Tamirat eniyew

Tamirat eniyew Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tamirat eniyew, Digital creator, Dire Dawa.

28/07/2023
20/07/2023

ድምፃዊ እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬቱን አስመልክቶ ይህን ብላለች

«እምዬ አገሬ ውድ አገሬ ኢትዮጵያ...እንዲሁም በጣም የምወዳችሁ፣ የማከብራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ፥ ሰላም ሰላም ሰላም ብያለሁ!

በአክብሮት የሰጣችሁኝን የአክብሮት ዶክትሬት በጣም በትልቅ ደስታ ነው የተቀበልኩት። በጣም አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

እኔ በጣም፣ በጣም ነው የገረመኝ........ ታጭቼ ብገኝ እንኳን የሚያስደንቀኝ ነበር፤ .......ተመርጬ ስለተነገረኝ በጣም ነው የማመሰግነው። በጣም እግዚአብሔር ያክብርልኝ።

ፍቅራችሁ እንዲሁ አክብሮታችሁ ስለሆነ፣ በእኔ እና በወገኖቼ ስም፤ እንዲሁም በዚህ ሁሉ ደስ በሚላቸው ኢትዮጵያውን ስም ከልቤ በጣም በጣም አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ሕይወታችሁን ይባርከው።

የኢትዮጵያ፥ ዛሬ ያሉትን ተማሪዎች፣ እንዲሁም የወደፊቱን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክ። አገራችንን መንፈስ ቅዱስ ይጠብቅልን።

ያስቸግራል ለመግለጽ ደስታዬን። በጣም አመሰግናለሁ። በጣም ክብራችሁ እና ፍቅራችሁ ከልክ ያለፈ ነው በቃ... ለእኔ የሚገባኝ አይደለም። ግን ይኽን ሁሉ ስላከበራችሁኝ በጣም እግዚአብሔር ይስጥልኝ። በጣም አመሰግናለሁ።

የኢትዮጵያን ሕዝብ እግዚአብሔር ይጠብቅልን። ምስጋናዬ በጣም ከፍ ያለ ነው።

በአካል ተገኝቼ አንድ ቀን እዚያ መጥቼ አያችኋለሁ። በሰላም ቆዩኝ። ይኽንን አጭር መልእክቴን ይቅር በሉኝ። ሌላ ጊዜ በደንብ አመሰግናችኋለሁ። (ሳቅ)

በጣም እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

እጅጋየሁ ነኝ። Thank You!»

19/07/2023

እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ)
(የሕይወት ዘመን ተሸላሚ)

ድምጻዊ፣ ባለቅኔ፣ ተዋናይት፣ የዜማና ግጥምየ ደራሲ እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የ15ኛው የአማራ ክልል ባህልና ኪነ-ጥበብ ፌስቲቫል "ለባህልና ኪነ-ጥበብ እድገት" ለአበረከተችው የላቀ አስተዋጽኦ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ሆና የክብር የእውቅና ሽልማት ተሰጥቷታል። ❤️❤️❤️



🙏

ለድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የዕውቅና ሽልማት ተሰጠ ********************* ለ15ኛ ጊዜ የተካሄደው የአማራ ክልል ባህል እና ኪነ ጥበባት ፌስቲቫል ለድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባ...
09/07/2023

ለድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የዕውቅና ሽልማት ተሰጠ
*********************

ለ15ኛ ጊዜ የተካሄደው የአማራ ክልል ባህል እና ኪነ ጥበባት ፌስቲቫል ለድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)፣ ለጌትነት እንየው እና ለአበበ ብርሃኔ የዕውቅና ሽልማት ሰጥቷል።

ገና በልጅነት ዘመኗ ጀመሮ ስለ ሀገር እና ስለ ሀገር ፍቅር በማቀንቀን በብዙዎች ልብ ውስጥ የገባችው እጅጋየሁ ሽባባው ላደረገችው አስተዋፅዖ ነው ሽልማት የተበረከተላት። ጂጂ ለሀገር ባቀነቀነቻቸው ዘፈኖቿ ብዙዎችን አስተሳስራለች።

የሀገር በቀል ሥራዎቿ በእጅጉ የሚወደዱላት፣ ኢትዮያዊነትን የምታስተጋባ፣ በኢትዮጵያዊነት ፍቅር የተንቀለቀለች፣ ሀገርን ያስቀደመች፣ ሕዝብ የሚያስፈልገውን ሁሉ የምታቀነቅን ድንቅ የጥበብ ሰው መሆኗ በሽልማት መርሐ-ግብሩ ላይ ተነግሯል።

እጅጋየሁ ሽባባው በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ የራሷን አሻራ ያሳረፈች፣ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ እያለች የተሰማች፣ ትንቢት የሚመስል ቃል አስቀድማ የተናገረች በሳል ድምፃዊት መሆኗም በመድረኩ ተነሥቷል።

ይገባሻል ጂጂዬ

28/06/2023



ይችን እንቁ ህፃን ልጅ እስኪ እስከመጨረሻው አዳምጧት

26/06/2023

➦ አሁንማ ~ ሞትም አይፈራ 😔
➟ ቴዲ አፍሮ ( ሀገራችን ያለችበት ወቅታዊ እዉነታ በጥበብ እይታ )

Like share & Follow me

.ደስ የሚል ዜና 👉🏾የምንወዳት ድምጻዊት ጂጂ ወደ ኢትዮጵያ በቅርቡ ልትመጣ ነው 🙏🏽❤️📌እህትዋ ሶፊያ ሽባባው ለኤንቢሲ "የጂጂ ፀሐይ አልጠለቀችም:: የጂጂ ፀሐይ ኢትዮጵያ ላይ ነች" በማለት...
29/03/2023

.ደስ የሚል ዜና 👉🏾የምንወዳት ድምጻዊት ጂጂ ወደ ኢትዮጵያ በቅርቡ ልትመጣ ነው 🙏🏽❤️

📌እህትዋ ሶፊያ ሽባባው ለኤንቢሲ "የጂጂ ፀሐይ አልጠለቀችም:: የጂጂ ፀሐይ ኢትዮጵያ ላይ ነች" በማለት እንደምትመጣ ፍንጭ ሰጥታለች::

📌ጀግኒት በደማቁ እንቀበላታለን ትምጣልን

የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከተናገራቸው ጋዜጠኛ፦ ሕይወትህ ላይ መሰናከሎች ሲያጋጥሙህ በምን አይነት መንገድ ነው የምታልፋቸው?ቴዲ አፍሮ፦ ‹‹... ቀላል ይሆናል ...
25/03/2023

የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከተናገራቸው

ጋዜጠኛ፦ ሕይወትህ ላይ መሰናከሎች ሲያጋጥሙህ በምን አይነት መንገድ ነው የምታልፋቸው?

ቴዲ አፍሮ፦ ‹‹... ቀላል ይሆናል እያልኩ ነው የማልፋቸው። ክብደታቸውን ሳስብ ይከብዱኝና እንድቆም ወይም እንዳቋርጥ ያደርጉኛል። ነገር ግን ክብደታቸውን ማየት ሳይሆን ያለውን የመጨረሻ አቅም ተጠቅሞ ወደ 'ሚቀጥለው ጫፍ ለመሄድ ቀላል ይሆናል ብሎ መነሳትን ይጠይቃል። "የናቁት ይወርሳል" እንደሚባለው ትንሽ ያደረጉት ነገር ትልቅ ይሆንና በጣም ትልቅ ያደረጉት ነገር ደሞ በትንሽ ነገር ግን ትንሽ በማይባል ሀሳብ ሊሸነፍ ይችላል።

ለምሳሌ፥ ጣልያኖች በአድዋም ሆነ በማይጨው ወረራ በሚያካሂዱበት ግዜ የነበራቸውን ታንክ የነበራቸውን የጦር መሳርያ አቅም አይተው አባቶቻችን ጋሻ፣ ጦር፣ ቢላ እና ጎራዴ ይዘው ነገሩን ቢያስቡት ሎጂካሊ አይሆንም። ነገር ግን አሸናፊው ሰው ውስጥ የተቀመጠው መንፈስ ነው አሸናፊ የሚያደርገው። መንፈስን ጠንካራ አድርጎ ሁልግዜም ለአሸናፊነት የመጨረሻውን አቅም ሁሉ መጠቀም ጥሩ ነው። ስለዚህ ከባድም ቢሆን ቀላል ይሆናል ብሎ ማሰብ ይሻላል።››

ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

ካህኑ በድንጋይ ተወግረው ተገደሉ!😭በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ መጋቢት 14/2015 ዓ.ም ቀሲስ ዐባይ መለሰ የተባሉ ካህን ቅዳሴ ጨርሰው ወደ ቤታቸው በመሄድላይ እንዳሉ በድንጋይ ተ...
24/03/2023

ካህኑ በድንጋይ ተወግረው ተገደሉ!😭

በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ መጋቢት 14/2015 ዓ.ም ቀሲስ ዐባይ መለሰ የተባሉ ካህን ቅዳሴ ጨርሰው ወደ ቤታቸው በመሄድላይ እንዳሉ በድንጋይ ተወግረው ሕይወታቸው ማለፉን የዐይን እማኞች እንዳረጋገጡለት የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።

የሆርሲሳ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የነበሩት ቀሲስ ዐባይ መለሰ ሕይወታቸው ሲያልፍ ችግሩ ታወቀ እንጂ አስቀድሞ በአካባቢው አገልጋዮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይደርስ እንደነበር መረጃ ሰጭዎቻችን በቦታው ለተገኘው ዘጋቢያችን ገልፀዋል ብሏል ቴሌቪዥን ጣቢያው።

@የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን

— Lyrics for Kelal Yihonal by Teddy Afro. ዳገቱ ላይ አትዛል ጉልበቴ የተራራው ጫፍ ፍቅር ናት ርስቴ ቀላል ይሆናል ቀና አድርገኝ ፅናቴ........ሰው❤️ፍቅር ነው ሀ...
18/03/2023

— Lyrics for Kelal Yihonal by Teddy Afro. ዳገቱ ላይ አትዛል ጉልበቴ የተራራው ጫፍ ፍቅር ናት ርስቴ ቀላል ይሆናል ቀና አድርገኝ ፅናቴ........ሰው❤️

ፍቅር ነው ሀገሩ ፣
ፍቅር ነው በትሩ ፣
የጥንካሬው ምንጭ የቴዲ ምስጢሩ ፤

Address

Dire Dawa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tamirat eniyew posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tamirat eniyew:

Share