27/09/2025
በኢፌዲሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ዶ/ር ተስፋዬ በልጂጌ ለኦይዳ ወረዳ አስተዳደር ከ300,000 ብር በላይ የሚገመት የኮሚፕዩተር ድጋፍ አደረጉ።
ሳውላ ፣ መስከረም /2018 ዓ/ም
ዶ/ር ተሰፋዬ በልጂጌን በመወከል የኮሚፕዩተር ድጋፉን ያስረከቡት የጎፋ ዞን ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እና የመንግሥት ረዳት ተጠሪ አቶ ይሁን ደምሴ በዶ/ር ተስፋዬ በልጂጌ በኩል የተደረገው ድጋፍ ዶክተሩ ለአከባቢው ያለውን መቆርቆር የሚያሳይ መሆኑን በመግለጽ ዶ/ር ተስፋዬ በየጊዜው ለሚያደርገው ድጋፍ በዞኑ ስም አመስግነዋል።
የኦይዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታዘቤ ጋትሦ በበኩላቸው ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ ከአከባቢው አልፎ በሀገር ደረጃ ትላልቅ ሥራዎችን የሠራ እና እየሠራ ያለ ብርቱ ሰው መሆናቸውን በመጥቀስ ከዚህ በፊትም ለወረዳው በተለያየ መልኩ ድጋፍ ስያደርጉ መቆየታቸውን በማስታወስ በተደረገው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ ከልብ አመስግነዋል።