Gebeyaw media

Gebeyaw media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gebeyaw media, Media/News Company, Bure, Gojam.

22/12/2022

የሲሚንቶ የመሸጫ ዋጋ ተመን ወጣ

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ለቀጣይ ስድስት ወራት የሚቆይ
የሲሚንቶ የነጻ ገበያ ወጋ ወሰነ።

የሲሚንቶ ዋጋ በመንግሥት ተወስኖ እንዲሸጥ መደረጉ በርካታ ቅሬታዎችን ሲያስነሳ መቆየቱን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። ይህም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች፥ ሲሚንቶን በቀላሉ እንዳያገኙ አድርጓቸው እንደነበር የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተሻለ በልሁ ገልጸዋል።

በተሻሻለው መመሪያ መሠረትም አከፋፋዮችን እና ቸርቻሪዎችን መምረጥ የፋብሪካዎቹ እድል መሆኑ ተጠቅሷል።

የፋብሪካዎቹ የመሸጫ ዋጋ ለጊዜው ምርታማነት እስከሚጨምር ድረስ የፋብሪካ ዋጋ በስድስት ወር አንድ ጊዜ በሚኒስቴሩ እንደሚወሰን ነው ሚኒስትር ዲኤታው የተናገሩት።

መንግሥት ከግብይቱ የወጣ ሲሆን በተሻሻለው መመሪያ መሠረትም መንግሥት ሽያጩ ያለ ደረሰኝ እንዳይካሄድ ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስረድተዋል።

በግብይቱ ውስጥም ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ እና ደረሰኝ ግዴታ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ከዛሬ ጀምሮም ሲሚንቶ በየትኛውም ቦታ ቁጥጥር እና ክትትል ሳይደረግበት በነጻ ገበያ ይካሄዳል ነው ያለው ሚኒስቴሩ።

ከፋብሪካ ሲሚንቶ የሚወጣ ማንኛውም ተሽከርካሪ የመዳረሻ ሰነድ መያዝ እንደሚኖርበትም ነው የተናገሩት።

መንግሥት አሁን ያወጣው ተመን ፋብሪካዎች የአቅርቦት እና ፍላጎቱን ክፍተት መሙላት በሚችሉ ጊዜ የሚነሳ ይሆናል።

ከዚህም በተጓዳኝ በአዲሱ መመሪያ መሠረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቤቱ ለ6 ወራት የሚቆይ የፋብሪካ መውጫ ዋጋ ወስኗል።
በዚህም መሠረት:–
👉ዳንጎቴ 795 ብር ከ93 ሳንቲም፣

👉ደርባ 761 ብር ከ55 ሳንቲም፣

👉ሙገር 755 ብር ከ70 ሳንቲም ፣

👉ናሽናል 756 ብር ከ50 ሳንቲም

👉ሃበሻ 754 ብር ከ48 ሳንቲም፣

👉ፓዮኔር 753 ብር ከ95 ሳንቲም

👉ኢትዮ 753 ብር ከ60 ሳንቲም፣

👉ኢንጪኒ 750 ብር ከ21 ሳንቲም

👉ኩዩ 752 ብር ከ50 ሳንቲም

👉ኢስት 753 ብር ከ82 ሳንቲም

👉ካፒታል 751 ብር ከ34 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል፡፡

በመግለጫው ፋብሪካዎቹ በተሻሻለው ተመን መሠረት ከዛሬ ጀምሮ መሸጥ ይችላሉ ተብሏል።

መንግሥት አሁን ያወጣው ተመን ፋብሪካዎች የአቅርቦት እና ፍላጎቱን ክፍተት መሙላት በሚችሉ ጊዜ የሚነሳ ይሆናል ነው የተባለው።

አሚኮ እንደዘገበው

22/12/2022

እምባሽ እንደውሀ ቢወርድ በጅረቱ
ልጅሽ በረሀብ ጠኔ ቢታጠፍ አንጀቱ
ቢበዛም ቢተርፍም ሲቃይ እንግልቱ።
አይዞሽ እናት ሀገር አንች የፍቅር ሸማ
መምሸቱ እንደማይቀር በንጋት ዋዜማ
ቀኝሽ አይረሳሽም በቅዱስ ቃል ዜማ።

ታሪክ ያለኝ ባለ ዝናከኩሩ አ'ገር ሁሌ ብስራት የድል ዜናዜማ ቅኔ ታሪክ ድርሳንየጀግንነት ብሩህ ልሳንባለፀጋ ሀብት ውርሱከሞላባት ባህል ቅርሱተፈጥሬ ከኢትዬጲያ ከታላቋሰው መፍጠር በሰውነት አ...
20/12/2022

ታሪክ ያለኝ ባለ ዝና
ከኩሩ አ'ገር ሁሌ ብስራት የድል ዜና
ዜማ ቅኔ ታሪክ ድርሳን
የጀግንነት ብሩህ ልሳን
ባለፀጋ ሀብት ውርሱ
ከሞላባት ባህል ቅርሱ
ተፈጥሬ ከኢትዬጲያ ከታላቋ
ሰው መፍጠር በሰውነት አይደል ብርቋ

05/12/2022

Address

Bure
Gojam

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gebeyaw media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share