Essa Arts

Essa Arts በ essa arts የተለያዩ አዝናኝ አስተማሪ እና ቁምነገር ያዘሉ ምስ?

የተለያዩ ጥራት ያላቸውን  #ለፕሮፋይል  #የፍቅር     #ለእምነት  #ለከቨር        #የሀገር      #የመዝናኛጥራት ያላቸውን ምስሎች ፔጁን ይቀላቀሉ
07/03/2022

የተለያዩ ጥራት ያላቸውን
#ለፕሮፋይል #የፍቅር #ለእምነት
#ለከቨር #የሀገር #የመዝናኛ
ጥራት ያላቸውን ምስሎች ፔጁን ይቀላቀሉ

ለ profile የሚሆን   ፎቶ አተዋል ?? እንግዲያው እኛ ማንነትና አስተሳሰብን የሚያንጸባርቁ ጥራት ያላቸውን ፎቶወች አቅርበናል ። ፔጁን ላይክ በማድረግ ተጨማሪ ያግኙ
07/03/2022

ለ profile የሚሆን ፎቶ አተዋል ?? እንግዲያው እኛ ማንነትና አስተሳሰብን የሚያንጸባርቁ ጥራት ያላቸውን ፎቶወች አቅርበናል ። ፔጁን ላይክ በማድረግ ተጨማሪ ያግኙ

06/03/2022
ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫየኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ከአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ጋር በመሆን ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ፣ አ...
05/03/2022

ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ከአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ጋር በመሆን ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ሁነቶች ያለምን የጸጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቁና የሀገራችን ገጽታ እንዲገነባ የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ ቆይቷል።
ይሁን እንጂ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ቡድኖችና ግለሰቦች ሰሞኑን በሀገራችን በታላቅ ድምቀት በተከበሩት የአድዋ ድል በዓልን እና በዛሬው ዕለት ተከብሮ በዋለው የካራማራ ድል በዓል ላይ በመገኘት በሀገራችን ብሄር ብሄረሰቦችና በህዝብ መካከል ግጭት ለመቀስቀስ ሞክረዋል።
ደከመን ሰለቸን ሳይሉ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ሌት ተቀን የሚጠብቁ የፀጥታ አካላትን ክብር አስፀያፊ ስድቦችን በመሳደብ ደፍረዋል።
ከፀጥታ ኃይሎች ጋር አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ ለመግባት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም።
ይሁን እንጂ የፀጥታ ኃይሎች ሁሉንም ትንኮሳዎች በትግስት በማለፍ በዓላቱ በሰላምና በድምቀት እንዲከበሩ አድርገዋል።
እነዚህ ውስን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ቡድኖችና ግለሰቦች የሚፈልጉትን ህግና ስርዓት ተከትለው ማድረግና ሐሳባቸውን በነፃና በዴሞክራሲያዊ መንገድ በተፈቀደላቸው ስፍራ ማራመድና መፈፀም ሲችሉ ብሄርን ከብሄር፣ ሀይማኖትን ከሀይማኖት ጋር ለማጋጨት ስራዬ ብለው ሌት ተቀን በህቡዕ እና በግልጽ ጭምር እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ግብረ-ኃይሉ ደርሶበታል።
በመሆኑም እነዚህ ውስን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ቡድኖችና ግለሰቦች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ግብረ-ኃይሉ እያሳሰበ ማንም ከህግ በላይ ስላልሆነ ህግን ጥሰን ድርጊታችንን እንቀጥላለን የሚሉ ከሆነ የጋራ ግብረ ኃይሉ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድና በህግም ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው ያሳስባል።
በመጨረሻም ሰላም ወዳዱ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ይህንን ተገንዝቦ ከተማውንና አካባቢውን ነቅቶ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር እንዲጠብቅ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ግብረኃይሉ ይጠይቃል።
የካቲት 26 ቀን 2014 ዓ.ም
ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል

 🇪🇹ክፍል 1🇪🇹ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ከአባታችው ከሸዋው ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴና ከእናታቸው ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አድያም ቅዳሜ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፮ዓ.ም. ደብረ ብርሃን አካባቢ...
02/03/2022


🇪🇹ክፍል 1🇪🇹
ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ከአባታችው ከሸዋው ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴና ከእናታቸው ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አድያም ቅዳሜ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፮ዓ.ም. ደብረ ብርሃን አካባቢ አንጎለላ ከሚባል ሥፍራ ተወልደው፤ በአንጎለላ መቅደላ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ክርስትና ተነሱ።

አያታቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የልጁን መወለድ ሲሰሙ “ምን ይልህ ሸዋ” በሉት ብለው ስም አወጡ። እሳቸው “…ምኒልክ በሚል ስም የሚነግሥ ንጉሥ ኢትዮጵያን ታላቅ ያደርጋታል” የሚል ትንቢት ስለነበር ‘ምኒልክ’ የኔ ስም ነው ብለው ነበር። ሆኖም፣ በህልማቸው ከልጁ ጋር አብረው ቆመው ከሳቸው ጥላ የልጁ ጥላ በልጦ፤ በእግር የረገጡትን መሬት ሲያለካኩ እሳቸው ከረገጡት ልጁ የረገጠው ረዝሞ አዩ። ከዚህ በኋላ “ምኒልክ የኔ ስም አይደለም። የሱ ነው። ስሙን ምኒልክ በሉት” ብለው አዘዙ ይላል ጳውሎስ ኞኞ “አጤ ምኒልክ” በተባለው መጽሐፉ (ገጽ ፲፪)

ምኒልክ እስከ ሰባት ዓመታቸው ድረስ መንዝውስጥ ጠምቄ በሚባል አምባ ከእናታቸው ዘንድ አደጉ።አያታቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ሲሞቱ የሸዋውን አልጋ የምኒልክ አባት ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ ወረሱ።

ዓፄ ተዎድሮስ በጥቅምት ወር ፲፰፻፵፰ ዓ/ም ትግራይንና ወሎን አስገብረው፣ አቤቶ ምኒልክ ገና የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ሳሉ፤ የድፍን አማራንና የወሎን ጦር አስከትተው የሸዋውን ንጉሥ ኃይለ መለኮትን ለማስገበር ሸዋ ገቡ። ሁለቱ መሪዎች ጦርነት ለመግጠም ተዘጋችተው ሲጠባበቁ ንጉሥ ኃይለ መለኮት ባደረባቸው ሕመም ጥቅምት ፴ ቀን አረፉ። በዚህ ጊዜ የሸዋ መኳንንት ሕጻኑን ምኒልክን ከጠላት እጅ እንዳይወድቅባቸው ይዘው ሸሹ፤ ዳሩ ግን ዓፄ ቴዎድሮስ እንደሚከታተሏቸው ስላወቁ ኅዳር ፴ ቀን ፲፰፵፰ ዓ/ም የልጅ ምኒልክ ሠራዊትና የዓፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት በረከት ላይ ገጥሞ የምኒልክ ሹማምንት እነአቶ በዛብህ፣ እነአቶ አንዳርጋቸው ሁሉ ተያዙ። ልጅ ምኒልክም ለቴዎድሮስ ገባ።[3

አድዋ 🇪🇹💪
02/03/2022

አድዋ 🇪🇹💪

😭 የሀዘን መግለጫ 😭🌿ነፍስ ይማር 🌿በደሴ ከተማ የተወለደው እና በብስክሌት ዘርፍ አማራ ክልልን ወክሎ ሲወዳደር የነበረው ወጣት  በልምምድ ወቅት በደረሰበት አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል...
27/02/2022

😭 የሀዘን መግለጫ 😭

🌿ነፍስ ይማር 🌿

በደሴ ከተማ የተወለደው እና በብስክሌት ዘርፍ አማራ ክልልን ወክሎ ሲወዳደር የነበረው ወጣት
በልምምድ ወቅት በደረሰበት አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል 😭
ለወጣቱ ቤተሰቦች ጓደኞች የቡድን አጋሮች እንዲሁም ለመላው የደሴ ከተማ ነዋሪ እና የስፖርቱ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን 🌿

ነፍስን በገነት ያኑራት ?Essa Artsa Arts

HD ጥራት ምርጥ ምርት የአማርኛ ጥቅሶች ፣ፕሮፋይል ፒክቸሮች እንዲሁም አዳዲስ መረጃዎች ያገኛሉ ። ፔጁን LIKE SHARE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ።
27/02/2022

HD ጥራት ምርጥ ምርት የአማርኛ ጥቅሶች ፣ፕሮፋይል ፒክቸሮች እንዲሁም አዳዲስ መረጃዎች ያገኛሉ ። ፔጁን LIKE SHARE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Address

Dessie

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Essa Arts posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Essa Arts:

Share