Current Waghimra news የዋግ አሁናዊ ዜና

  • Home
  • Current Waghimra news የዋግ አሁናዊ ዜና

Current Waghimra news        የዋግ አሁናዊ ዜና ሸጋ እናብስራለን!

28/06/2025

ሰኔ ማርያም!

ስትጠነክር እንዲህ ነው።ስጠነከር ሁሉንም  ታቸንፍለክ። አንተ ለጠንካሮች ምሳሌ መሆን ችሃል።እንኳን ደስ አለህ!!!ESHETE W
23/06/2025

ስትጠነክር እንዲህ ነው።
ስጠነከር ሁሉንም ታቸንፍለክ።
አንተ ለጠንካሮች ምሳሌ መሆን ችሃል።
እንኳን ደስ አለህ!!!

ESHETE W

የመንግስትን ስም የሚያጠለሹ ጽሑፎችና መልዕክቶች ያሰራጨው ግለሰብ በ7 ዓመት እስራት ተቀጣበማህበራዊ ሚዲያ የመንግስትን ስም የሚያጠለሹ እና ራሱን የአማራ ፋኖ ብሎ የሚጠራውን ጽንፈኛ ቡድን ...
19/06/2025

የመንግስትን ስም የሚያጠለሹ ጽሑፎችና መልዕክቶች ያሰራጨው ግለሰብ በ7 ዓመት እስራት ተቀጣ

በማህበራዊ ሚዲያ የመንግስትን ስም የሚያጠለሹ እና ራሱን የአማራ ፋኖ ብሎ የሚጠራውን ጽንፈኛ ቡድን የሚደግፉ ጽሑፎች እና መልዕክቶች በማሰራጨት የሽብር ተልዕኮ ሲፈፅም የነበረ ግለሰብ በሰባት ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።

የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሽ ወንድማገኝ በርገና በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ሀ፣ ለ እና ሐ ድንጋጌ በመተላለፍ የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን የዐቃቤ ሕግ ክስ ያመላክታል።

ተከሳሹ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በሀሳቡ፣ በወንጀል ድርጊት እና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን መንግስትን በጦርነት ከስልጣን ለማስወገድ አስቦ በህገወጥ መንገድ የጦር መሳሪያ በመታጠቅ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ጦርነት ውስጥ በመግባት እየተዋጋ ያለውና ራሱን ፋኖ ብሎ የሚጠራ የጽንፈኛ ቡድን የፕሮፖጋንዳ ክንፍ በመሆን "በርገና ወንድማገኝ" የሚል የዋትስአፕ አካውንት ከፍቶ ነበር፡፡

የቡድኑ ልሳን ለሆኑ በዋናነትም ዘመድኩን በቀለ ለተባለ ግለሰብ በየካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ለቡድኑ የፕሮፖጋንዳ ሥራ ግብዓት የሚሆኑ በአርባ ምንጭ ከተማ መንግስት ቤት እያፈረሰ ነው የሚል መልዕክት እንዲሁም በየካቲት 24 ቀን 2016 ዓ.ም የመንግስትን ሥርዓት ለመገርሰስ ብቸኛው አማራጭ የትጥቅ ትግል ነው የሚል መልዕክት ማስተላለፉ በዐቃቤ ህግ ክስ ላይ ተገልጿል፡፡

‘እኔም አንዱ የዛ አካል ነኝ፤ ፋኖን እደግፋለሁ ሁሉም ሰው የድርሻውን ሊወጣ ይገባል’ የሚል እና ‘ሥርዓቱን በተለያዩ አማራጮች ማዳከም አለብን' የሚል መልዕክት በቪዲዮ ቀርጾ ለዘመድኩን በቀለ እንደላከ ተገልጿል።

ወንድማገኝ ገብሬ በሚል ስም በተከፈተ የቲክቶክ አካውንት ላይ የተገለጹትን የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶች በቪዲዮ አሰራጭቶ ከ10 ያላነሱ ሰዎች የተመለከቱት የመንግስትን ስም የሚያጠለሹ ተግባራትን ሲፈጽም ነበር።

እንዲሁም ራሱን የአማራ ፋኖ ብሎ የሚጠራውን ጽንፈኛ ቡድን አመራሮች ፎቶ በመለጠፍ እንዲሁም ማንነታቸው ያልታወቁ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ግለሰቦችን ፎቶ በመለጠፍ ጦርነትን የሚያባብሱ የተለያዩ መልዕክቶችን በማሰራጨት እንዲሁም ወጣቱን ለጦርነት የሚያነሳሱ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት እንዲሰራጩ በማድረግ ወንጀል ተከሷል፡፡

ግለሰቡ የፕሮፖጋንዳ ስራ በመስራት በመንግስት ላይ ጥርጣሬ እንዲፈጠርና የጠላት አላማ እንዲሳካ የተለያዩ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶች በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲያሰራጭ የነበረ ሲሆን÷ ኢትዮጵያ ጦርነት ላይ እያለች የጠላት ዓላማን ለማሳካት በማሰብ የጠላትን ጥቅም በሚያራምድ የፕሮፖጋንዳ ስራ ውስጥ በመሳተፍ ጠላትን የደገፈ በመሆኑ በፈጸመው ጠላትን መተባበር ወንጀል ተከሷል፡፡

ተከሳሹ በአጠቃላይ አመጽ ቀስቃሽ የሆኑ በርካታ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችና ቪዲዮዎች ሲያጋራ እና ሲያነሳሳ እንደነበር የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ ክዶ በመከራከሩ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቧል።

በዚህም መሰረት ተከሳሹ የቀረበበትን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብር ወንጀል ችሎት ተከሳሹ በ7 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ምንጬ፦ፍና ሚዲያ ነው

"ተስፍ ለመምህራን"=============የደሞዝ ጥያቄ ህጋዊ ነው አጣጥመን ለመሔድ እንሞክራለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመላው ኢት...
15/06/2025

"ተስፍ ለመምህራን"
=============
የደሞዝ ጥያቄ ህጋዊ ነው አጣጥመን ለመሔድ እንሞክራለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ መምህራን ጋር በተወያዩበት ወቅት የደሞዝ ጥያቄ ህጋዊ ነው አጣጥመን ለመሔድ እንሞክራለን ብለዋል፡፡

ለመምህራን ትልቅ ክብር እንዳላቸው የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እኔ በህይወት እያለሁ መኪናቸውን ነድተው ሃይስኩል በር ላይ አቁመው ሲያስተምሩ ከማየት በላይ ደስታ የለኝም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሰዎች በፖለቲካው መንደር፣ በፌስ ቡክ እንዲሁም በፓርላማ ነገሮችን አዛብተው ቢያመጡ የሚጠበቅ ነው፤ መምህራን ጋር ግን ነገር ከተበላሸ የሀገር ጉዳት ነው ብለዋል።

በመሆኑም የመምህራን ሐሳብ የፖሊሲ ግብዓት ጭምር በመሆኑ እያንዳንዱ የሚነሡ ጉዳዮችን በጥንቃቄ እንደሚያዩት ተናግረዋል።

አሁን የሚደረገው ውይይትም የይስሙላ ሳይሆን ከልብ የመነጨ እና ጥቅም የሚገኝበት ይሆናል ብለው እንደሚያምኑም ነው የገለጹት።
ደመወዝ ቢጨመር ቤት ቢኖር የሰው ልጅ ፍላጎት ገደብ የለውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ነገር ግን ለማደግና ለመሻሻል መጓጓት ተገቢ ስለሆነ ሁለቱን አጣጥሞ መሄድ እንደሚገባ ገልጸዋል።

መልካም እለተ ሰንበት!የገንዘብም፣ የፍቅርም፣ የፅድቅ ስራ የሚሰራበት የበረከት ቀን ይሆን ዘንድ የፈጣሪ ፍቃድ ይሁን።
15/06/2025

መልካም እለተ ሰንበት!

የገንዘብም፣ የፍቅርም፣ የፅድቅ ስራ የሚሰራበት የበረከት ቀን ይሆን ዘንድ የፈጣሪ ፍቃድ ይሁን።

በህንዱ አውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ያጡት አሳዛኙ የአንድ ቤተሰብ ታሪክ::ዶ/ር ኮሚ እና ባለቤታቸው ዶ/ር ፕራቲክ ከሶስት ልጆቻቸው፣ ናኩል፣ ፕራዲያት እና ጆቪሽ ጋር በአንድ ላይ በአውሮፕ...
13/06/2025

በህንዱ አውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ያጡት አሳዛኙ የአንድ ቤተሰብ ታሪክ::

ዶ/ር ኮሚ እና ባለቤታቸው ዶ/ር ፕራቲክ ከሶስት ልጆቻቸው፣ ናኩል፣ ፕራዲያት እና ጆቪሽ ጋር በአንድ ላይ በአውሮፕላን ሲጓዙ በደረሰ አደጋ አምስቱም የቤተሰብ አባላት ሕይወታቸውን አጥተዋል።

ዶ/ር ኮሚ ከምሰራበት ሆስፒታል በተሻለ ሥራ ወደ ለንደን፣ እንግሊዝ አዲስ ህይወት ለመጀመር ከቤተሰቧ ጋር በጉጉት ስትጏዝ ነበር።

ነገር ግን "ነገ የተሻለ ሕይወት ይኖረኛል፣ ነገ ከቤተሰቤ ጋር ደህና ኑሮ እኖራለሁ" ብለው ሲያስቡ፣ ያልጠበቁት አደጋ የሁሉንም ሕይወት ቀጥፎ ሳይመለሱ ቀርተዋል።

ይህ አሳዛኝ ክስተት የመጨረሻ ፎቶግራፋቸውን
እንደ ትዝታ ትቶ አልፏል።

💔

🌴🌴🌴

ዜና እረፍት።።።።።።።።።።።።።።።።።የአበርገሌ ወረዳ  ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የነበሩት የተከበሩ አቶ ሃበን ገበረሂወት ባጋጠማቸው  ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ።የተከበሩ ...
12/06/2025

ዜና እረፍት
።።።።።።።።።።።።።።።።።
የአበርገሌ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የነበሩት የተከበሩ አቶ ሃበን ገበረሂወት ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ።

የተከበሩ አቶ ሃበን ገበረሂወት ከአባቱ ገበረሂወት በደለና ከእናቱ ወ/ሮ ማንጠግቦሽ በለጠ በ1974 ዓ/ም ተወለዱ እድሜያቸው ለትም/ት በደረሰ ጊዜ ከ1-6 በፃና ትም/ት ቤት ፣ 7-8 ማርነት ትም/ት ቤት 9-10 በሰቆጣ ዋግ ሹም ፣ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትም/ት ቤት ዲፕሎማን በደሴ መምህራን ኮሌጅ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል ።

የተከበሩ አቶ ሃበን ገበረሂወት በ1997 ዓ/ም ጀምረው በመምህርነት ፣ በርዕሰ መምህርነት ፣ በአበርገሌ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት ባለሞያ ፣ የስቪል ሰርቪስ ባለሞያ ፣ ከ2011 ዓ/ም እስከ 2014 ዓ/ም የአበርገሌ ወረዳ ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ከ2014 ዓ/ም ጀምረው የአበርገሌ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ በመሆን ለ20 ዓመታት ለህዝባቸው በቅንነትና በታታሪነት አገልግለዋል ።

የተከበሩ አቶ ሃበን ገበረሂወት ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስም የአበርገሌ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

የተከበሩ አቶ ሃበን ገበረሂወት ባለትዳርና የ3 ወንድ ልጆች አባት ነበሩ ።
የአበርገሌ ወረዳ ተቀዳሚ አሰተዳዳሪ አቶ ነይኑ በላይ ለተከበሩ አቶ ሃበን ገበረሂወት ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን በመግለጽ ፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለሥራ
ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል ፡፡

መረጃው፦ የአበርገሌ ወረዳ ኮምንኬሽን ነው

11/06/2025

ለአዳዲሶቹ ዋና አድናቂዎቼ ታላቅ ምስጋና! ደሳለኝ በለይ, aron abate አመሰግናለሁ

ፍትህ ለብሄራዊ ጀግናችን!ፍትህ ለገለቴ ቡርቃ!ፍትህ ለሴት አትሌቶች!
10/06/2025

ፍትህ ለብሄራዊ ጀግናችን!
ፍትህ ለገለቴ ቡርቃ!
ፍትህ ለሴት አትሌቶች!

ኢትዮጵያ መድን  በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ሻምፒዮን ሆነ***************************ኢትዮጵያ  መድን እግር ኳስ ክለብ የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡
09/06/2025

ኢትዮጵያ መድን በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ሻምፒዮን ሆነ
***************************
ኢትዮጵያ መድን እግር ኳስ ክለብ የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡

ፍትህ  በባለቤቷ እየተበደለች ላለችው እና ለብሄራዊ ጀግናችን  ገለቴ ቡርቃ!
09/06/2025

ፍትህ በባለቤቷ እየተበደለች ላለችው እና ለብሄራዊ ጀግናችን ገለቴ ቡርቃ!

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Current Waghimra news የዋግ አሁናዊ ዜና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share