Meriba production Dire Dewa

Meriba production Dire Dewa Meriba Production Dire Dewa

05/06/2024
05/06/2024

ሎዛ በአሜሪካ.... 🇺🇸

⚽ ለክለቧ እስካሁን 5 ጨዋታዎችን አድርጋለች

⚽ ሁለት ጎሎችን አስቆጥራለች

⚽ ሶስት የጎል ኳሶችን አቀብላለች

⚽ በ USL ሴቶች ሊግ በምስራቃዊ ዞን የሚወዳደረው የሎዛ ክለብ ከመሪው በሶስት ነጥብ ርቆ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል

⚽ የሉሲ አምበልና የቨርጂኒያ ማራውደርስ 10 ቁጥር ለባሽ ሎዛ አበራ በዘንድሮው የሰሜን አሜሪካ የስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ የክብር እንግዳ ሆና ተጋብዛለች

⚽ "አክብረው ስለጋበዙኝ በጣም ደስ ብሎኛል፤ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሚገኙበት በዚህ ትልቅ መድረክ ላይ ስለምገኝ ደስታዬ እጥፍ ነው፤ ለግብዣው የማህበሩን የቦርድ አባላት በሙሉ በጣም አመሰግናለሁ" ብላለች ሎዛ

⚽ የአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች የሆነችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ ግርማ በተመሳሳይ በአትላንታው ፌስቲቫል ላይ የክብር እንግዳ ነች

⚽ ሎዛ አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለተቋቋመውና በህፃናት ትምህርት ላይ ለሚሰራው love in action የበጎ አድራጎት ተቋም አምባሳደር ሆና ተሹማለች

(ታምሩ ዓለሙ)

21/02/2024

🎯 ስለ ተዋናይት ዕድለወርቅ ጣሰው 👌💞

| አንዲት ሴት እንዴት 42 ደቂቃውን እጇን እንዲህ እንዳጣመረች ፤ የተቀመጠበችበትን ቦታ ሳትቀይር ፤ የተለየ ረዥም ሳቅ ሳትስቅ ቃለመጠይቋን ትጨርሳለች? እድለወርቅ ጣሰው ላይ ያየሁት ስርአት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሰልፍ በላይ እጅግ ያማረ እና ጠጠር ያልተወረወረበት ባህር ያለውን መርጋት አእምሮዬ ላይ ነው በድምጿ እና በማንነት ቡሩሿ የሳለችው።

ይህቺ ሴት ስክሪንህን በገለጥክ ቁጥር አታያትም ፣ ከተማውን በየቀኑ ብትዞር በሦስት ወራት ውስጥም አታገኛትም ፣ አርቲስት ነችና ብለህ የፊልም ሲዲዎችህን ስትበረብር ብትውል ከጥቂቶቹ ላይ ካልሆነ ተመሳሳይ ስም እንኳ አታገኝላትም። ብዙዎች ለአንድ ስራ የተመረጡ ሊሆኑ ይችላሉ የእርሷ እና የዳዊት ፅጌ (ስለሱ አንድ ቀን መፃፌ አይቀርም!) ለሙያችው ያላቸው ክብር እና እስከ አቅማቸው የሰማይ ንጣፍ ድረስ በፍፁም ጥንቃቄ እና ብቃት የሚከውኑት ነገር ዝሆን በጭንቅላቱ መቆም የሚችል እንስሳ ነው ከሚለው በላይ ይደንቀኛል።

እድል ደግሞ በጣም ትለያለች፤ ስታለቅስ አለም የተከፋች ፣ ስትስቅ አለም የሞላላት ፣ ስትቆጣ አለም የነደደች እስኪመስልህ ነው የቲቪህ መስታወት ላይ ገዝፋ ብቅ የምትለው የተሰጠሽን ጥበብ በእጅጉ የሴትነት ባህሪሽ አጅበሽ ጨዋነትሽ የስርአትን መዝሙር እየዘመረ ላሳየሽን ፊልሞችሽም ሆነ ማንነትሽ እጅ ነስተናል።

የአለምን ሴቶች እወድ ዘንድ ሁሉ እንዳንቺ እንዲሆኑ አብዝቼ እመኛለሁ።

Via ፕሮፌሰር ሄኖክ አረጋ

😭
21/02/2024

😭

06/02/2024
21/12/2023

Address

Dire Dawa

Telephone

+251948593841

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Meriba production Dire Dewa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share