
07/10/2025
መዲናችን ዱራሜ እና መታወቂያ ካርዳችን ሐምበሪቾ ተራራ በነገው ዕለት ትልቅ እንግዳ ያስተናግዳሉ!!!!
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚነስትር፣ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ፕሬዚዳንት፣ የኖቤል ተሸላሚ፣ የህዳሴ ግድብን በቃሉ መሠረት የፈጸመ፣ በሶማሊያ በረሃ ሌላ ድንቅ ታሪክ ያስጀመረ፣ የመደመር መንግስት ቀማሚ እና መሪ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ነገ ወደ ዞናችን ከተፍ ይላሉ!!!
እሳቸው በመጡ ማግስት ሚዲያዎች፣ ኤምባሲዎች፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ጋዜጣዎች እና መሰል ተያቢዎች ስለ ከምባታ ጻፉ/ስለ ከምባታ አወሩ!!!
እሳቸው ከሙጡ ማግስት ጀምሮ መላው የዞናችን ሕዝብ በአንድነት በመቆም ከዞናችን መሪዎች ጋር በማበር ሐምበሪቾ ላይ ሌላ ታሪክ ሌላ የቱሪስትን ልብ የሚያማልል ድንቅ ታሪክ ተሰራ!!!
ይሄ ሁሉ በእግዚአብሔር ሰዓት እና ጊዜ ሆነ!!!
እነሆ ነገ እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶች እና ልጆች በሙሉ የሰላም ማሳያ የሆነውን አረንጓዴ ሳር ይዛችሁ በመዲናችን ዱራሜ ከተማ እንድታጥለቀልቁና ጠቅላይ ሚኒስተራችንን ዶ/ር አብይ አህመድን በክብር እንድንቀበል ይሄ የከበረ ጥሪያችን ነው።
ነገ ማነስ አይቻልም...እስካሁን የኢትዮጵያ መሪዎች ባላከበሩን መጠን ያስከበረንን ዶ/ር አብይ አህመድን በየስፍራው በደማቁ እንድንቀበል ይሁን!!!!
እግዚአብሔር ሕዝባችንን ይባርክ!!!
Ethiopia Land of Origins Binye Alex Visit Kambata