Dilla town culture , tourism & Gov,com

Dilla town culture , tourism & Gov,com Promotion and public figure page

21/11/2025
‎ዲላ ከተማ እና የሰሟ አሰያየም :-‎‎ በአንድ ወቅት ትናንሽ ሰፈሮችና መንደሮች የነበሩ አካባቢዎች በፖለቲካዊ ስርዓትበማህበራዊ መስተጋብር በኢኮኖሚ ፋይዳዎችና መሰል ምክንያቶች አድገዉ የብ...
10/11/2025

‎ዲላ ከተማ እና የሰሟ አሰያየም :-

‎ በአንድ ወቅት ትናንሽ ሰፈሮችና መንደሮች የነበሩ አካባቢዎች በፖለቲካዊ ስርዓትበማህበራዊ መስተጋብር በኢኮኖሚ ፋይዳዎችና መሰል ምክንያቶች አድገዉ የብዙ ሺህዎች መኖሪያ ሆነዉ ማየት የተለመደ ነው።

‎ በዚህ ሂደት ውስጥ በቡድንም ሆነ በግል ለትናንሽ መንደሮች ማደግና መለወጥ አስተዋጽአቸው የጎላ ግለሰቦች መኖራቸው የማያጠያይቅ ጉዳይ ነው።

‎ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር መቀመጫ ዲላ ከመንደርነት አንስቶ አሁን ካለችበት የእድገት ጎዳና ስትደርስ የበርካታ ግለሰቦችና ቡድኖች ሚና የጎላ ቢሆንም የመጀመሪያው ጠጠር የጣሉትን የባላምባራስ በደቻ ኡዶ ቡርይን/ዩባ አስተዋጽኦ የሚተካ አለ ብሎ መገመት ይከብዳል።

‎ ባላንባራስ ''ዩባ'' በደቻ ኡዶ 1861 ዓ.ም በቀድሞ መጠሪያ በሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት በጌዴኦ አውራጃ በወናጎ ወረዳ በወላጅ አባታቸው ኡዶ ቡርይ በተቆረቆረችውና በኋላም በስማቸዉ በተጠራችዉ ሚቺሌ-ኡዶ የገጠር ከተማ ተወለዱ።

‎ የአባቱ ልጅ የሆኑት ዩባ በደቻ ኡዶ እድሜያቸው ለአቅመ አዳም ሲደርስ በ1887 ዓ.ም ከመጀመሪያ ሚስታቸው ከወ/ሮ ጂቦ ባንት/Jibboo Banti ጋር በትዳር ተጣምረው ዘጠኝ ልጆችን አፍርትዋል።

‎ ከ12 ዓመት በኋላም በ1898 ዓ.ም ከሁለተኛ ባለቤታቸው ከወ/ሮ ሲቦ ኮሜ/Baabba Simboo Ko'me አስር ልጆችን ያገኙ ሲሆን በ1902 ዓ.ም ከሶስተኛ ባለቤታቸው ከወ/ሮ ማኖ በደቻ/Baabba Maanoo Badachcha ካገኟቸው ሶስት ልጆችን ጨምሮ የ22 ልጆች አባት ነበሩ።

‎ ባላምባራስ ዩባ በደቻ ኡዶ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1882 ዓ.ም በተወለዱበትንና ያደጉበትን እንዲሁም ሀብትና ንብረትያፈሩበትን የአባታቸዉን ቀዬ ሚቺሌ ኡዶን ለቀው ወደ ዲላ መጡ።
‎ ያኔ ዲላ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አልከተሙባትም፣ከ15 በላይ የፋይናንስ ተቋማትም ንግዱን አልመሩትም፣የግልና የመንግስት ተቋማት መናገሻም ዳሩ በበረሃ ቁጥቋጦች የታጨቀች እጅግ የሚወብቅ ሙቀት ያላትና በወባ ትንኞች የተሞላች ስትሆን አንዲት መንደር እንኳን አልነበራትም።

‎ ነጋዴዎችም ረዥም ጉዞ ሲጋዙ ለድካማቸው እፎይታ ከማረፍ ባለፈ ዲላን ለኑሮ ሆነ ለንግድ የደፈራትአልነበረም።

‎ባላምባራስ ዩባ በደቻ ኡዶ የአሁኑ(በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኘዉ) የጌዴኦ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤትን ጨምሮ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን የዲላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርሰትያንን እስከ ኢቲዮ ቴሌኮም ዲላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ድረስ ከ10 ሄክታር የሚበልጥ ቦታን ይዘው ሰፈሩ።
‎ለተከታታይ 10 አመታትም አካባቢውን ለኑሮና እርሻ
‎ሲያለማምዱ ከቆዩት ዩባ በደቻ ኡዶ ከ10 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1902 ዓ.ም ትንባሆ በመትከል ለጪጩና ለቀባዶ ገበያ በማቅረብ ገንዘብ ማግኘታቸውንም ይነገራል።

‎ ምድሩም ግብርናውን እየለመደው እንዳለ እያስተዋሉ የመጡት ሰዎች ባላምባራስ ዩባ በደቻ ኡዶን ይጠጓቸው ጀመር፣እሳቸዉም ወዳጆቻቸውና ዘመዶቻቸውን ሊያገለግሏቸው የሚችሉ ሰዎችን ይጠሯቸው ነበር።

‎ አንድ ሁለት ሲባልም በአጭር አመታት ዲላ ሰዎች የሚኖሩባት መንደር ሆነች።በወቅቱም የተለያዩ የግብርና ምርቶች ጨምሮ ጨውና የቤት እንስሳትን ለመገበያየት ዲላ የገበያ ቦታ ስላልነበረች ጪጩ አልያም አባያና ቀባዶ ለመሄድ ይገደዱ ነበር።ገበያ ፍለጋ ጪጩ ሲሄዱ ሴት ልጆቻቸው ይጠለፉና የተለያየ ጥቃቶች ይደርስባቸዋል።

‎ቀይረውም ቀባዶና አባያ ሲሄዱ ወንድ ልጆቻቸው እስከ መሰለብ የሚደርስ ጥቃት ይደርስባቸው እንደነበር ይነገራል።
‎ ።
‎ በገበያ እጦት ምክንያት የሚደርስባቸው እንግልትና ጥቃት እንደተጠበቀ ሆኖ ባላምባራስ በደቻ ኡዶ በ1903 ዓ.ም አገልጋዮቻቸውና በርካታ ወላጆቻቸውን በማስተባበር የዘሩት ጤፍ ውጤት አስገኝቶላቸዋል።

‎ምርቱም በአንድ በኩል ለባለጸጋ ሲያደርጋቸው በሌላ በኩል ለገበያ ለማብቃት ተቸግረው ሳሉ በቀድሞ አጠራር የሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ሹም የነበሩት ደጃዝማች ባልቻ አባ ነብሶ የዘመኑን የጪጩ ገበያ ቀረጥ ወስደው በቂ መስተንግዶ ባለማግኘታቸው ሲመለሱ ባላምባራስ ዩባ በደቻ ኡዶ ተቀብለው አስተናግደዋል።

‎በመቀጠልም በመንደሩ ስላለው የገበያ ችግር አጫውቷቸው ደጃዝማች ባልቻም ይህንን ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ግዛቱ እንዲያመለክቱ በመጠቆም መርቀው ተሰናብተው ወደ መጡበት ተመልሰዋል።

‎ በ1904ዓ.ም ባላምባራስ ዩባ በደቻ ኡዶ የነት ማዕረጋቸዉን ያገኙበት ዲላም ለገበያ ማህከልነት የታጨችበት ዘመን ነው።ባላምባራስ ዩባ በደቻ ኡዶም 120 መስፈሪያ ጤፍ፣ሙክት በግ፣ ቅቤና ማር እንዲሁም ከመንደራቸዉ ውጪ ከአባታቸው በዉርስና በግዥ ያፈሩትን የቡና ማሳና የእርሻ ቦታን እና በቅሎሆቻቸውን በአራት መቶ አርባ ብርበመሸጥ የተጠቀሱትን እጅ መንሻና አስራ አምስት ሰዎችን አስከትለው በወቅቱ የሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት መቀመጫ ወደሆነችው ተፈሪ-ኬላ በመሄድ በመንደሬ ገበያ ይቋቋምልኝ ጥያቄያቸዉን አቅርበዋል።

‎ ደጃዝማች ባልቻ ጥያቄው ተገቢ መሆኑን ተቀብለው ከባላምባራስ ዩባ በደቻ ኡዶ ጋር አምስት ሰዎችን ገበያ በዲላ እንዲቋቋም ልኳቸዋል።
‎ገበያውም የአሁኑን የዲላ ቴሌኮምን ጨምሮ በአሁኑ መጠሪያ ቦዒቴ ሰፈርን ይዞ
‎ተቋቋመ።
‎ደጃዝማች ባልቻም "ዲላ ከተማ ናት"ብለው በመሰየም በሰሜን ቀባዶ በደቡብ ጪጩ በምዕራብ 130 ጋሻ እስከ አባያ በምሰራቅ 120 ጋሻ እስከ አንዲዳ ለዩባ በደቻ ኡዶም የ"ባላንባራስ"ነት ማዕረግ ሰጥተዋል።

‎ዲላም ለመጀመሪያ ግዜ በ1904 ዓ.ም ጥር ወር ውስጥ በራሷ የገበያ ማዕከል ተገበያይታለች።

‎ገበያውን ያቆሙ ሰዎች ሲመለሱም ባላምባራስ ዩባ በደቻ ኡዶ አንድ አንድ ብር አበል በመክፈል በግዛቱ ታሪክ ከደሞዝ በለይ የተከፈለ ከፍተኛ የውሎ አበል ሆኖ ተመዝግቧል።

‎[ስለ ዲላ ከተማ ስያሜ በርካታ መላምንት የሚሰጥ ቢሆንም የባላምባራስ ዩባ በደቻ ኡዶ የቅርብ ሰዎች ባላምባራስ በደቻ ለከተማዋ ስያሜ ወደ ማጌኖ/ፈጣሪ ጸሎት ማድረጋቸውን ተከትሎ ከሰማይ ግዙፍ ነገር መውደቁንና
‎ከፍተኛ የሆነ የሚል የሚያስገመግም ድምፅ ማሰማቱን ይስማሙበታል።ባላምባራስ ዩባ በደቻ ኡዶ ከተሰማው የሚል ጩኸት ተነስተው የገበያ መንደሩንም ዲላ ማለታቸው ይነገራል ።እስከአሁንም ድረስ ዲላ ከተማ ተብሎ ሲጠራ ባላምባራስ ዩባ በደቻንም የሰማይ አምላክ ይሰማዋል ብሎ በማመን በበደቻ አድባር ይማላል፣ይመረቃል፣ይረገማልም።

‎ ባላምባራሰ ዩባ በደቻ ኡዶም በ1946 ዓ.ም አገልጋያቸው በነበሩት ጌጤ በምትባል ሴት በሚል ተከሰው በፍርድ ቤት የተወሰነባቸውን
‎ገንዘብ ለመክፈል ከሸጡት የእርሻ ቦታ ዉጪ በ1949 ዓ.ም የጤና እክል ገጥሟቸው ለቀዶ ህክምና ወላይታ ሶዶ እስከሄዱበት ጊዜ ድረስ በርካታ ሄክታር መሬት በእጃቸው እንደነበር ይነገራል።

‎ በኋላም እስከ 1951 ዓ.ም ድረስ በነበሩት ጊዜያት ጨቋኝ የነበረውን የአቢሲኒያ ንጉሳዊና ሰለሞናዊ ስርዓት አንድም ለመንግስታት ተቋም ሌላም ጊዜ ለንግድ ሲያሻውም ለመኳንንቶች እየተባለ ያለምንም ካሳ እራሱ ቀንቶ ሀገር ያቀና ጀግናን ወድያ ገፍቶ ለፍቶና ጥሮ ያለማውን ጓሮ ዛሬም ድረስ አንዲት ክፍለ ከተማ ከመሰየም ያለፈ ለታታሪነቱ፣ለጀብደኝነቱ፣ለጀግንነቱ ለእሱም ሆነ ለቤተሰቡ የታሰበ ዲላ ከተማ እና የሰሟ አሰያየም :-

‎ በአንድ ወቅት ትናንሽ ሰፈሮችና መንደሮች የነበሩ አካባቢዎች በፖለቲካዊ ስርዓትበማህበራዊ መስተጋብር በኢኮኖሚ ፋይዳዎችና መሰል ምክንያቶች አድገዉ የብዙ ሺህዎች መኖሪያ ሆነዉ ማየት የተለመደ ነው።

‎ በዚህ ሂደት ውስጥ በቡድንም ሆነ በግል ለትናንሽ መንደሮች ማደግና መለወጥ አስተዋጽአቸው የጎላ ግለሰቦች መኖራቸው የማያጠያይቅ ጉዳይ ነው።

‎ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር መቀመጫ ዲላ ከመንደርነት አንስቶ አሁን ካለችበት የእድገት ጎዳና ስትደርስ የበርካታ ግለሰቦችና ቡድኖች ሚና የጎላ ቢሆንም የመጀመሪያው ጠጠር የጣሉትን የባላምባራስ በደቻ ኡዶ ቡርይን/ዩባ አስተዋጽኦ የሚተካ አለ ብሎ መገመት ይከብዳል።

‎ ባላንባራስ ''ዩባ'' በደቻ ኡዶ 1861 ዓ.ም በቀድሞ መጠሪያ በሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት በጌዴኦ አውራጃ በወናጎ ወረዳ በወላጅ አባታቸው ኡዶ ቡርይ በተቆረቆረችውና በኋላም በስማቸዉ በተጠራችዉ ሚቺሌ-ኡዶ የገጠር ከተማ ተወለዱ።

‎ የአባቱ ልጅ የሆኑት ዩባ በደቻ ኡዶ እድሜያቸው ለአቅመ አዳም ሲደርስ በ1887 ዓ.ም ከመጀመሪያ ሚስታቸው ከወ/ሮ ጂቦ ባንት/Jibboo Banti ጋር በትዳር ተጣምረው ዘጠኝ ልጆችን አፍርትዋል።

‎ ከ12 ዓመት በኋላም በ1898 ዓ.ም ከሁለተኛ ባለቤታቸው ከወ/ሮ ሲቦ ኮሜ/Baabba Simboo Ko'me አስር ልጆችን ያገኙ ሲሆን በ1902 ዓ.ም ከሶስተኛ ባለቤታቸው ከወ/ሮ ማኖ በደቻ/Baabba Maanoo Badachcha ካገኟቸው ሶስት ልጆችን ጨምሮ የ22 ልጆች አባት ነበሩ።

‎ ባላምባራስ ዩባ በደቻ ኡዶ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1882 ዓ.ም በተወለዱበትንና ያደጉበትን እንዲሁም ሀብትና ንብረትያፈሩበትን የአባታቸዉን ቀዬ ሚቺሌ ኡዶን ለቀው ወደ ዲላ መጡ.
‎ ምንጭ--- ሻላይቱ መጽሔት

10/11/2025
በነገር ሁሉ እግዚአብሔር ለዕቅዳችን ስኬትን፤ ለምድራችን ሠላሙን ያብዛልን።
03/11/2025

በነገር ሁሉ እግዚአብሔር ለዕቅዳችን ስኬትን፤ ለምድራችን ሠላሙን ያብዛልን።

‎በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ከአንገት በላይ ነፃ ቀዶ ጥገና ህክምና ለ3 ቀናት ስያካህዱ የቆዩት የጤና ባለሙያዎች  የጌዴኦ ዞንን ብርቅዬ ቅርሶች ጎበኙ‎=====*********** ...
01/11/2025

‎በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ከአንገት በላይ ነፃ ቀዶ ጥገና ህክምና ለ3 ቀናት ስያካህዱ የቆዩት የጤና ባለሙያዎች የጌዴኦ ዞንን ብርቅዬ ቅርሶች ጎበኙ
‎=====*********** ******========
‎ጌዞባቱ: ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም - ዲላ

‎በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ለሶስት ቀናት የቆየ ነፃ ከአንገት በላይ ቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎት ያካሄዱት የጤና ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት የዓለም ዐቀፍ ቅርስ የሆነውን የጌዴኦ ታሪካዊ የጨልባ ቱቲቲ ትክል ድንጋይ የመካነ ቅርስ ሥፍራን ጎብኝተዋል ።

‎በጉበኝት ፕሮግራሙ የክብር ተሳታፊ እንግዶች ከውጪ ሀገር የመጡት የአንገት በላይ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪሞች በሀገር ውስጥ ካሉ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ጋር በመቀናጀት ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ህፃናት ህክምናውን በነፃ ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ በጌዴኦ ዞን የተደረገውን ነጻ የህክምና አገልግሎት ፕሮግራም ባጠናቀቁበት ወቅት ነው።

‎የዲላ ዩንቨርስቲ የመማሪያና ህክምና ሆስፒታል ኃላፊ አቶ ትዝአለኝ ተስፋዬ እንደተናገሩት የጌዴኦ አባቶች ሀገር በቀል ዕውቀት በዩኔስኮ የተመዘገበው የጌዴኦ ዞን ባህላዊ መልክዓምድር ትሩፋት የሆነውና በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ከምገኙት ትክል ድንጋዮች ታሪክ በአንድ ሥፍራ በጥቂት ሄክታር ውስጥ ከ1ሺ656 በላይ ትክል ድንጋዮች ሰፍሮ መገኘት መካነ ቅርሱን ልዩ ያደርገዋልብሏል።

‎ አክሎም በዞኑ በተደረገው ነጻ ከአንገት በላይ ቀጥተኛ ህክምና ከ35 ህጻናት በላይ ለ2ኛ ጊዜ እርዳታ የተደረገላቸው ሲሆን ለበርካታዎቹ የምርመራ አገልግሎት ተደርጎላቸዋል።

‎የጌዴኦ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ዲላ

23/10/2025

22/10/2025
የዓመቱ አመርቂ ሥራ
21/10/2025

የዓመቱ አመርቂ ሥራ

Address

Dilla

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dilla town culture , tourism & Gov,com posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share