LIGHT MEDIA 30

LIGHT MEDIA 30 WELL CAME TO LIGHT MEDIA 30!

''የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር ዛሬን እንተጋለን''
#ማስታወቂያ ለማሰራት ከፈለጉ በ ያውሩን
The sun will rise again and I will try again.
(12)

Yana Tafesse (Engineer) Contact:-

ባርሴሎና ሮድሪን ከማንቸስተር ሲቲ ለማስፈረም ተስማማ ባርሴሎና ስፔናዊውን አማካይ ሮድሪን ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል። ባርሴሎና ቀደም ብሎ 45 ሚልዮን ዩሮ አቅርቦ ውድቅ ቢደረግበትም...
17/08/2026

ባርሴሎና ሮድሪን ከማንቸስተር ሲቲ ለማስፈረም ተስማማ

ባርሴሎና ስፔናዊውን አማካይ ሮድሪን ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል።

ባርሴሎና ቀደም ብሎ 45 ሚልዮን ዩሮ አቅርቦ ውድቅ ቢደረግበትም፣ ዳግም ካቀረበው 60 ሚልዮን ዩሮ በተጨማሪ ብቃቱ እየታየ የሚጨመረውን በማካተት በድምሩ ያቀረበው የ76.5 ሚልዮን ዩሮ ጥያቄ በማንቸስተር ሲቲ ተቀባይነትን አግኝቷል።

ያለፉትን ሰባት ዓመታት በማንቸስተር ሲቲ ያሳለፈው ሮድሪ፣ በቆይታው የአውሮፓ ሻምፕየንስ ሊግ እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ 13 ዋንጫዎችን ከሲቲ ጋር አሸንፏል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ እና ጥገና 108 ቢሊዮን ብር ማውጣቱን አስታወቀየኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ...
15/08/2026

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ እና ጥገና 108 ቢሊዮን ብር ማውጣቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ እና ጥገና 108 ቢሊዮን ብር ማውጣቱን አስታወቀ ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. (አሐዱ ሬዲዮ) ፡- በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 24 ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የተለያዩ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ለማከናወን 108 ቢሊዮን ብር ማውጣቱን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለአሐዱ ሬዲዮ አስታውቋል።

አስተዳደሩ 105 ኪሎ ሜትር ከባድ የኮንክሪት መንገዶችን፣ 12.7 ኪ.ሜ.

የፌዴራል ዋና ዋና መንገዶችን እና 580 ኪ.ሜ.

አዳዲስ እና የፍጥነት መንገዶችን ጠግኗል።

የመንገድ ደረጃዎችን ማሻሻሉ ተገልጿል።

Source: Ahadu Radio

☀️🏢መስኮቶች በራሳቸው ኤሌክትሪክ የሚያመነጩበት ዘመን መጣ!🌟​የደቡብ ኮሪያ ሳይንቲስቶች የከተሞቻችንን ተራ የሕንፃ መስተዋቶች ሳይለወጡ እና ውበታቸው ሳይነካ ኃይል ማመንጨት የሚያስችል ግል...
14/08/2026

☀️🏢መስኮቶች በራሳቸው ኤሌክትሪክ የሚያመነጩበት ዘመን መጣ!

🌟​የደቡብ ኮሪያ ሳይንቲስቶች የከተሞቻችንን ተራ የሕንፃ መስተዋቶች ሳይለወጡ እና ውበታቸው ሳይነካ ኃይል ማመንጨት የሚያስችል ግልጽ የሶላር መስተዋት ቴክኖሎጂ (Transparent Solar Window Technology) አዳብረዋል።

🏛​ከUNIST፣ ከኮሪያ ዩኒቨርሲቲ፣ ከKIST እና ከኮሪያ ኤሮስፔስ ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ የምርምር ቡድኖች ግልጽነታቸውን ጠብቀው ኃይል ማመንጨት የሚችሉ የሶላር ሴሎችን ፈጥረዋል. ከዚህ ቀደም የነበሩ ግልጽ የሶላር ቴክኖሎጂዎች ቅልጥፍናን ለመጨመር ሲሉ ግልጽነታቸውን ያጡ (የደበዘዙ) ነበር፤ አሁን ግን አንደኛው ስሪት ከ75 በመቶ በላይ የሚታይ የብርሃን ማስተላለፊያ አቅም (Visible Light Transmittance) በማሳየት ይህንን ትልቅ ፈተና ፈትቶታል.

• ​የቴክኖሎጂው ሀሳብ፦ ከተሞች በሙሉ ብርሃን ከማስገባት ውጭ ሌላ ፋይዳ በሌላቸው የግላስ (መስተዋት) ሕንፃዎች የተሞሉ ናቸው. መስኮቶች ኤሌክትሪክ ማመንጨት ከቻሉ፣ ራሳቸው ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ተጨማሪ የጣሪያ ቦታ ሳይፈልጉ የራሳቸውን የኃይል ፍጆታ የተወሰነ አካል መሸፈን ይችላሉ.
• ​ወቅታዊ ደረጃ፦ ይህ ቴክኖሎጂ አሁን ላይ በምርምር እና በፈተና ላይ ያለ እንጂ ገና በዕለት ተዕለት ሕንፃዎች ላይ የተገጠመ አይደለም.
​ግንባታ እና ኃይል ማመንጨት ተጣምረው የሚሄዱበት የወደፊት የኢንጂነሪንግ ምዕራፍ እየተከፈተ ይገኛል።

🚥ማጠቃለያ

"የነገው ግሪን ኢንጂነሪንግ ሕንፃዎች መኖሪያ ብቻ ሳይሆኑ፣ የራሳቸውን ኃይል በራሳቸው የሚያመነጩበት ዘመናዊ ሥርዓት ይሆናሉ!"

etconp

ከጥርስ ቡርሽ እስከ ማንችስተር ሲቲ! — የያብ አርትስ (Yabu Arts) አስደናቂ ድል "ጥበብ መሳሪያ አይመርጥም፤ ለሚጥር ሰው ደግሞ ድንበር የላትም!"በኢንስታግራም እና ማህበራዊ ሚዲያዎች...
14/08/2026

ከጥርስ ቡርሽ እስከ ማንችስተር ሲቲ! — የያብ አርትስ (Yabu Arts) አስደናቂ ድል

"ጥበብ መሳሪያ አይመርጥም፤ ለሚጥር ሰው ደግሞ ድንበር የላትም!"

በኢንስታግራም እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ለየት ባለ መንገድ የጥርስ ቡርሽን በመጠቀም የታዋቂ እግር ኳስ ተጫዋቾችን ድንቅ ስዕል በመሳል የሚታወቀው ኢትዮጵያዊው ወጣት ባለጥበብ ያብ አርትስ (Yabu Arts) ድንቅ አህጉር ተሻጋሪ ታሪክ ሰርቷል!

ያብ አርትስ የማንችስተር ሲቲውን ፈጣን ክንፍ ጀርሚ ዶኩን (Jérémy Doku) በቡርሹ አስማት ሰርቶ ያቀረበ ሲሆን... ታሪኩ እዚህ ላይ አላበቃም!

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ 60 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው የማንችስተር ሲቲ (Manchester City) ኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፅ በጥበቡ እጅጉን በመደመም የስዕሉን ስራ በገጹ ላይ ሼር አድርጎታል።

ይህም ኢትዮጵያዊ ጥበብና ፈጠራ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ግዙፍ ክለብ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በክብርና በኩራት ሲወጣ የመጀመሪያው አጋጣሚ ሆኗል!

ፖስቱም በአጭር ሰዓታት ውስጥ የብዙ ሺህዎችን ትኩረት ስቧል።

ለዚህ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ወጣት ባለጥበብ ያለንን አክብሮት፣ ኩራትና ድጋፍ በኮመንት እና በሼር እንግለጽለት!

እንኳን ደስ አለህ Yabu Arts!

በ933.6 ሚሊዮን ብር  የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮና ግንባታ ሥራ የውል ስምምነት ተፈረመነሐሴ 6/2018 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ.) – የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ...
13/08/2026

በ933.6 ሚሊዮን ብር የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮና ግንባታ ሥራ የውል ስምምነት ተፈረመ

ነሐሴ 6/2018 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ.) – የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ከቢጌታ ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ጋር የ933,609,566.54 ብር የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮና ግንባታ ሥራ የውል ስምምነት ፈርመዋል።

የፕሮጀክቱ ትግበራ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ከምባታ ዞን፣ አንጋጫ ወረዳ የሚከናወን ሲሆን፣ ወጪውም በመንግሥት በሚመደብ በጀት የሚሸፈን ነው።

በውሉ መሠረት ሥራው በ18 ወራት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ የሲቪል ግንባታ ሥራዎችን ጨምሮ የውሃ ቧንቧዎች፣ መገጣጠሚያዎችና የቫልቭ መለዋወጫዎች አቅርቦት፣ እንዲሁም የኤሌክትሮ-ሜካኒካል መሣሪያዎች ግዥና ተከላ ይካተታሉ።

ፕሮጀክቱ በCR-WASH መርሃ ግብር ሥር የሚተገበር ሲሆን፣ በአካባቢው የውሃ አገልግሎትን ለማስፋፋትና ለማሻሻል ያለመ ነው። በተለይም ለሕብረተሰቡ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን በማሳደግ የኑሮ ሁኔታን ለማሻሻል ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።

የሥራው ተቋራጭ ቀደም ሲል በተመሳሳይ የውሃ ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ የሥራ ልምድ ያካበተ መሆኑ ታውቋል።

በውል ስምምነቱ ወቅት ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ፣ ተቋራጩ የተወሰኑትን የጥራት መስፈርቶች በጥብቅ በመከተል ሥራውን በተያዘለት ጊዜ እንዲያጠናቅቅ አሳስበዋል። ፕሮጀክቱ ለሕዝብ ዘላቂ ጥቅም እንዲያስገኝ በሥራ አፈጻጸሙ ላይ ትኩረት እንዲደረግም ገልጸዋል።

ሚኒስቴሩ በበኩሉ የፕሮጀክቱን አፈጻጸም በቅርበት በመከታተል ሥራው በውሉ መሠረት እንዲከናወን እንደሚያደርግ ገልጿል።

የሥራው ተቋራጭም ለተሰጠው የሥራ ዕድል ምስጋና በማቅረብ፣ ፕሮጀክቱን በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ፣ የጥራት መስፈርቶችን በማሟላት ለማጠናቀቅና ለማስረከብ ቃል ገብቷል።

መልካም ጋብቻ ብለናል 👫ጋብቻ የፍቅር የመተሳሰብ የመተዛዘን እና የእውነተኛ ህይወት አንድነት መጀመሪያ ነው።መጪው ዘመንና ጊዜያችሁ በፍጹም ፍቅርና በመተሳሰብ የታነጸ በደስታ በጤናና በበረከት...
12/08/2026

መልካም ጋብቻ ብለናል 👫

ጋብቻ የፍቅር የመተሳሰብ የመተዛዘን እና የእውነተኛ ህይወት አንድነት መጀመሪያ ነው።መጪው ዘመንና ጊዜያችሁ በፍጹም ፍቅርና በመተሳሰብ የታነጸ በደስታ በጤናና በበረከት የተሞላ በማንኛውም የህይወት አጋጣሚ እጅ ለእጅ ተያይዛችሁና ጸንታችሁ የምታልፉበት ይሁንላችሁ ወንድሞች 🙏

በድጋሜ መልካም ጋብቻ መብሩክ !

የኢትዮጵያን አየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ የሚጠብቀው ዘመናዊ አየር ሃይል…የሰማዩ ንስርአየር ሃይል የአንድን ሀገር የአየር ክልል በንቃትና በተጠንቀቅ ከማንኛውም ጥቃት የመጠበቅ ሃላፊነት አ...
11/08/2026

የኢትዮጵያን አየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ የሚጠብቀው ዘመናዊ አየር ሃይል…የሰማዩ ንስር

አየር ሃይል የአንድን ሀገር የአየር ክልል በንቃትና በተጠንቀቅ ከማንኛውም ጥቃት የመጠበቅ ሃላፊነት አለበት፡፡

ጥቃት የሚፈጸም ከሆነም አስፈላጊውን አጸፋዊ ርምጃ በመውሰድ ጥቃቱን ይቀለብሳል ፤ ፈጥኖም በአነስተኛ ኪሳራ ያጠናቅቃል፡፡

ለዚህ ደግሞ ዘመኑን የዋጀ እና ዓለም የደረሰችበትን ወታደራዊ ቴክኖሎጂ የታጠቀ አየር ሃይል መገንባት ያስፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለሀገራዊ ሉዓላዊነት እና ለሕዝባዊ ኩራት ዋስትና ሆኖ የቆመ፣ ዘመናትን የተሻገረ የታሪክ እና የጀግንነት ማማ ነው፡፡

"ሰማዩ የኛ ነው" የሚለው መሪ ቃል የተሰጠውም በጀግኖች አብራሪዎች ደምና አጥንት፣ በላቀ የአየር ላይ የበላይነት እንዲሁም ጥልቅ በሆነ የሀገር ፍቅር የተጻፈ እውነት ስለሆነ ነው፡፡

የመደመር መንግሥት ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበና በሁለንተናዊ አቅሙ የጎለበተ ዘመናዊ አየር ሃይል ከመገንባት አንጻር ያከናወናቸው ሥራዎች አበረታች ናቸው፡፡

በዚህም የአየር ሃይሉን የቴክኖሎጂ ሽግግር በማጠናከር ቀጣናዊ ሰላምን ከማስከበር ባለፈ አህጉራዊ ተወዳዳሪ እንዲሆን በቁርጠኝነት እየተሰራ ይገኛል፡፡

በተለይም የዘመኑን ውጊያ ስልት አጢኖ የሚረዳ የሰለጠነ የሰው ሃይል እንዲሁም ውጊያ ጨራሽ የሆኑ ሰው አልባ አውሮፕላኖችና ሌሎች ተዋጊ ጀቶች መታጠቅ ላይ ትኩረት ተደርጓል፡፡

ለዚህም ከዓመት በፊት የተመረቀው ለሲቪልና ወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን የሚያመርተው ስካይ ዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪ መጥቀስ ይቻላል፡፡

ዘርፈ ብዙ ችሎታ ያላቸው ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በራስ አቅም በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ዲዛይን አድርጎ የማምረት አቅም መፍጠር ለኢትዮጵያ ትልቅ እመርታ ነው፡፡

ቴክኖሎጂው የጠላት እንቅስቃሴዎችን በቅጽበት ለመከታተል፣ ጥናት ለማድረግ እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

መሰል አቅምን ይበልጥ ማጠናከርም አየር ሃይል ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂን ለመታጠቅ የጀመረውን ጥረት ይበልጥ ለማሳለጥ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡

በተለይም የዘመኑን ቴክኖሎጂ የሚረዳ የሰው ሃብት፣ ዘመናዊ ትጥቆችና የውጊያ መሰረተ ልማት ለማሟላት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡

አየር ሃይል ጥቃት የሚፈጸም ከሆነ ጥቃቱን በአጭር ጊዜ ለመቀልበስና በትንሽ ኪሳራ ለመጨረስ ከማስቻሉ ባለፈ ግጭትን የማስቀረት አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡

የቀጣናው የጸጥታ ሁኔታ በየጊዜው በፍጥነት በሚለዋወጥበት ሁኔታ እንዲሁም ግጭትን በሚፈልጉ ተዋንያን ፊት ግጭትን ለማስቀረት የሚችል አቅም መፍጠር ደግሞ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም፡፡

የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ እንደሚሉት÷ አሁን ላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሀገሪቷን አየር ክልል ከማንኛውም ጥቃት መጠበቅና መከላከል የሚያስችል ቁመና ላይ ይገኛል፡፡

አየር ኃይሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂን በማፍለቅና የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት በ2022 ዓ.ም ከአፍሪካ ቀዳሚ የአየር ኃይል ለመሆን በቁርጠኝነት እየሰራ ነው፡፡

ለዚህም የለውጡ መንግሥት የአየር ሃይል አባላት ከፖለቲካና ከብሔር አስተሳሰብ እንዲወጡ በማድረግ ኢትዮጵያዊ መልክ እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሠራዊቱ በየቀኑ የመሳሪያ፣ የአካልና የእውቀት ፍተሻ በማድረግ የተሟላ ሥነ ልቦና ተላብሶ ሀገሩን እንዲጠብቅ እየተሰራ ነው፡፡

የኢትዮጵያን ሰማይ ከማንኛውም ያልተፈቀደ እንቅስቃሴ ለመጠበቅና ሉዓላዊ ደህንነቷን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥ ዘመናዊ የራዳር እና የዲጂታል ኮሙኒኬሽን

አባት ይሄዳል፤ ትዝታው ግን አይሞትም!የዓለማችን የምንጊዜም ታላቁ የእግር ኳስ ትጫዋች ሊዮኔል ሜሲ በሜዳ ላይ ከሚያሳየው ብርታት ጀርባ አባቱ የነበረውን ሚና ያውቃል።ይህንን ውድ አባቱን ሰሞ...
11/08/2026

አባት ይሄዳል፤ ትዝታው ግን አይሞትም!

የዓለማችን የምንጊዜም ታላቁ የእግር ኳስ ትጫዋች ሊዮኔል ሜሲ በሜዳ ላይ ከሚያሳየው ብርታት ጀርባ አባቱ የነበረውን ሚና ያውቃል።

ይህንን ውድ አባቱን ሰሞኑ በሞት አጥቷል። በእውነቱ ሜሲን በዚህ ጥቁር ሃዘን ውስጥ ማየት በራሱ ያሳዝናል💔

አባቱን ያጣ ሰው በየቀኑ የሚረዳው እውነታ አለ። አባት ማለት በሕይወትህ ከሁሉም ነገሮችህ ፊት የሚቆም ሰው ብቻ ሳይሆን፣ ከሄደም በኋላ በውስጥህ እየሰማሃው የሚቀጥል ታላቅ ድምፅ ነው።

አባት እጁ ይለያይ ይሆናል፤ የሚሰጠው ምክር ግን አይለይም። ድምፁ ጠፍቶ ይሆናል፤ በልጆቹ ልብ ውስጥ የዘራው ቃል ግን ዕድሜ ይኖረዋል።

የአባትህ ሞት የሚያስተምርህ ትልቅ ነገር አለው። አባትህን ስታጣ ትርጉሙ የአንድ ሰው መለየት ብቻ አይደለም። የራስህን አንድ ክፍል እስከነው መሸኘት ነው!

❤️💍 **13 ዓመታት ፍቅር፣ ትዕግስት እና በረከት** 💍❤️ዛሬ 13ኛ የጋብቻ ዓመታችንን ስናከብር፣ ልቤ በምስጋና ተሞልቷል። 🙏ከ13 ዓመታት በፊት የጀመርነው ጉዞ ሁልጊዜ ቀላል አልነበረም።...
11/08/2026

❤️💍 **13 ዓመታት ፍቅር፣ ትዕግስት እና በረከት** 💍❤️

ዛሬ 13ኛ የጋብቻ ዓመታችንን ስናከብር፣ ልቤ በምስጋና ተሞልቷል። 🙏

ከ13 ዓመታት በፊት የጀመርነው ጉዞ ሁልጊዜ ቀላል አልነበረም። ደስታንም ሆነ ችግርን፣ ስኬትንም ሆነ ፈተናን አብረን አልፈናል። በሁሉም ውስጥ ግን እግዚአብሔር እጁን ከእኛ ላይ አላነሳም።

ዛሬ የምንመለከተው ቤተሰብ፣ የልጆቻችን ፈገግታ እና አብረን ያሳለፍነው የሕይወት ጉዞ ትልቁ ስጦታችን ነው። ❤️

**ከ13 ዓመታት በኋላም እንደገና የመምረጥ ዕድል ቢሰጠኝ፣ እንደገና አንቺን እመርጥሻለሁ። ❤️**

ውዷ ባለቤቴ፣ ለፍቅርሽ፣ ለትዕግስትሽ እና ለእኛ ቤተሰብ ለምታደርጊው ሁሉ ከልብ አመሰግንሻለሁ።

**Happy 13th Wedding Anniversary, My Love! ❤️💍**

እግዚአብሔር ወደፊትም ብዙ ዓመታትን በፍቅር፣ በጤና፣ በሰላምና በበረከት አብረን እንድናከብር ያድርገን። 🙏❤️

**13 years down, forever to go. 💍❤️**



Dr-Nebiyu Lera Alaro

የኢትዮጵያ ሰውነት መገንባትና ፊትነስ ፌዴሬሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ የሰውነት ቅርጽ ውድድር አካሄደ።የኢትዮጵያ ሰውነት መገንባትና ፊትነስ ፌዴሬሽን በዓይነቱ ል...
10/08/2026

የኢትዮጵያ ሰውነት መገንባትና ፊትነስ ፌዴሬሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ የሰውነት ቅርጽ ውድድር አካሄደ።

የኢትዮጵያ ሰውነት መገንባትና ፊትነስ ፌዴሬሽን በዓይነቱ ልዩ የሆነ የሰውነት ግንባታ ውድድር በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ በዞኑ ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ማካሄዱ ተመልክቷል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የከምባታ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ እንግዳ ተሰማ እንደገለፁት ሰውነት መገንባትን የሚፈልግና ከተሰራበት ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ሊያስገኝ የሚችል እንደሆነ ጠቁመዋል።

ይህን በዓይነቱ ልዩ የሆነና በክልል ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውን ውድድር በዞናችን እንዲዘጋጅ ዕድል የሰጠዉን የኢትዮጵያ ሰውነት መገንባትና ፊትነስ ፌዴሬሽንን በማመስገን ለዛሬው ስኬት ብዙ ዋጋ የከፈላችሁትን በዞናችን ውስጥ የምትገኙ የዘርፉ ስፖርተኞች እና አማተር ባለሙያዎች በመምሪያው ስም እናመሰግናለን ብለዋል አቶ እንግዳ ተሰማ።

የከምባታ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ም/ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማዬ አድማሱ በበኩላቸው በተፈጥሮ ያገኘነው ሰውነት በአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች እንዲዳብር በማድረግ ሀገርንና ህዝብን ከፍ ማድረግ እንደሚቻል በመጥቀስ ለዚህ ተስፋ ያላችሁ የዛሬ ተወዳዳሪዎች ነገ ለሚጠብቃችሁ ውጤት በቁርጠኝነት ልትሰሩ ይገባል ብለዋል።

በመርሐ-ግብሩ የዱራሜ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማኑኤል ማትዎስን ጨምሮ ከተለያዮ ዞኖችና ወረዳዎች የተወጣጡ ስፖርተኞችና የከተማው ማህብረሰብ ታዳሚ እንደሆኑ ከዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ዱራሜ ከተማ አስተዳደር

Address

Ethiopia
Gimbi
PAPY_17

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when LIGHT MEDIA 30 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share