Harsis

Harsis Providing fast and real information to the public is our main vision

09/06/2024

ተፈላጊ ወንጀለኛ

በአፋር ክልል በሎጊያ ከተማ፣ በትናንትናው እለት ከቀኑ አስራ አንድ ሰአት አካባቢ ፣ በተለምዶው ፒያሳ ሙሳ ሐኒድ ምግብ ቤት ጀርባ ላይ፣ የፍራፍሬ ነጋዴ የሆነችው ነጃት እንድሪስን ፣ በድንገ...
09/06/2024

በአፋር ክልል በሎጊያ ከተማ፣ በትናንትናው እለት ከቀኑ አስራ አንድ ሰአት አካባቢ ፣ በተለምዶው ፒያሳ ሙሳ ሐኒድ ምግብ ቤት ጀርባ ላይ፣ የፍራፍሬ ነጋዴ የሆነችው ነጃት እንድሪስን ፣ በድንገት ማንነታቸው በማይታወቁ ግለሰቦች ፣ ከመኖሪያ ቤቷ ወደ ስራ ቦታ በመሄድ ላይ እያለች፣ በድንገት ታፍና ተወስዳ ለግዜው የት እንዳለች በማይታወቅ አካባቢ ተሰውራ ትገኛለች። ነጃት እንድሪስ ባለትዳርና የልጆች እናት ስትሄን፣ ገና ስራ ሰርታ ያልጠገበች ወጣት ልጅ ስትሆን፣ ወላጅ እናቷ በአሁን ሰአት ራሷን በመሳት እያለቀሰች ትገኛለች፣ ታጋች ነጃት እንድሪስ አንድ ግዜ በስልክ ደውለው ከቤተሰቦቿ ጋር ፣ ተገናኝታ ለቅሶ በተሞላበት ስሜት ራሷን የት እንዳለች ለማወቅ ተቸግራ ትገኛለችና ፣ በሎጊያ ከተማና በሰማራ ከተማ ኬላ ላይ ያላችሁ ፖሊሶች እንደዚህ አይነት ከባድ ወንጀለኞችን በቀላሉ ለመቆጣጠር ሲባል ከአካባቢው ውጭ ያሉ አዲስ ተሽከርካሪዎችን ሀይሉክስ፣ስቴሽንና ኮብራ የመሳሰሉ በተለይ የአዲስ አበባና የትግራይ ሰሌዳ ተሽከርካሪዎችን መስታወታቸው ሙሉ በሙሉ በእስቲከር የተለጠፉ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት ፍተሻ እንዲደረግባቸው ይገባል፣ ምክኒያቱም አንድ ሰው አግተው በሚወስዱበት ሰአት በመኪናው ውስጥ ለረጅም ደቂቃዎች ራሱን የሚስት መርፌ ስለሚወጋ ፌንት ተቅሎ መኪናው ውስጥ ስለሚተኛ ኬላ ላይ በፍተሻ ደረጃ ቀላል የሆነ መንገድ በመሆኑ በዚህ አጋጣሚ ኬላ ላይ ፍተሻ የምታደርጉ ፖሊሶችና እንዲሁም ትራፊክ ፖሊሶችም ጭምር በዚህ አይነት መንገዶች ንፁሃን ግለሰቦች ታግተው እንዳይወሰዱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስላለው እባካችሁ ይህንን መልዕክት አንብባችሁ ለሌሎችም ሼር በማድረግ ላልሰሙት እንዲሰሙ በአክብሮት እንጠይቃለን።

በምስሉ ላይ የምትመለከቷት ልጅ ሐናን ቃሲም ትባላለች፣ የምትኖረው አረብ አገር ሲሆን የምትሰራው ስራ በቲክቶክ 44.1K follower ባላት የቲክቶክ አካውንቷ አረብ አገር የሚገኙ ሴቶች እህ...
01/06/2024

በምስሉ ላይ የምትመለከቷት ልጅ ሐናን ቃሲም ትባላለች፣ የምትኖረው አረብ አገር ሲሆን የምትሰራው ስራ በቲክቶክ 44.1K follower ባላት የቲክቶክ አካውንቷ አረብ አገር የሚገኙ ሴቶች እህቶቻችንን በቲክቶክ እናዳድራለን እያለት ሙስሊም እህቶቻችንን በእስልምና መንገድ እንዲወጡና ከዚያም አልፎ ተርፎ ሴቶች እህቶቻችን እውነት እየመሰላቸው ቲክቶክ ላይ በርካታ ወንዶች ስም እየቀያየሩ በተለያዩ ስሞች ሴቶችን እየሸወዱና አረብ አገር ደክመው ሰርተው ያገኙትን ገንዘብ እውነተኛ ትዳር እየመሰላቸው ተጋባን ብለው የሚልኩላቸውን ገንዘብ እየበሉባቸውና እንዲሁም ክህደት እየፈፀሙ በርካታ እህቶቻችን ለአእምሮ በሽታ እየተጋለጡና ራስን እስከማጥፋት ደረጃ እንዳለሁም በመረጃ ተረጋግጧል ። በዚህ መሠረት ሌሎች ሴት እህቶቻችን ከእንደዚህ አይነቶች መሰል ተግባራቶች ገንዘብ ለማግኜት ብለው ፎሎና ላይክ ሼር እንዲበዛላቸው ሲሉ የሚጠቀሙበት ዘዴ ስለሆነ እራሳችሁን እንድትጠብቁና እንድትጠነቀቁ እናሳስባለን።

07/04/2023
በአፋር ክልል በሎጊያ ከተማ ትናንትና የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ እስካሁን ድረስ ምን ያህል ሰው እንደወሰደ በውል ባይታወቅም የሶስት ሰው ህይወት ማለፋቸውና አስክሬናቸውም መገኜቱን በአካባቢው ለመመ...
15/08/2022

በአፋር ክልል በሎጊያ ከተማ ትናንትና የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ እስካሁን ድረስ ምን ያህል ሰው እንደወሰደ በውል ባይታወቅም የሶስት ሰው ህይወት ማለፋቸውና አስክሬናቸውም መገኜቱን በአካባቢው ለመመልከት ችለናል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዋሽ ወንዝ እስካሁን ድረስ በአይነቱ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ የሆነ ጎርፍ አስከትሎ ከአዲስ አበባ ወደ ጂቡቲ የሚወስደውን የዋና አስፋልት መንገድ ሀይል አድርጎ በመጣው ጎርፍ በመሸርሸሩ ተሽከርካሪዎች በአሁን ሰአት እንደልባቸው መተላለፍ ባለመቻላቸው የሎጊያና የሰመራ አገናኝ መንገድ ክራውድድ በመሆኑ ለትራፊክ አደጋ እያጋለጠ በመሆኑ መንግስትም ሆነ የሚመለከተው አካል ጉዳዩ አሳሳቢ በመሆኑ በአስቸኳይ ትኩረት እንዲሰጠውና ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ከዚህ የባሰ የጎርፍ አደጋ እንዳይከሰት ከወዲሁ አፋጣኝ የሆነ መፍትሄ እንዲደረግለት ያሸዋል በማለት ከአሁኑ እናሳስባለን።

18/05/2022

ይህ ፅሁፍ ረጂም ቢሆንም ሳያነቡት እንዳያልፉት
---------------- // ------------------ // ------------------
በአባቶቻችን እና በአያቶቻችን ዘመን በእርግጥም ባልሰለጠነው ዘመን በርካታ የሆኑ የሀይማኖት ትምህርቶችና ግንዛቤዎችም ባይኖሩም በእነሱ ዘመን የመተሳሰብ፣የመቻቻል፣የአንድነትና የማህበራዊ አኗኗር ዘይቤዎቻቸው ለመጭው ትውልድ ከፍተኛ የሆነ አሻራ አሳርፈው እንዳለፉ ይታወቃል። ነገር ግን እኛ ግን የእነሱን አርአያ መሆን እንኳን ባንቺል እርስ በራሳችን ለምን ጥላቻን እንፈጥራለን? ትናንት ኢንጂነር ተብሎ የተማረው ሰው የሰው ህይወት ሲያጠፋ ያውም የሚወዳትን የትዳር አጋሩን ነስፍ ሲያጠፋ ዛሬ ደግሞ ዶክተር ተብላ ሰባት አመት ሙሉ ተምራ የመጨረሻዋ ራዕይ ራሷን በማይሆን ነገር ከፎቅ ላይ በመውደቅ ህይወቷን አጠፋች የሚል ወሬ ስንሰማ በጣም ያሳዝናል። ይህ ሁሉ ግን በዋነኛነት የሀይማኖት ግንዛቤ ባለመኖሩ ይመሥለኛል። ማንኛውም ሀይማኖትም ቢሆን በቁዱስ መፅሀፍ ላይ የሰውን ህይወትም ሆነ የራሱን ህይወት እንዲያጠፋ አይፈቅድም። በስልጣን ላይ እያሉ፣ሰውን በማጭበርበርም ሆነ በተለያዩ መንገዶች የሰውን ገንዘብም ሆነ ንብረት መዝረፍ በፈጣሪ በኩል ትልቅ ወንጀል ነው ከባድ ነው ያስጠይቃል ትኩረት እንስጥ እንደሰው እናስብ ለማይረባ ኑሮ በማለት የዛኛውን የዘላለማዊ ኑሮአችንን ባናበላሸው መልካም ነው ብየ አምናለሁ። እባካቹህ ሙስሊም ኦርቶዶክስና የሌሎች ሀይማኖቶች ተከታዮች ሁሉ ዘወር ብለን ያለፉትን የአያቶቻችንን ባህል፣ኑሮና መልካም ስራዎቻቸውን መለስ ብለን እናስብና የእነሱን ስርአት በመከተል አንድነታችንን እናጠናክር ፍቅርን እንፍጠር እንደሰው የማያስቡ አንዳንድ ሰው መሠል ሰይጣኖችን መከተል የለብንም። ሁሉም ነገር ያልፋል በመጨረሻም ላይ ግን ስንሞት ማንም ወዳጂም ሆነ ቤተሰብ ተከትሎን ማንም ከሞት የሚያስጥለን የለም። ለእኛ የሚጠቅመን ትልቁ ነገር በእዚች ምድር ላይ መልካም ስራችን ብቻ ነው ፈጣሪ ጋር የሚያገናኜን ለእዚያኛው አለም ስንቅ የሚሆነን መልካም ስራችን ብቻ ነው። አሁን በቃ ንቁ የተኛቹህ ከባለፈው ስህተታችን ታርመን የወደፊት ቀሪውን ህይወታችንን ጥሩ ስራ እየሰራን እና ፈጣሪያችንን እየለመንን ዱዓ(ንስሃ) በመግባት ለራሳችን፣ የቤተሰቦቻችን እና ለአገራችን በማሰብ ካለፉት መጥፎ ስራዎች እየተማርን ለቀጣይ ትውልድ ደግሞ የሚወለዱት ልጆቻችን ከእኛ መልካም ስራዎችን እንዲወርሱ ሁላችንን የበኩላችንን ሀላፊነት እንድንወጣ ለሌሎች ወንድሞቻችን እና ወንድሞቻችን ይህንን ጠቃሚ ትምህርቶችን ሼር በማድረግ የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙ የበኩላችንን ድርሻ እንወጣ በማለት መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።

የቀድሞው የተባበሩት አረብ ኢምሬት ንጉስ ሼይክ ኸሊፋ ኢብን ዛይድ በዛሬው ዕለት በ70 ዓመታቸው ከዚህ አለም ተለይተዋል። ሼይክ ኸሊፋ ኢብን ዛይድ በጣም ጥሩ ሰው እና እንዲሁም ለአገራቸው ከ...
13/05/2022

የቀድሞው የተባበሩት አረብ ኢምሬት ንጉስ ሼይክ ኸሊፋ ኢብን ዛይድ በዛሬው ዕለት በ70 ዓመታቸው ከዚህ አለም ተለይተዋል። ሼይክ ኸሊፋ ኢብን ዛይድ በጣም ጥሩ ሰው እና እንዲሁም ለአገራቸው ከፍተኛ ለውጥና እድገት ያመጡ ታላቅና ተወዳጅ ንጉስ ነበሩ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በዱባይ በዛሬው እለት ለ40 ቀን የሚቆይ የሀዘን አዋጅ አውጥተዋል።

የኢትዮጲያ ኤሌትረክ አገልግሎት         ------------------------------------------የሰሜን ምስራቅ ሰመራ ሪጅን ቅርንጫፍ መ/ቤት----------------------...
26/03/2022

የኢትዮጲያ ኤሌትረክ አገልግሎት
------------------------------------------
የሰሜን ምስራቅ ሰመራ ሪጅን ቅርንጫፍ መ/ቤት
--------------------------------------------------------------
የአፋር ህዝብ በሰሜን ትግራይ በኩል የተከፈተበትን ጦርነት ምክኒያት የተለያዩ የትግራይ አጎራባች ወረዳዎች ውስጥ የሚኖሩ የአፋር ህዝብ በአሁን ሰአት በጦርነቱ ምክኒያት ቤትና ንብረታቸውን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ጭምር በተሰነዘረባቸው ጦርነት ምክኒያት በአሁን ሰአት በሰመራና ሎጊያ አካባቢዎች ተፈናቅለው በመምጣት በመጠለያ ላይ ሲገኙ፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጲያ ኤሌትሪክ አገልግሎት የሰመራ ሪጅን ቅርጫፍ አገልግሎት ሰጭ የሚባለው መስሪያ ቤት በሎጊያ ከተማ በየመኖሪያ ቤቱ እየተዘዋወሩ ያለምንም መረጃ በስህተት የመብራት ውዝፍ እዳ ባለመክፈልዎ የመብራት አገልግሎት መጠቀም ስለማይችሉ በማለት መብራት እየቆረጡ አስቸግረዋል። ልብ ይበሉ በአሁን ሰአት ሙቀት የጀመረበት ወራት በመሆኑ የተፈናቃዩ ቁጥር እየጨመረ በመጣ ቁጥር የነበረው ሙቀት በዚያ ልክ እየጨመረ በመምጣቱ ለአፋር ህዝብ ደግሞ በአሁን ሰአት በዚህ ላይ ሁለኛ ጦርነት እንደተከፈተበት ይቆጠራል። በሰመራ መብራት ኃይል መ/ቤት ውስጥ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ ሙስና የተስፋፋበት ሲሆን ግቦ ተቀብለው በሎጊያ ከተማ የመብራት ኃይልን መኪናዎች በየጫት ቤት እየተንቀሳቀሱበት በመሆኑ በተደጋጋሚ አዘውትረን ተመልክተናል። መንግስት በአሁን ሰአት በሰመራ ሪጅን መብራት ኃይል ቅርንጫፍ ላይ አስፈላጊውን ሪፎርም ሊያደርግ ይገባል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harsis posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Harsis:

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share