሲሆን፣ ጉዳት ስለመድረሱ የወጣ ዘገባ የለም።

በሌላ በኩል ፤ እስራኤል እየወሰድች ባለው ጥቃት በኢራን በዋና ከተማ ቴህራን የሚገኘው የሳህራን ነዳጅ ማከማቻ መመታቱን የኢራን ነዳጅ ሚኒስቴር ገልጿል። የነዳጅ ማቀነባበሪያው በጥቃቱ የእሳት አደጋ ቢደርስበትም አሁን በስራ ላይ መሆኑ ተሰምቷል።

መረጃው ከቢቢሲ ሲሆን ቪድዮው ከማህበራዊ ሚዲያዎች የተገኘ ነው።

ቪድዮ፦ ሀይፋ ዛሬ ምሽት (እስራኤል)

እስራኤል ሌላ ዙር ጥቃት ፈፀመች ! ቴላቪቭ   በርካታ ፍንዳታዎችን እና ውድመትን ያስከተለው ጥቃት በኢራን ላይ መፈፀሟ ተነገረ ።በቴህራን የኢራን መንግስት ቲቪ እንደዘገበው ከሆነ ዛሬ አመሻ...
14/06/2025

እስራኤል ሌላ ዙር ጥቃት ፈፀመች !

ቴላቪቭ በርካታ ፍንዳታዎችን እና ውድመትን ያስከተለው ጥቃት በኢራን ላይ መፈፀሟ ተነገረ ።

በቴህራን የኢራን መንግስት ቲቪ እንደዘገበው ከሆነ ዛሬ አመሻሹ ላይ እስራኤል ከ150 በላይ ቦታዎች ላይ ጥቃት መፈፀሟን እና በተፈፀመው ጥቃትም በኢራን ደቡባዊ ቡሻህር ግዛት ውስጥ ከጋዝ ማውጫ ጨምሮ በርካታ ቦታዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የገለፀ ሲሆን
በጥቂቱም 20 ህጻናትን ጨምሮ ወደ 60 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን እና በመላ ሀገሪቱ ተጨማሪ ጥቃቶች መፈፀሙን ዘግቧል ። ተብሏል

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ ያለው እና በሲኤንኤን የተወሰደው የቪዲዮ ምስል በኢራን ደቡባዊ ቡሻህር ግዛት ውስጥ ከጋዝ ማውጫው የተነሳ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ እና ጭስ የሚያሳይ ሲሆን ጥቃቱ ከእስካሁኑ የከፋ መሆኑን የዘገበው ሮይተርስ ነዉ
yeneta

12/06/2025

#ሙሉጌታከበደ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን  ተጫዋች ሙሉጌታ ከበደ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።  ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለረጅም ዓመታት በስኬት የዘለቀው ሙሉጌታ ከበደ ባጋ...
11/06/2025

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሙሉጌታ ከበደ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለረጅም ዓመታት በስኬት የዘለቀው ሙሉጌታ ከበደ ባጋጠመው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ሕይወቱ ማለፉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አሳውቋል፡፡
ለመላው ቤተሰቡ መፅናናትን እንመኛለን።

ፖርቹጋል ሻምፒዮን 🏆 ሆነች !የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን የስፔን አቻውን በመለያ ምት 5ለ3 በማሸነፍ የኔሽንስ ሊግ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።በመደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታቸ...
09/06/2025

ፖርቹጋል ሻምፒዮን 🏆 ሆነች !

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን የስፔን አቻውን በመለያ ምት 5ለ3 በማሸነፍ የኔሽንስ ሊግ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።

በመደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታቸውን 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የስፔንን ግብ ዙቢሜንዲ እና አኦያርዛባል ሲያስቆጥሩ ለፖርቹጋል ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሜንዴዝ ከመረብ አሳርፈዋል።

ፖርቹጋል ሁለተኛ የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ዋንጫዋን ማሸነፍ ችላለች።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን 138ኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን የኔሽንስ ሊግ ዋንጫን ሁለት ጊዜ ያሳካ የመጀመሪያ ብሔራዊ ቡድን ሆኗል።

ፖርቹጋል ስፔንን በ 21ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፋታለች።

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደሴ ሚዲያ ኔትወርክ -Dessie Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ደሴ ሚዲያ ኔትወርክ -Dessie Media Network:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share