24/08/2026
ራዕይና ተልዕኮን ወደ ተግባር የቀየረ ድንቅ መሪ!!!
በአመራርና አስተዳደር ሳይንስ ራዕይ (Vision) ማለት «ወደፊት የት መድረስ እንፈልጋለን?» ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ፣ በግልፅ ታቅዶ እውን የሚደረግ ተስፋ ሰጪ የመዳረሻ ፍኖተ ካርታ ነው። ተልዕኮ (Mission) ደግሞ «ለምን ወደ ሀላፊነት መጣን? አሁንስ ምን እየሰራን ነው?» የሚለውን መሠረታዊ ዓላማና የዕለት ተዕለት የትጋት መንገድን ይገልፃል።
ይህንን ሳይንሳዊ የአመራርነት ዋና ፅንሰ ሃሳብ ወደ መሬት ከማውረድና ወደ ትግበራ ከመቀየር አንፃር ስናይ፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው ያሳዩት ቁርጠኛና ብቁ የአመራርነት ሚና ሁነኛ ማሳያ ነው።
በግልፅ የተደራጀ ራዕይ፦ ዶ/ር እንዳሻው ክልሉን መምራት ሲጀምሩ ግልፅና አቅጣጫ ጠቋሚ ራዕይ በመሰነቅ ጀምረዋል። ክልሉን ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ በሁሉም ዘርፎች የላቀ ውጤት የሚያስመዘግብና ለሌሎችም «የተሞክሮ ማዕከል» የሚሆን ሞዴል ክልል የማድረግ ራዕያቸው ይኸው በተጨባጭ የታየ እውነታ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ ክልሉን ከዕዳ ወደ ምንዳ ማሸጋገር አንዱ ነው፡፡
🎯 ተልዕኮን በተግባር መተርጎም፦ የተሰጣቸውን ህዝባዊ ሀላፊነትና ተልዕኮ በብቃት በመምራት፣ የአመራር መዋቅሩን አስተባብረው የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ በመመለስ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ የህዝብ አገልጋይነት ባህሪ መላበሳቸው አንዱ ማሳያ።
💎 የዶ/ር እንዳሻው ጣሰው የብቁ አመራርነት ልዩ ባህሪያት፦
* ተግባር ተኮር ስብዕና፦ ራዕይን በወረቀት ላይ ማስቀመጥ ብቻ ሳይሆን፤ ወደ መሬት በማውረድ መቆጠርና መለካት በሚችሉ ስኬቶች ማረጋገጥ።
* ጽናትና ቁርጠኝነት፦ አላስፈላጊ ሀሰተኛ ወሬዎችንና የፀረ-ልማት አጀንዳዎችን በልማት፤ በሰላምና የፀጥታ ስራዎች መመከት።
* አካታች መሪነት፦ ህዝብንና አመራሩን አስተባብሮ የጋራ ህልምን በጋራ ክንድ የመገንባት ጥበብ።
ራዕይና ተልዕኮን አጣምሮ የያዘ ብቁ መሪ ሲኖር; ሁልጊዜም ውጤቱ ዘላቂ ብልፅግናና እድገት ነው!