Prophet Nebiyu Fiseha

Prophet Nebiyu Fiseha Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Prophet Nebiyu Fiseha, TV Network, Gambela.

01/03/2025
11/02/2025

በእውነት ብር የሚወጣበት፥ ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ።
2፤ ብረት ከመሬት ውስጥ ይወሰዳል፤ መዳብም ከድንጋይ ይቀለጣል።
3፤ ሰው ለጨለማ ፍጻሜን ያደርጋል፤ የጨለማውንና የሞት ጥላን ድንጋይ እስከ ወሰኑ ድረስ ይፈላልጋል።
4፤ ሰው ከሚኖርበት ርቀው መውረጃ ይቈፍራሉ፤ ከሰውም እግር ተረሱ፥ ከሰዎችም ርቀው እየተንጠለጠሉ ይወዛወዛሉ።
5፤ እንጀራ ከምድር ውስጥ ይወጣል፤ በእሳትም እንደሚሆን ታችኛው ይገለበጣል።
6፤ ድንጋይዋ የሰንፔር ስፍራ ነው፥ የወርቅም ድቃቂ አለው።
7፤ መንገድዋን ጭልፊት አያውቀውም፥ የአሞራም ዓይን አላየውም።
8፤ የትዕቢት ልጆች አልረገጡአትም፥ ደቦል አንበሳ አላለፈባትም።
9፤ ሰው ወደ ቡላድ ድንጋይ እጁን ይዘረጋል፥ ተራራውንም ከመሠረቱ ይገለብጣል።
10፤ ከድንጋይ ውስጥ መንዶልዶያ ይወቅራል፤ ዓይኑም ዕንቍን ሁሉ ታያለች።
11፤ ፈሳሹም እንዳይንጠባጠብ ይገድባል፤ የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል።
12፤ ነገር ግን ጥበብ የምትገኘው ወዴት ነው? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው?
13፤ ሰው መንገድዋን አያውቅም፤ በሕያዋን ምድር አትገኝም።
14፤ ቀላይ። በእኔ ውስጥ የለችም ይላል፤ ባሕርም። በእኔ ዘንድ የለችም ይላል።
15፤ በምዝምዝ ወርቅ አትገኝም፥ ብርም ስለ ዋጋዋ አይመዘንም።
16፤ በኦፊር ወርቅ፥ በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም።
17፤ ወርቅና ብርጭቆ አይወዳደሩአትም፥ በጥሩ ወርቅም ዕቃ አትለወጥም።
18፤ ስለ ዛጐልና ስለ አልማዝ አይነገርም። የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍ ይልቅ ይበልጣል።
19፤ የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን አይተካከላትም፥ በጥሩም ወርቅ አትገመትም።
20፤ እንግዲያሳ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው?
21፤ ከሕያዋን ሁሉ ዓይን ተሰውራለች፥ ከሰማይ ወፎች ተሸሽጋለች።
22፤ ጥፋትና ሞት። ወሬዋን በጆሮቻችን ሰማን ብለዋል።
23፤ እግዚአብሔር መንገድዋን ያስተውላል፥ እርሱም ስፍራዋን ያውቃል።
24፤ እርሱም የምድርን ዳርቻ ይመለከታል፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።
25፤ ለነፋስ ሚዛንን ባደረገለት ጊዜ፥ ውኆችንም በስፍር በሰፈረ ጊዜ፥
26፤ ለዝናብም ሥርዓትን፥ ለነጐድጓድ መብረቅም መንገድን ባደረገ ጊዜ፥
27፤ በዚያን ጊዜ አያት፥ ገለጣትም፤ አዘጋጃትም፥ ደግሞም መረመራት።
28፤ ሰውንም። እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል ነው አለው።

❤
08/03/2024

05/11/2023
29/10/2023

እግዚአብሔር ድል እየሰጠን ነው

   (Dec 7, 2019)  (February 12, 2021)  (June 5, 2021)  ቾ (September 14, 2021)★ በ3 ዓመታት ውስጥ ብቻ እነዚህን ታላላቅ የእግዚአብሔር አገልጋዮች...
04/10/2023


(Dec 7, 2019)
(February 12, 2021)
(June 5, 2021)
ቾ (September 14, 2021)

★ በ3 ዓመታት ውስጥ ብቻ እነዚህን ታላላቅ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ካገለገሉት ጌታ ጋር እንዲሆኑ ዘንድ ውደ እርሱ ተወስደዋል!!🙇‍♂️🔥☝️

ወንጌላዊ ሬይንሃርድ ቦንኬ: በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2000-2009 ብቻ እንኳ በዘለቀ አገልግሎታቸው ከ 57 ሚሊዮን ሰዎች በላይ በህይወት ዘመን አገልግሎታቸው ደግሞ ከ75 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ወደ እግዚአብሄር መንግስት መጨመር ምክንያት የሆኑ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ናቸው።

ሐዋርያው ፍሬድሪክ ኬሲ ፕራይስ: በእጅጉ ቀንሶ የነበረውን በአሜሪካ የሚገኙ ክርስቲያኖች ቤተክርስቲያን የመካፈል ፍላጎት የእምነት ህይወትን ከመንፈስ ቅዱስና ከእግዚአብሄር ቃል ጋር በመጣመር በማስተማር ብቻ በየሳምንቱ 28 ሺህ ሰዎችን በአንድ አገልግሎት/Service ያስተማር የነበረ በተጨማሪም በቴሌቪዥን አገልግሎቱ ምድርን በእምነት ህይወት አስተምዕሮ ያናወጠ እንዲሁም ለተወደደ የእግዚአብሔር ሰው ቲቢ ጆሽዋ በኢማኑኤል ቴሌቪዥን አገልግሎት ለመጀመር ቀስቃሽ የነበረ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ነው!!

ነብይ ቲቢ ጆሽዋ: አስደናቂ በሆኑ በትንቢት ፣ በፈውስ፣ በነፃ መውጣትና በበጎ አድራጎት ስራዎች አለምን ልዩ በሆነ የመንፈስ ቅዱስ አሰራር ያገለገለ ፣ ለ 15 ዓመታት በዘለቀ የቴሌቪዥን አገልግሎት ሚሊየኖችን በክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌል የደረሰ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ነው።

መጋቢ ዴቪድ ዮንጊ ቾ: በቀን 24 ሰዓታትና በሳምንት 7 ቀናት ያልተቋረጠ የፀሎት ሰንሰለት፣ በአውሮፓ ብቻ ከ 10 ሺህ በላይ ቤተክርስቲያን የተከሉ፣ የኮሪያ ፔንቴኮስታል ሪቫይቫል ውጤት የሆኑ፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ጉባኤ በአንድ አገልግሎት/Service የሚያገለግሉ፣ በሴል ግሩፕ / በቤት ውስጥ አገልግሎት ለ46 ዓመታት ተፅዕኖ የፈጠሩ፣ በአገልግሎታቸው የሩቅ ምስራቅን የክርስትና ቅርስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የቀየሩ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ናቸው!!!

የኤልያስ መወሰድ ለኤልሳዕ የአዲስ አገልግሎት በር መከፈት ምክንያት ነበር!!!!
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ወጣቶች ጊዜ የለንም!!! በፊልም፣ በሾው፣ በመዝናኛ፣ በእግር ኳስ ጊዜያችንን ምናጠፋበት ወቅት አይደለም!!! 🤷‍♂️
3 እና 4 ሰዓታት ፊልም በማየት፣ 8 ሰዓታት በመተኛት፣ 1:30 ሰዓት ኳስ በማየት ሪቫይቫሊስ መሆን ፈፅሞ አይቻልም!!! 🙅‍♂️
ቅባት ዋጋ ያስከፍላል Association ሳይሆን Separation ይፈልጋል!!!
ፀልዩ!!! ክብርማ አለ‼🔥☝️🙇‍♂️🙇‍♂️
የሚባክን ግዜ የለም

 ........ዓለም አቀፉ ወንጌላዊ ራይንሓርድ ቦንኬ በአዋሳ ከተማ እንደሚያገለግል በስፋት መነገር በጀመረ ጊዜ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ሪፖርተር ነበርኩ።  ይህ ክንውን...
04/10/2023

........

ዓለም አቀፉ ወንጌላዊ ራይንሓርድ ቦንኬ በአዋሳ ከተማ እንደሚያገለግል በስፋት መነገር በጀመረ ጊዜ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ሪፖርተር ነበርኩ። ይህ ክንውን እንደዜና ጋዜጠኝነቴን እንደ ፕሮግራም ደግሞ መንፈሳዊነቴን የሚነካ በመሆኑ ለመሄድ አላመነታሁም።
አመሻሽ ላይ ጤፍ በሚያስለቅመው የባውዛ ብርሃን ጀማ ስብከቱ ተጀመረ። ገና በመጀመሪያው ቀን ገና ሳይመሽ አደባባዩ ከአምሳ ሺሕ በማያንስ ሕዝብ ተጨናንቆ ማየቴን ማስታወሻዬ ላይ ጽፌአለሁ። መድረኩ አካባቢ ላሉ አስተናባሪዎች ማንነቴን አሳወቅሁ። እነርሱም ፊት ወንበር ላይ የሚያስቀምጠኝን የይለፍ ወረቀት ሰጡኝ።
የተለመደው ዝማሬና አምልኮ ተካሄደ። የሲዳምኛ መዝሙሮች ልብን ያሞቃሉ። ራይንሃርድ ቦንኬ የድምፅ ማጉያውን ጨበጠ። የሚናገረው ይስባል። በቃላቱ ውስጥ ፍቅር ሙሉ ነው። ከፍርድ ይልቅ ጸጋ ላይ ያተኩራል። እግዚአብሔርን አስፈሪና ቁጡ ሳይሆን ርኅሩኅና አፍቃሪ አድርጎ ይስለዋል። ብዙ ታላላቅ ሰባኪያንን ሰምቻለሁ። በርግጥም ይሰብካሉ። ቦንኬ ደግሞ እነርሱ የሰበኩትን ያብራራል። ይኸው ነው። በነዚያ ቀናት በሺዎች የሚቆጠሩ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሲፈልሱ በርካታ ሕሙማንም ከነበረባቸው ደዌ ሲፈወሱ ዐይቻለሁ። ቦንኬ የወንጌል ዕቃ ዕቃ የሚጫወት ሰው አልነበረም። አይቼ የማላውቀውን የቃሉን ሌላ ገጽታ አስተዋልኩ። እነሆም ከዚያች ቀን በኋላ ተመልሼ እንደዱሮው መሆን አልቻልኩም።
እንዳናግረው ቀጠሮ ተይዞልኝ የነበረ ቢሆንም ያንን የሕዝብ ማዕበል ተሻግሬ ሆቴሉ ለመድረስ ሌላ ግማሽ ሰዓት አስፈለገኝ። ስደርስ ረዳቱ የሆነ ኬንያዊ አገኘሁ።
“ቢረፍድብኝም ደርሻለሁ!”
“አዝናለሁ” አለ ሳያመነታ።
“እንዴት”
“ለጸሎት ተንበርክኳል፤ ቶሎም አይጨርስም!”
በዘመኔ ሁሉ እንደ ራይንሐርድ ቦንኬ ዓይነት ሰባኪ አላየሁም። ነፍሱ በሰላም ዐርፋለች!
አለማየሁ ማሞ

01/10/2023

Address

Gambela

Telephone

+251912323101

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prophet Nebiyu Fiseha posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Prophet Nebiyu Fiseha:

Share

Category