ልጅ አሌክስ -ቤተ አማራ

ልጅ አሌክስ -ቤተ አማራ ቤተሠብ ሁኑ ቤተሠብ እንሆናለን

05/04/2025
04/04/2025

በፖሊስ ተሽከርካሪ ውስጥ ሆኖ ብር ሲቀበል በቪዲዮ የታየ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ዋለ።

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ ኢንስፔክተር ኤርሚያስ ኤርጌኖ የተባለው የፖሊስ አባል በፖሊስ ተሽከርካሪ ውስጥ ሆኖ ሁለት መቶ የብር ኖት ሲቀበል የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ መዘዋወሩን መነሻ ባደረገ መረጃ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ቪዲዮ አባሉ በተሽከርከሪ ውስጥ ተቀምጦ ሪሲቲ እየሰጠ የ200 ብር ኖት ጉቦ ሲቀበል የሚያሳይ ነው፡፡

በፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥ ተገልጋዩን የሚያማርሩ እና የተቋሙን መልካም ገፅታ ከሚያበላሹ ህገ-ወጥ ተግባራት ውስጥ ጉቦ መቀበል አንዱ መሆኑን የገለፀው ፖሊስ፤ መሰል ህገ-ወጥ ተግባር በሚፈፅሙ አመራርም ሆነ አባላት ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት መብታቸውን በገንዘብ የሚገዙም ሆነ ህገ-ወጥ ተግባር ፈፅመው ጉቦ በመስጠት ከተጠያቂነት ለማምለጥ የሚሞክሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ያሳሰበው ፖሊስ ብልሹ አሰራርን ለማጋለጥ በተለያዩ አግባቦች መረጃን የሚሰጡ አካላትን በማመስገን በቀጣይም መረጃዎችን በማድረስ የህብረተሰቡ ተባባሪነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አሰ‍እተላልፉዋል።

በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ (አስክሬን) በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር!"ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለ...
03/04/2025

በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ (አስክሬን) በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር!

"ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለኸው ብትሄድ እኮ ድካምህ ይቀንስልህ አልነበር?" ሲል ጠየቀው::

ሕጻኑም ሲመልስ እንዲህ አለ:- "ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም" አለው::

ያን ጊዜ ጥያቄውን ያቀረበው ወታደር ራሱን መቆጣጠር አልቻለም ... ስሜቱ በጣም ተነካ ... ዓይኖቹ በዕንባ ታጠቡ::

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጃፓን ይህ ምስል ... የወንድማማችነት፣ የአንድነት ተምሳሌት ሆነ::

እናም ... የሕይወት መርሃችን እንዲህ ቢሆንስ:-

ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም !
እህቴ ናት እኔን አትከብደኝም !
ወንድምህ ቢወድቅ አንሳው !
እህትህ ብትደክም ከጉኗ ቁም !
ወንድምህ ቢስት በየውሃት መንፈስ አቅናው !
እህትህ ስህተት ብትሰራ ይቅርታህን አትንፈጋት ።

እነዚህን ወገኖቻችንን መርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው
25/12/2024

እነዚህን ወገኖቻችንን መርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው

በእራብ አለጋ እየተሰቃዩ ባሉ ወገኖቻችን ላይ ፖለቲካ መስራት በጣም ያበሳጫልወገኖች እንድረስላቸው እራብ ለነገ አይባልም እንበርታ ይህም ቀን አልፎ ያስተዛዝበናል
23/12/2024

በእራብ አለጋ እየተሰቃዩ ባሉ ወገኖቻችን ላይ ፖለቲካ መስራት በጣም ያበሳጫል
ወገኖች እንድረስላቸው እራብ ለነገ አይባልም እንበርታ
ይህም ቀን አልፎ ያስተዛዝበናል

ዳናዊት መክብብ 200,000 ብር ሰጠችዳናዊት መክብብ ለወንድሟ ዘማሪ አቤል መክብብ አዲስ ላሳተመው "ተመስገን" የተሰኘ  አልበም ሕትመት ማገዣ ይውል ዘንድ 200,ዐዐዐ (ሁለት መቶ ሺህ ብር...
22/12/2024

ዳናዊት መክብብ 200,000 ብር ሰጠች

ዳናዊት መክብብ ለወንድሟ ዘማሪ አቤል መክብብ አዲስ ላሳተመው "ተመስገን" የተሰኘ አልበም ሕትመት ማገዣ ይውል ዘንድ 200,ዐዐዐ (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ሰጥታለች።

ለዘማሪ አቤል መክብብ "ተመስገን" የዝማሬ አልበም እገዛ እየተደረገ ያለው በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ዛሬ ታሕሳስ 13 ቀን 2017 በተዘጋጀ ልዩ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ላይ ነው።

አቤል መክበብ በተለይ በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ "ኃጢያተኛው ድንኳን" በተሰኘው መዝሙሩ ይታወቃል።

ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ሆኖ ተመረጠ   | በ28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለቀጣይ አራት አመት ፌዴሬሽኑን በፕ...
22/12/2024

ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ሆኖ ተመረጠ

| በ28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለቀጣይ አራት አመት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንት ለመምራት ምርጫ ተከናውኗል፡፡

በዚህም ከኦሮሚያ ክልል የተወከለው ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመርጧል፡፡

በተደረገው ምርጫ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን 11 ድምፅ በማግኘት ምርጫውን ሲያሸንፍ፤ አትሌት ገ/እግዚአብሄር ገ/ማርያም 9 እንዲሁም አቶ ያዬህ አዲስ 4 ድምፆችን አግኝተዋል፡፡

በውጤቱም መሰረት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ለቀጣይ አራት አመት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን በመተካት ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ተመርጧል፡፡

ኮማንደር አትሌት ስለሺ በአቴንስ እና ቤጂንግ ኦሎምፒኮች የብር ሜዳሊያዎች አሉት፡፡

በሄልሲንኪ እና ኦሳካ የአለም ሻምፒዮናዎች የብር ሜዳልያዎች ለሃገሩ ያስገኘ ሲሆን፤ በፓሪስ አለም ሻምፒዮናም የነሀስ ሜዳልያ አምጥቷል፡፡

አቡጃ ላይ በተደረገው የአፍሪካ ጨዋታዎች በ10ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጵያ አስገኝቷል፡፡

በሃብታሙ ካሴ

አምሐራ
07/11/2024

አምሐራ

 #ከዜናዎቻችን| በርካታ ነዳጅ የሚጠቀሙ ቅንጡ እና ውድ መኪናዎች ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ እንደሆነ ታወቀ (መሠረት ሚድያ)- በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በታገ...
28/10/2024

#ከዜናዎቻችን| በርካታ ነዳጅ የሚጠቀሙ ቅንጡ እና ውድ መኪናዎች ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ እንደሆነ ታወቀ

(መሠረት ሚድያ)- በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በታገደበት በአሁኑ ወቅት በርካታ ነዳጅ የሚጠቀሙ ቅንጡ እና ውድ መኪናዎች ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ እንደሆነ መሠረት ሚድያ ያደረገው ምርመራ ያሳያል።

ታድያ ከሁሉም በላይ መነጋገርያ የሆነው በታዋቂው የንግድ ሰው አቶ ሻቃ ጉርሜሳ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ፕሮሰስ ላይ የሚገኙት 700 ይደርሳሉ የተባሉት V8 መኪናዎች ጉዳይ ነው።

የ Shaka Mall ባለቤት የሆኑት አቶ ሻቃ መኪና በማስመጣት እና በመሸጥ ከበርካታ አመታት በፊት ጀምሮ ልምድ ያላቸው ቢሆኑም በዚህ ወቅት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በብዛት ማስገባት መቻላቸው ለብዙዎች እንቆቅልሽ እንደሆነ ሰምተናል።

በቅርቡ 700 V8 ላንድ ክሩዘር መኪናዎችን ሊያስገቡ ሂደት ላይ እንደሆኑ የታወቀ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከ40 በላይ የሚሆኑት በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ላይ ጥሩ የአመራር ብቃት ላሳዩ የመንግስት ተሿሚዎች በስጦታ መልክ የሚበረከቱ መሆናቸው ተሰምቷል።

"መድሃኒት ፈልጎ ማግኘት ከባድ በሆነበት፣ ብታገኝም ዋጋው በማይቀመስበት አገር እንዲህ አይነት የሃብት ብክነት እየተፈፀመ ይገኛል" ያሉት አንድ ጉዳዩን የሚያውቁ የመረጃ ምንጫችን ናቸው።

የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን የተሽከርካሪ አጠቃቀም አስመልክቶ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የዛሬ ስድስት አመት ያወጣው መመሪያ በበርካታ ተቋማት እየተተገበረ አለመሆኑ ተደጋግሞ እየተነሳ ይገኛል።

በመመሪያው ቁጥር 4 ንዑስ ቁጥር 1 ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ወጪ ቆጣቢና ውጤታማ የፋይናንስ አጠቃቀም እንዲኖር ለከተማ ውስጥ ስራ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎችን እንዲጠቀሙ ተደንግጓል።

በዚህ መሰረት የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ቪ8፣ ቪ9፣ ፕራዶና ፓጃሮ ተሽከርካሪዎችን ከሚጠቀሙ ይልቅ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎችን ቢጠቀሙ ከፍተኛ ወጪ በመቀነስ ውጤታማ አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል ተገልፆ ነበር።

ይሁንና አሁን ድረስ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ቪ8 እና ሌሎች ተመሳሳይ መኪናዎችን ከተማዎች ውስጥ እንደሚጠቀሙ መሠረት ሚድያ በቅርቡ መዘገቡ ይታወሳል።

via meseret media

ቦረና ሳይንት ብሔራዊ ፓርክ💚💛❤️ ዋና ፅ/ቤቱ በመካነ-ሰላም ከተማ የሚገኝ ድንቅ ቦታ ።ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ቦረና ሳይንት ብሔራዊ ፓርክ  በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በ3 ወርዳወች ማ...
15/08/2024

ቦረና ሳይንት ብሔራዊ ፓርክ💚💛❤️ ዋና ፅ/ቤቱ በመካነ-ሰላም ከተማ የሚገኝ ድንቅ ቦታ ።

ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ቦረና ሳይንት ብሔራዊ ፓርክ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በ3 ወርዳወች ማለትም በቦረና፣ በመሀል ሳይንትና በአምሃራ ሳይንት መካከል ይገኛል። ግንቦት 28 ቀን በ2001 ዓ.ም የፓርክነት ደርጃ አግኝቶ 4375 ሔክታር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ተከልሏል።

ፓርኩ በርካታ ብዝኃ ህይወትን አካቷል። ለአብነት ያህልም 496 የዕጽዋት ዝርያዎች ሲኖሩ ከነዚህ ውስጥ ብርቅየ የሚባሉት ዝግባ፣ ኮሶ፣ ወይራ፣ ጅብራ ፣ አስታ እና ገመራ ናቸው። ፓርኩ ከ30 በላይ የእንስሳት ዝርያዎች ይገኙበታል። ከነዚህም ውስጥ ቀይ ቀበሮ፣ የምኒሊክ ድኩላ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ እና የስፓርክ ጥንቸል ይገኙበታል። ከነዚህ በተጨማሪም 84 የአዕዋፍ ዝርያዎች በፓርኩ ይገኛሉ። በሀገር አቀፍ ደረጃ በቁመቱ 2ኛ ደረጃ በውፍረቱ ደግሞ 1ኛ ደረጃ የሆነው የዝግባ ዛፍ እዚህ ብሔራዊ ፓርክ ይገኛል።

የየጁወች ምድር ወልድያ ሽንቁሩ ዋሻ
15/08/2024

የየጁወች ምድር ወልድያ ሽንቁሩ ዋሻ

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ልጅ አሌክስ -ቤተ አማራ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share