Gofa TV

Gofa TV ለሁለንተናዊ ዕድገት እንተጋለን

ተጨማሪ 3 ሺህ 350 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥተዋልመስከረም 22/2018 ዓ.ም በተሻሻለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት እና በተስተካከለው የፊዝክስ ውጤት ተጨማሪ...
02/10/2025

ተጨማሪ 3 ሺህ 350 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥተዋል

መስከረም 22/2018 ዓ.ም

በተሻሻለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት እና በተስተካከለው የፊዝክስ ውጤት ተጨማሪ 3 ሺህ 350 ተማሪዎች አልፈዋል አለ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና አማካይ ውጤታቸው 49 ነጥብ 50 እስከ 49 ነጥብ 99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ወደ 50 በመቶ እንዲጠጋጋ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሰረትም የ2017 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ከ300 ወደ 297 ዝቅ ብሏል፡፡

በተጨማሪም በበይነ መረብ በተፈተኑ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ የፊዚክስ ውጤት ወደ መቶኛ ያልተቀየረላቸው እንዲሁም ወደ መቶኛ ሲቀየር በነጥብ ቤት የነበሩ ቁጥሮች ያልተደመረላቸው ተማሪዎች እንደነበሩ ተጠቅሷል፡፡

በዚህም ተማሪዎቹ ተያያዥ መረጃዎች ላይ ቅሬታቸውን አቅርበው ውጤታቸው መስተካከሉ ነው የተገለጸው፡፡

ይህን ተከትሎም 3 ሺህ 350 ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ያመጡ ሲሆን ÷ በ50 ከመቶና በላይ ያመጡ አጠቃላይ ተፈታኞች ቁጥርም 52 ሺህ 279 ደርሷል፡፡

ያለፉ ተማሪዎች ቁጥር በመቶኛ ሲገለጽም 8 ነጥብ 9 በመቶ ሆኖ መመዝቡን የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የጎፋ ጋዜ ማስቃላ አካል የሆነው የ"ጊያ ካንሶ" ባህላዊ ክብረ በዓል  በጋልማ ከተማ በድምቀት ተከበረ።‎‎ሣውላ፣ መስከረም 22/2018 ዓ.ም (ጎፋ ቴቪ)‎‎የጎፋ ጋዜ ማስቃላ አካል የሆነው ...
02/10/2025

የጎፋ ጋዜ ማስቃላ አካል የሆነው የ"ጊያ ካንሶ" ባህላዊ ክብረ በዓል በጋልማ ከተማ በድምቀት ተከበረ።

‎ሣውላ፣ መስከረም 22/2018 ዓ.ም (ጎፋ ቴቪ)

‎የጎፋ ጋዜ ማስቃላ አካል የሆነው የ"ጊያ ካንሶ" ባህላዊ ክብረ በዓል በዛላ ወረዳ ጋልማ ከተማ በድምቀት ተከብሯል።

‎የ"ጊያ ካንሶ" ባህላዊ ክብረ በዓል ልጃገረዶች ከወንዶች ጋር የሚተያዩበት፤ ያገቡት ሶፌ(ገበያ) የሚወጡበት፣ ጀግኖች የሚወደሱበት፤የተጣላ የሚታረቅበትና ፍቅር፣ አንድነትና ወንድማማችነት የሚጠናከርበት ነው።

‎የጎፋ ዞን አስተዳደር ተወካይና የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ብላቴ በክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንደተናገሩት፣ ወጣቶች ደምቀው የሚታዩበት ፍቅርና መተሳሰብ የሚደምቅበት በዓል መሆኑን ተናግረዉ የጊያ ካንሶ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ ያቆየውን የዛላ ወረዳ ሕዝብን በማድነቅ በዓሉ የአንድነትና የፍቅር መገለጫ መሆኑን ተናግረዋል።

‎የጋልማ ከተማ ከንቲባ አቶ ያዕቆብ ዘካሪያስ የጊያ ካንሶ ባህላዊ ክብረ በዓል በየዓመቱ በዛላ ወረዳ በድምቀት እንደሚከበር ገልጸዉ አባቶቻችን ጠብቀው ያቆዩት የ"ጊያ ካንሶ" ወይም የመስቀል ሽኝት ባህላዊ ክብረ በዓል ባህላዊ ትዉፊቱን ጠብቆ እንዲሄድ እየሠራን እንገኛለን ብለዋል።

‎የዛላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አንበስ ሃናን በበኩለቸው ይህ በዓል በወረዳዉ ከህጻን እስከ አዋቂ በድምቀት የሚያከብረው በዓል መሆኑን ተናግረዉ በወረዳው ጊያ ካንሶን ጨምሮ በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች የሚገኝበት መሆኑን በመግለጽ የ"ጊያ ካንሶ" ባህላዊ ክብረ በዓል ህዝቡን በፍቅር የሚያስተሳስር ነው ብለዋል።

‎በክብረ በዓሉ ላይ የጎፋ ዞን፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ የጋልማና የዛላ ወረዳ ነዋሪዎች፣የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ተመረቀ መስከረም 22/2018 ዓ.ምበሶማሌ ክልል ካሉብ በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪ...
02/10/2025

የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ተመረቀ

መስከረም 22/2018 ዓ.ም

በሶማሌ ክልል ካሉብ በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀናል።

በተመሳሳይም በአመት 1.33 ቢሊዮን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን ዙር አስጀምረናል።

ከፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ምርት ባሻገር በኃይል ማመንጫ ዘርፉም 1000 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም በመያዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ከሁሉም በላይ ፕሮጄክቱ የጋዝ ማምረቻ ብቻ አይደለም። ለማዳበሪያ ማምረቻ ወሳኝ የሆነውን ግብዓት በማቅረብ ለምግብ ሉዓላዊነት ጥረታችን የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል።

ለኃይል ማመንጫ እና የክሪፕቶ-ማይኒንግ ሥራዎቻችን አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ያቀርብልናል።

ዛሬ በሶማሌ ክልል የጀመርናቸው ከተያያዠ‍ መሠረተ ልማቶች ግንባታ ጋር በአጠቃላይ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች በተገቢ ክትትል እስከ መጠናቀቂያቸው ይደርሳሉ። የጀመርነውን ለመጨረስ ሁልጊዜም በጽናት እንደሠራነው ሁሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት ይደርሳሉ።

30/09/2025
‎ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በእንጀራ ጋጋሪና አቅራቢነት ማኅበር ለተደራጁ ሴቶች ድጋፍ አደረጉ ።‎‎ሳውላ ፤ መስከረም 20/2018 ዓ.ም ‎‎የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳ...
30/09/2025

‎ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በእንጀራ ጋጋሪና አቅራቢነት ማኅበር ለተደራጁ ሴቶች ድጋፍ አደረጉ ።

‎ሳውላ ፤ መስከረም 20/2018 ዓ.ም

‎የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በእንጀራ ጋጋሪና አቅራቢነት በማኅበር ለተደራጁ ሴቶች እንቅስቃሴ ማስጀመሪያ ከሦስት ኩንታል በላይ ጤፍ ድጋፍ አድርገዋል ።

‎ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ማኅበራቱን በጎበኙበት ወቅት እንደገለፁት ሴቶች ጠንካራና ለሥራ ትጉ መሆናቸውን ገልፀው በርትተው ከሠሩና ትንሽ ድጋፍ ከተደረገላቸው ለሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወቱ ገልፀዋል ።

‎ለማኅበራቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ 10 የኤሌክትሪክ ምጣድና ማቡኪያ ሮቶና 50 ኪሎ ግራም ጤፍ ፣ የሳውላ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል ።

‎ፍቅር የእንጀራ ጋጋሪና አቅራቢ ሴቶች ማኅበር በተደረገላቸው ድጋፍ እጅግ በጣም መደሰታቸውን ገልፀው ውጤታማ ሥራ ሠርተን እናስመሰግናለን ብለዋል ።

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በበድሮ ሴሎ ዋልፃ  ቀበሌ ላይ የማህበረሰብ ደህንነት ፓትሮል ቅኝት አባላት ስልጠና ተሰጠ።ቡልቂ ፣ መስከረም  19/2018 ዓ/ም                      ...
30/09/2025

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በበድሮ ሴሎ ዋልፃ ቀበሌ ላይ የማህበረሰብ ደህንነት ፓትሮል ቅኝት አባላት ስልጠና ተሰጠ።

ቡልቂ ፣ መስከረም 19/2018 ዓ/ም

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በበድሮ ሴሎ ዋልፃ ቀበሌ ላይ የማህበረሰብ ደህንነት ፓትሮል ቅኝት አባላት ስልጠና ተሰጠ።

የገዜ ጎፋ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የመህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ኃላፊ ረ/ኢ/ር ታደሴ ቱፋ በኩል የማህበረሰብ ደህንነት ፓትሮል ቅኝት ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርገዋል።

የማህበረሰብ ደህንነት ፓትሮል ቅኝት አባላቱ በአካባቢያቸው በሚፈፀሙ ወንጀሎች ላይ ቅድሜ ወንጀል መከላከል ሥራ እንዲሰሩ በበቂ ሁኔታ ስልጠና ተሰጥቷል።

አባላቱ ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት አስቀድሞ በመከላከል በኩል ጉልህ ድርሻ እንደሚኖራቸው የሚታወቅ ስሆን የአከባቢያቸውን ነባራዊ ሁኔታ ሁሌም በትኩረት ይከታተላሉ፣ አጣራጣሪ ነገሮች ቢያጋጥሙ ለአከባቢው ፖሊስ ማሳወቅ እንዳላቸው ተገልፆ እርስ በርሳቸውም መረጃ መለዋወጥ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልፆላቸዋል።

በአከባቢው ሰው ሰራሽም ሆነ በተፈጥሮ አደጋ ጊዜ በእርዳታና በይድረሱልኝ ጥሪዎች በመገኘት የራሳቸውን ድርሻ እንደሚወጡ አሳስበዋል።

አጠራጠሪ ሁኔታዎች በማንኛውም ከተለመደው ውጪ በአከባቢያችን ቀንም ሆነ ማታ የሚፈጠሩ /የሚከናወኑ ነገሮች/ተግባራት ካሉ የወንጀል ድርጊቶች ሊሆኑ ስለሚችሉ በትኩረት መመልከትና መገናዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።

የማህበረሰብ ደህንነት ፓትሮል ቅኝት አከባቢውን መጠበቅ ስሆን ይህ ተግባር በየተራ አከባቢያቸውን ከመጠበቅ(መቃኘት) ጀምሮ ስለወንጀል ስጋትም ሆነ ወንጀል ስለመፈፀሙ መረጃ ለፖሊስ እስከ ማድረስና የአካባቢው ነዋሪዎች ይህንን መረጃ በማጋራት አከባቢያቸውን ለመጠበቅ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ መሆኑን አብራርተዋል ።

በስልጠና ላይ ወንጀል ለሀገርም ሆነ ለአከባቢው ልማት ፀር ከመሆኑም ባሻገር በሰላም ውሎ ለማደር ሠላም ስለሚያስፈልግ በመድረኩ ላይ ሀሳብ ተቀምጠዋል ።

የማህበረሰብ ደህንነት ፓትሮል ቅኝት ዋና ዓለማው ማህበረሰቡ ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት የአከባቢው ሠላምና ደህንነት በባለቤትነት ለማረጋገጥ ለውጥ ማምጣት ስለሚያፈልግ ስልጠና ላይ ተካተዋል።

በመጨረሻም ከስልጠና በኋላ የማህበረሰብ ደህንነት ፓትሮል ቅኝት አባላት መለያ የሆነውን ማንፀባረቂያ በማልበስ ወደ ስራ ተግባር እንድገቡ ተደርጓል።

በመድረኩ ማጠቃለያም በማዕከሉ ምድብ ፖሊስ አባላት እና በቀበሌው አመራር የስራ ስምርት በመስጠት ተጠቃለዋል።

ይህ ትክክለኛ የጎፋ ቴለቪዥን የፌስቡክ ገፅ ነው።
29/09/2025

ይህ ትክክለኛ የጎፋ ቴለቪዥን የፌስቡክ ገፅ ነው።

Address

Gofa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gofa TV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category