26/09/2025
የመስቀል ደመራ በዓል አንድነትና ፍቅር የሚገለፅበት ለሰው ልጆች ሁሉ ተምሳሌት ነው - ክቡር ከንቲባ አቶ ታረቀኝ ተስፋዬ!!
በዱራሜ ከተማ አስተዳደር የመስቀል ደመራ በዓል የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በተለያዩ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች የእምነቱ ተከታዮችና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተከበሯል።
በሥፍራው በመገኘት መልዕክት ያስላለፉት የዱራሜ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ታረቀኝ ተስፋዬ የመስቀል ደመራ በዓል አንድነትና ፍቅር የሚገለፅበት ለሰው ልጆች ሁሉ ተምሳሌት ነው ብለዋል።
በሀገራችን ብሎም በከተማችን ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት የጥምቀትና የደመራ በዓል ከሃይማኖታዊ ዐዓል ባሻገር የሁሉም ቤተ እምነቶች የጋራ በዓል በሚመስል መልኩ በአንድነትና በጋራ ያለ አንዳች ልዩነት ፍጹም ፍቅር በተሞላበት ሁኔታ የሚከበር መሆኑ ልዩ መገለጫ እንደሆነም ገልፀዋል።
የእንጨቱ መሰብሰብና የደመራው መደመር በአንድ ሀሳብ ለፀሎት፣ ለፍቅር፣ ለልማት፣ ለሰላምና ለአንድነት መትጋት እንዳለብን የሚያስተምር ነው ያሉት ክቡር ከንቲባ ሁላችን በመገንዘብ ለጋራ አላማ በጋራ መቆም አለብን ብለዋል።
በመርሐ-ግብሩም የከምባታ ጠምባሮና ሀላባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ ሚካኤል ታደሰ፣ የቤተ እምነቱ መሪዎችን ጨምሮ መላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን የተለያዩ የኃይማኖቱ ክዋኖች በማድረግ ተጠናቅቋል።