
04/09/2025
ስለ ወሎ ያልተነገሩ እውነቶች
" በአማራ ክልል አካባቢወች ውስጥ የኤሌክትሪክና ስልክ አገልግሎትን ቀድሞ በማግኘት ወሎ ቀዳሚው ነው። ደሴ ከተማ ከክልሉ ከተሞች ውስጥ ስልክ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት በማግኘት ቀዳሚዋ ነች።
ባቲ፣ ትዝታ፣ አንቺ ሆዬ እና አምባሰል የሚባሉት አራቱ የኢትዮጲያ የሙዚቃ ቅኝቶች መሰረታቸው ወሎ ነው (ሌሎች ኢትዮጲያውያን ወገኖቻችን ደስ እንዲሰኙባቸው ምክንያት መሆናችን ደስ አሰኝቶናል)።
"በአማራ ክልል ውስጥ ቀዳሚው ዘመናዊ ትምህርት ቤት የተጀመረው ወሎ ደሴ ላይ ነው።
" በኢትዮጲያ እስልምና ታሪክ ውስጥ ስማቸው ገናና ሆኖ የሚታወቁት እነደ ዳና፣ ጥሩ ሲና፣ ሾንኬ፣ ጫሊ፣ ገታ፣ ደገር ወዘተ አይነት መድረሳወች የሚገኙት ወሎ ውስጥ ነው።
"ኢትዮጲያዊ የሆነው መንዙማ የተጀመረው በወሎ ነው
"በአማራ ክልል ከሚገኙ ጥንታዊ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ እጅግ ጥንታዊ የሆነችው እና ቀደምቷ ተድባበ ማርያም የምትገኘው በወሎ ነው።
" አማራ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ከ1000 ዓመት በላይ እድሜ ካስቆጠሩ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ በግርድፉ ከ70% በላይ የሚሆኑት የሚገኙት በወሎ ውስጥ ነው።
"የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ አማኞች በታላቅ ክብር ከተለያየ የኢትዮጲያ ክፍልና ከአለም ተሰባስበው ለሃይማኖታዊ የሚታደሙባቸው ግሸን ደብረ ከርቤ እና ቅዱስ ላሊበላ የሚገኙት በወሎ ነው።
"ኢትዮጲያን ለዘመናት የገዟት የዛጉዌ፣ የሰሎሞናዊ፣ የወረሴህ እና የማመዶች ሥርወ መንግስታት የተመሰረቱት በወሎ ነው። መራ ተክለ ሃይማኖት፣ ዓጤ ይኩኖ አምላክ ፣ አባ ሴሩ ጓንጉል፣ አባ ጂቦ መሀመድ አሊ የተሰኙት የእነዚህ ሥርወ መንግስታት መስራቾች ከዚሁ ከወሎ ምድር የተፈጠሩ ናቸው።
" የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የአገው እና የአርጎባ ህዝቦች በወሎ ውስጥ ይገኛሉ ።
" በዘመናዊ የኢትዮጲያ ታሪክ ውስጥ የወሎየወች ከፍታ የሚባለው አቤቶ እያሱ ስልጣን ሲወርሱ አባታቸው ሚካኤል ዓሊ ንጉሠ ጽዮን ተብለው የወሎ፣ የጎንደር ፣ የትግሬና የጎጃም የበላይ ገዥ ሲባሉ ነው።
" ከአማራ ክልል አካባቢወች ግንባር ቀደም በመሆን የአክስዮን ማህበር ያቋቋሙት ወሎየወች ናቸው። የወሎ ፈረስ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበርን በእነ ፊታውራሪ አመዴ ለማ አማካኝነት በግንባር ቀደምነት ተመስርቷል።
" ወሎ የበርካታ ማዕድኖች መገኛ እንደሆነ ይነገራል። የብረት፣ የድንጋይ ክሰል ፣ የነዳጅ ፣ የወርቅ ፣ የከበሩ ድንጊያወችና ላይም ስቶን ወዘተ እምቅ ሀብት አለው።
"የተከዜ ወንዝ መነሻ ወሎ ውስጥ ነው። ለአባይ ገባር የሆነው ታላቁ በሽሎ እና የአዋሽ ገባር የሆነው ቦርከናም ከወሎ የተለያዩ አካባቢወች የሚነሱ ናቸው።