Wollo Worebabo

Wollo Worebabo �ONE DAY!

31/05/2025

የጽንስ መጨንገፍ (ሾትላይ)

------ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባ------
በተለምዶ ሾተላይ “በእንግሊዘኛው Rh-Incompatablitiy” በሚባለው ችግር ብዙ ሰዎች ወልደው መሳም ፈልገው ሳይችሉ መቅረታቸውን፣ በዚሁ ምክንያት አያሌ ቤተሰብ እንደተበተነ ሁላችንም የምናውቀው እውነታ ነው፡፡ ሾተላይ መፍትሄው ቀላል ሆኖ ሳለ በየአካባቢያችን የፈጠረው ቀውስ ቀላል አይደለም፡፡ የመጀመሪያው መፍትሄ ስለችግሩ ተዓማኒ እውቀት ማግኘት ነውና ይህንን መረጃ ሸርና እንድታደርጉ ለተከታዮቻችን እናደርሳለን፡፡

ሾተላይ ምንድን ነው?
ሾተላይ በመባል የሚታወቀው ክስተት ብዙ ጊዜ አንዲት እናት ከመጀመሪያ እርግዝናዋ በኃላ በተደጋጋሚ የሚከሰት የጽንሱ መጥፋት ነው።
ይህ ለምን ይሆናል?

የሰዎች ደም በአራት ዓይነት ይከፈላል(A, B, AB, O) እነዚህ ደግሞ እያንዳንዳቸው በሁለት አበይት መደብ ይከፈላሉ፡ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) እና አር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-)። ለምሳሌ፦ የአንድ ሰው የደም ዓይነት A+ ወይም A- ሊሆን ይችላል። የሰው ማንነቱ ከእናቱና ከአባቱ በሚወስደው የዘር-መል ይወሰናል። የደም ዓይነትም በዚሁ መልክ እንወስዳለን። ከአር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) አባት እና ከአር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-) እናት የሚፈጠር ጽንስ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የመሆን እድሉ የሰፋ ነው።

ሾተላይ የሚከሰተው አንዲት ሴት የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ሆኖ ከዚህ በፊት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) የሆነ ደም ወደ ሰውነቷ ሲገባ ደሟ ውስጥ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የሆኑ የደም ህዋሶችን የሚያጠፋ ንጥረ-ነገር በደሟ ውስጥ ይመረታል። ይህ ንጥረ-ነገር አንዴ ከተመረተ በደሟ ውስጥ እስከ ህይወቷ ፍጻሜ ድረስ ይኖራል።

በመሆኑም በማህጸንዋ ውስጥ የያዘችው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ የተመረተው ንጥረ-ነገር ጽንሱን እንደ ባእድ አካል ስለሚቆጥረው ያጠቃዋል። በዚህም ምክንያት በተደጋጋሚ የምትይዘው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ አስፈላጊውን ህክምና ካልተደረገላት ይሞትባታል። የደም ዓይነቱ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ከሆነ ግን በጤና ይወለዳል። ይህ እንዲሆን ግን የአባትየው የደም ዓይንት አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) መሆን አለበት?

ሕክምናው

1. የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) የሆነች እናት ሕክምናዋ በሆስፒታል ውስጥ መሆን አለበት።
2. በደሟ ውስጥ ያለውን የንጥረ-ነገር መጠን መለካትና የጽንሷን የጉዳት መጠን በማየት ብዙ ሳይጎዳ እንዲወለድ ማድረግ ይቻላል።
3. በሀገራችን በቅርቡ የተጀመረው ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እያለ ደም በመለገስ እንዲያድግና እንዲወለድ ማስቻል።

እንዴት እንከላከለው?

1. ማንኛዋም ሴት ከማርገዟ ወይም ማንኛውንም ደም ከመውሰዷ በፊት የደም ዓይነቷን ማወቅ አለባት።
2. የወንድ አጋሯን የደም ዓይነት ማወቅ አለባት።
3. እርግዝና አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ አጋሯ ከተፈጠረ መጀመሪያ በሚደረግላት ምርመራ (indirect coomb’s test) ንጥረ-ነገሩ አለመመረቱን ያረጋግጣል። እዳይመረት የሚከላከል መድኃኒት (Anti-D) 7ተኛ ወሯ ላይ ይሰጣታል። ከወለደች በኃላ የልጇ የደም ዓይነት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ በድጋሚ መድኃኒቱ ይሰጣታል።
4. እርግዝናው ከማህጸን ውጭ ወይም በውርጃ ቢያበቃም መከላከያውን መድኃኒት መውሰድ አለባት።
"ጤና ለሁሉም "

30/05/2025

የሀገሪቱ የልብ ትርታ ጤና ባለሙያዎች ናቸው።
👉በወረርሺኝ ጊዜ
👉 በጦርነት ጊዜ
👉በሰላሙም ጊዜ

28/05/2025

አልሃምዱሊላህ

28/05/2025
13/04/2025

ዛሬ ሚያዚያ 5/2017 ዓ.ም በደ/ወሎ ዞን በሆጤ አስቴድየም እየተካሄደው በሚገኘው የወንዶች የእግር ኳስ ጨዋታ ወረባቦ ከሀርቡ ጋር የመጀመሪያውን 90 ደቂቃ 1ለ1 ነገር ግን በፔናልቲ ሀርቡ ከተማ አሸንፏል።

13/04/2025

ዛሬ ሚያዚያ 5/2017 ዓ.ም በደ/ወሎ ዞን በሆጤ አስቴድየም እየተካሄደው በሚገኘው የወንዶች የእግር ኳስ ጨዋታ ወረባቦ ከሀርቡ ጋር የመጀመሪያውን 90 ደቂቃ 1ለ1🙏🙏

12/04/2025

በ9ኛው የመላ ደቡብ ወሎ ጨዋታ የቅዳሜ ሚያዚያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በሆጤ ስታዲየም በሚካሄድ የጥሎ ማለፍ የእግር ኳስ ውድድር መርሀ-ግብር ላይ
👉 ወረባቦ ከ ጊምባ ሰዓት ከጠዋት 2:00 በነበረው ጨዋታ ወረባቦ በ90ዎቹ አንድ ጎል ሲያስቆጥር በተጨማሪ አምስት ደቂቃ ውስጥ ጉምባ 1 ጎል ሲያገባ አንድ እኩል ነገር ግን ወሎ ወረባቦ በፔናልቲ 5ለ4 በሆነ ውጤት ጥሎ ማለፉን ጥሎ አልፏል። ዛሬ ላይ በነበረን ቆይታ ሁላችሁም ክብር ይገባቾኋል።!!!

08/04/2025

አላህ ቀብራቸውን ኑር ማረፊያቸውን ፊርደውስ ያድርግላቸው።

እንኳን ለ1446ተኛ ዓመተ ሂጅራ ዒድ አል-ፈጥር በዓል አደረሳችሁ።  "عيد مبارك" تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال كل عم وأنتم بخير ተቀበለሏሁ ሚና ወሚንኩ...
29/03/2025

እንኳን ለ1446ተኛ ዓመተ ሂጅራ ዒድ አል-ፈጥር በዓል አደረሳችሁ። "عيد مبارك"
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال كل عم وأنتم بخير
ተቀበለሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሃል አዕማል ኩሉ ዓም ወዓንቱም ቢኸይር
👉 አላህ ስራችንን ይቀበለን፤ፅናትን ይስጠን፤መጨረሻችንን ያሳምርልን።

24/03/2025

WhatsApp Group Invite

አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካዓትሁ👉ከዚህ በፊት በረመዷን 21ኛው ለይል የወሎ ወረባቦ ቢስቲማ ፉርቃን መስጅድ ግንባታ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም የተካሄዴ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ዛሬም...
24/03/2025

አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካዓትሁ
👉ከዚህ በፊት በረመዷን 21ኛው ለይል የወሎ ወረባቦ ቢስቲማ ፉርቃን መስጅድ ግንባታ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም የተካሄዴ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ዛሬም ረመዳን 25ኛው ለይል የወሎ ወረባቦ ቢስቲማ ፉርቃን መስጅድ ግንባታ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም በድጋሚ በይፋ እየተካሄደ ይገኛልና በቻልነው እንሳተፍ እላለሁ።
ነብዩ (𝓢𝓮𝓵𝓮𝓵𝓪𝓱𝓾 𝓐𝓵𝓮𝔂𝓱𝓲 𝓦𝓮𝓼𝓮𝓵𝓮𝓶 ) ዛሬ በዱኒያ ላይ መስጅድ የገነባ አላህ በጀነት ላይ ቤት ይገነባለታል ብለዋል...
የገንዘብ በረካ ይኖረዋል።
የአላህን ውዴታ ያስገኛል።
የሁልጊዜ የማይቋረጥ ሶደቃ ያገኛል።....
👉ይህ በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ የፉርቃን መስጅድ፦
የዋትሳፕ ቁ1ሊንክ https://chat.whatsapp.com/LyMLkzKpJRh6DMzbEPVrMi

የዋትሳፕ ቁ2ሊንክ https://chat.whatsapp.com/DP7cDPYXjwjL881Q02NE8C

https://t.me/WOREBABO_BISTIMA_MESJIDELFURQAN

"ባረከሏሁ ፊኩም"

WhatsApp Group Invite

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wollo Worebabo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share