Light Media Network

Light Media Network Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Light Media Network, Media/News Company, Gimbi.
(9)

WELL CAME TO LIGHT MEDIA NETWORK !

''የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር ዛሬን እንተጋለን''
*ስነግምባታ፤መዝናኛ ፤ቁምነገር፤ትምህርታዊ፤መረጃ፤ሰብዓዊነት የሚስተናገድበት አለማቀፍ የፌስቡክ ቻናል

>> #ማስታወቂያ ለማሰራት በቴሌግራም አካውንታችን ማግኘት ይችላሉ>> #እናመሰግናለን

👉የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሲቪል ሥራ 70 በመቶ መድረሱን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።▶️ በዛሬው ዕለት ከሚኒስትሮቻቸው ጋር የኮይሻ ፕሮጀክትን ...
23/10/2025

👉የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሲቪል ሥራ 70 በመቶ መድረሱን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

▶️ በዛሬው ዕለት ከሚኒስትሮቻቸው ጋር የኮይሻ ፕሮጀክትን በመጎብኘት የ100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ መጀመራቸውንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የገለፁት።

▶️ ፕሮጀክቱ ከባለፈው ጉብኝት ጋር ሲነፃፀር የሚለካ የሥራ እድገት የታየበት መሆኑን እና ይህ ስኬት ለኃይል ምንጭ ዋስትና ለሚደረገው ያላሰለሰ ጥረት ምስክር መሆኑን አስታውቀዋል።

▶️ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባጋሩት መረጃ እንዳስታወቁት የግድቡ ከፍታ ከመሰረቱ 128 ሜትር ደርሷል።

👉የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ቤት ወይም ቪላ አልፋ እድሳት መጠናቀቁ ተገለጸ💫የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ቤት ወይም ቪላ አልፋ እስከ ጥቅምት 2018 ለሕዝ...
23/10/2025

👉የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ቤት ወይም ቪላ አልፋ እድሳት መጠናቀቁ ተገለጸ

💫የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ቤት ወይም ቪላ አልፋ እስከ ጥቅምት 2018 ለሕዝብ ክፍት ይሆናል ቢባልም፤ ክፍት ከመደረጉ በፊት መሰራት ያለባቸው ሥራዎች ገና ባለመጠናቀቃቸው እስከ ሚያዚያ ወር ሊቆይ እንደሚችል ነው የተገልጿል፡፡

የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ በሚያዚያ 2 ቀን 2004 ዓ.ም ካረፉ በኋላ ዝግ ሆኖ እስካሁን የዘለቀው ቪላ አልፋ፤ የተለያዩ የጥገና ሥራዎች እየተሰሩለት ነው ቢባልም ግን ለሕዝብ እይታ ተከልክሎ 14ኛ ዓመቱን ይዟል፡፡

ቪላ አልፋ የጥገና ሥራው ከመጀመሩ በፊት ውስጡ ያሉት ተንቀሳቃሽ የጥበብ ሥራዎች እና ሌሎችም ንብረቶች ወደ ቅርስ ባለ-ስልጣን መስሪያ ቤቱ እንዲሄዱ ተደርጎ እንደነበርም የሚታወስ ነው፡፡

ከመሬት በታች በሚወጣ እና ከላይ በሚዘንብ ዝናብ ቪላ አልፋ በጣም ተጎድቶ ነበር፤ አሁን ላይ ግን ከውጭ ሀገራትም ይሁን ከሀገር ውስጥ የአርቲስቱን ሥራዎች እየተመለከቱ ባለሙያዎች ትምህርት ለመውሰድ በሚችሉበት ደረጃ ጥገናው ተደርጓል ነው የተባለው፡፡

እንደ ሙዚየም የሚደራጅ በመሆኑ ጊዜ እንደወሰደም ነው የተገለጸው፡፡

የእድሳቱ ሥራ ተጠናቆ የርክክብ እና ቅርሶችን በቦታቸው የመመለስ ሥራዎች ብቻ ቀርቷል ሲሉም የብሄራዊ ሙዚየም መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዷለም ግርማይ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

"የእድሳቱ ሥራ ጥንቃቄዎችን የሚጠይቅ ነበር" ያሉት አቶ እንዷለም፤ የርክክብ ሥራዎች ሲጠናቀቁ ቪላ አልፋን በ2018 እስከ ሚያዚያ ወር ለእይታ ክፍት ለማድረግ ታስቧል ነው ያሉት፡፡

የእድሳት ሥራው 65 ሚሊየን ብር እንዳስወጣ ከዚህ በፊት የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡የእድሳት ሥራው በምዕራፎች የተከፋፈለ ነበር ነው የተባለው፡፡

የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን13/02/2018 ዓ/ም
23/10/2025

የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን
13/02/2018 ዓ/ም

21/10/2025

ደቡብ አፍሪካ ክፍል 2

ከብዙ ወንዶች ጋር ተኝቻለሁ “ዘሪቱ ከበደ” ሰሞኑን ባስነበበችው መፅሀፍ ላይ የገለፀችው ፅሁፍ እያነጋገረ ነው። • ተወዳጇ አርቲስት ዘሪቱ ከበደ በሰሞኑ በሳተመችው መፅሃፏ ላይ የህይወት ታሪ...
21/10/2025

ከብዙ ወንዶች ጋር ተኝቻለሁ “ዘሪቱ ከበደ” ሰሞኑን ባስነበበችው መፅሀፍ ላይ የገለፀችው ፅሁፍ እያነጋገረ ነው።

• ተወዳጇ አርቲስት ዘሪቱ ከበደ በሰሞኑ በሳተመችው መፅሃፏ ላይ የህይወት ታሪኳን ስትናገር ብዙዎቻችንን የማንደፍረውን የፆታዊ ግንኙነት ታርኳን አብራርታ የፃፈች ሲሆን

• ከብዙ ወንዶች ጋር አንሶላ መጋፈፏን አስታውቃለች እንደዚህ አይነት ነገሮች ታቡ በሆኑበት የሚደርግ ግን የማይነገር ተደርጎ በታመነበት ማህበረሰብ ውስጥ በግልፅ ያለፈችበትን መንገድ መናገሯ ለብዙዎች አስተማሪ ነው ። አብዛኞቻችን በአደባባይ ጨዋ የግብረገብ አስተማሪ በድብቅ ዋልጊ ስለሆንን በቀላሉ እንተች ይሆናል ።

• ከዘሪቱ የሚብሱ ብዙዎች የግብረገብ አስተማሪዎች መኖራቸው ግን የማይካድ ነው ። ዘሪቱ ያ ህይወቷ በዝናዋ የተደበቀ ከባድ ህመም እንደፈጠረባት ነው የነገረችን በድርጊቷ ኮርታ ተመፃድቃ አይደለም ።

እናንተስ ምን ትላላችሁ ሐሳባችሁን አካፍሉን። ?

  ከመተኛትህ በፊት በምታገኘው ረፍት ድብቁ የአእምሮ ክፍል በሰፊው ክፍት ስለሚሆን፣ የምታስበውን በትክክል ለማግኘት እድሉ ይኖረዋል። ይህ ማለት ዘርን በሚያለመልም አፈር ላይ በትክክለኛው ሰ...
21/10/2025



ከመተኛትህ በፊት በምታገኘው ረፍት ድብቁ የአእምሮ ክፍል በሰፊው ክፍት ስለሚሆን፣ የምታስበውን በትክክል ለማግኘት እድሉ ይኖረዋል።

ይህ ማለት ዘርን በሚያለመልም አፈር ላይ በትክክለኛው ሰአት መትከል ማለት ነው። በዚህም ህልምህ ስር እንዲይዝ እና እድገት እንዲያገኝ መፍቀድ ይሆናል።



ምክንያቱም ብዙ ህልሞች የሞቱት በፍርሃት መሆኑን እወቅ። ሩቅ የሚያስጉዝ አቅም አሳስሮ የሚያስቀምጥህ ፍርሃት የተበለ ነቀዝ ነው። ምን ይሉኝ ይሆን ብለህ አትስብ፤ የሚሉትን ይበሉ፤ ግን መኖር አለብኝ ብለህ የምታስበው ኑር። ደፋር ሁን፤ ፍርሃት እንኳን ዙሪያህ ቢከብህም።

አንተ የሚወቅስህ እና አትችልም የሚልህ አብዛኛው ጊዜ ምንም ነገር ሞክሮ የማያወቅ የመቀመጥ ንጉስ፣ የጥላቻ አለቃ የሆነ ሰው ነው። ተዋቸው ያሉትን ይበሉ። ዛሬ ነው ዳዴ የምትለው ከሆነ ጊዜ በኃላ ምን ያህል እርቀት ከእነሱ እንደሚኖርህ አስብ።

ከመሃንዲስ መንደር
@ያና

አሳዛኝ ዜና 😭በድሬዳዋ ደወሌ ባቡር ላይ በደረሰ አደጋ 14 ሰዎች ሞቱ።በድሬዳዋ ደወሌ ባቡር ላይ በደረሰ አደጋ 14 ሰዎች ሲሞቱ 29  ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።...
21/10/2025

አሳዛኝ ዜና 😭
በድሬዳዋ ደወሌ ባቡር ላይ በደረሰ አደጋ 14 ሰዎች ሞቱ።

በድሬዳዋ ደወሌ ባቡር ላይ በደረሰ አደጋ 14 ሰዎች ሲሞቱ 29 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

ከደወሌ መነሻውን አድርጎ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ባቡር ትላንት ሌሊት 8:00 አካባቢ በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ወረዳ ላይ በደረሰበት አደጋ 14 ሰዎች ሲሞቱ 29 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ከሽኒሌ ወረዳ አስተዳደር የደረሰን መረጃ ያመለክታል ሲል ድሬ ቲቪ ነው የዘገበው።

Light Media Network

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ ወደ  #ሞስኮ አቀኑ፤ በኢኮኖሚ እና ኒውክሌር ትብብር ዙሪያ መከሩየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትና...
21/10/2025

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ ወደ #ሞስኮ አቀኑ፤ በኢኮኖሚ እና ኒውክሌር ትብብር ዙሪያ መከሩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ሞስኮ-ሩስያ መግባታቸው ተገለጸ።

በመጀመሪያ ዕለትም ከሩስያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ ማክሲሞ ሬሼንኮቭ ጋር ውይይት አድርገዋል ሲል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል። ሁለቱ ወገኖች በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን አድማሰ ሰፊ እና የቆየ ትብብር የበለጠ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ተብሏል።

እንደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ፣ የሩስያው የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲሞ ሬሼንኮቭ አገራቸው ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለምትደርገው ጥረት ሙሉ ድጋፍ እንደምትሰጥ ለዶ/ር ጌዲዎን አረጋግጠዋል።

ዶ/ር ጌዲዎን ከሮሳቶም፣ ከሩስያ አቶሚክ ኤጄንሲ እና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ጋር በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የቴክኖሎጂ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ተወያይተዋል።

በመስከረም ወር፣ ኢትዮጵያና ሩሲያ በኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ይህ ስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሞስኮ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ከተወያዩበት ሰፊ የትብብር አካል ነው።

ስምምነቱ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም በሩሲያ አቶሚክ ኢነርጂ ኮርፖሬሽን (ሮሳቶም) ዋና ዳይሬክተር አሌክሲ ሊካቼቭ እና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) መካከል ተፈርሟል።

ይህም ሮሳቶም እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመገንባት ለሚያደርጉት ትብብር ተግባራዊ እርምጃን የሚያስቀምጥ መሆኑ ተገልጿል።

As the 18th Ethiopian Society of Orthopedics & Traumatology (ESOT) Annual Conference comes to a close, we extend our hea...
21/10/2025

As the 18th Ethiopian Society of Orthopedics & Traumatology (ESOT) Annual Conference comes to a close, we extend our heartfelt gratitude to everyone who made this event an incredible success.

🌟 To our distinguished guests, for your inspiring presence and contribution.
🤝 To our sponsors and partners, for your unwavering support and collaboration.
🧠 To all speakers, researchers, and presenters, for sharing your knowledge and innovation.
💼 To our organizers, volunteers, and the Melacare Events & Consultancy team, for your dedication and professionalism behind the scenes.
🩺 And to all participants and ESOT members, for your engagement and continuous effort to advance Orthopedics and Trauma care in Ethiopia.

Together, we have celebrated excellence, shared ideas, and strengthened our commitment to improving healthcare.
Here’s to more collaboration, innovation, and progress in the years ahead! 🌍✨

20/10/2025

በህዝበ ሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን በአብዛኛው ህዝበ ክርስቲያን እጅግ የሚወደዱት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር ኢድሪስ ንግግር

ነብስ ይማር 🥲
Light Media Network

Address

Gimbi
PAPY_17

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Light Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share