10/02/2025
ነገሩ ቀላል ባይሆንም ውስብስብ ግን አይደለም።
It is simple, but not easy እንደሚባለው
100 ብር ቢሰጥህ ምን ታደርጋለህ?
ይህንን ጥያቄ ለትንንሽ ልጆቼ (ድሮ ነው) ያቀረብኩላቸው።
ትንሽ እንዲያስቡ ካደረግኋቸው በኋላ ለእያንዳንዳቸው 100 ብር ሰጠኋቸው።
ምሳ ላይ ብሩን ምን እንዳደረጉበት ጠየቅኋቸው።
#የመጀመሪያው ልጅ ከምሳ በፊት 100 ብሩን ጨርሷል። ብስኩት፣ ቸኮሌት ምናምን ገዛዛበትና በላ፣ ለሌሎቹም ሰጠ።
#ሴቷ ልጅ 80 ብር ያህል አጥፍታ 20 ብር ገደማ ቀርቷታል።
እሷም የተለየ ነገር አላደረገችም። ኬክና ሌሎች ጣፋጮችን፣ የጸጉር ማስያዣ ጌጦች ገዛዛችበት።
#ሌላኛው ልጅ ገንዘቡን ምንም ሳያጠፋ የድሮውን ጌም እየተጫወተ ነው። ብሩን ማስቀመጡን አምጥቶ አሳየ። ጥቂት ሳምንታት እንዳለፉም ብሩን ማስቲካ ገዝቶ ትምህርት ቤት እየወሰደ በትርፍ መሸጥ ጀመረ።
ይህንን ድርጊት ትምህርት ቤቱ ደርሶበት እስኪያስቆመው ድረስ ገፍቶበት ነበር።
ይህንን ለምን እንዳስቆሙት ዛሬም ድረስ አይገባኝም። ከዚህ የተሻለ ትምህርት የሚሰጡት አይመስለኝም።
ዛሬ ያ ልጅ ስለ ቢዝነስ ኮሌጅ ገብቶ እየተማረ ነው።
እስኪ አንተን ልጠይቅህ?
100 ሺህ ብር ቢሰጥህ ምን ታደርግበታለህ?
እሱ አነሰ ካልክ
1 ሚሊየን ብር ቢሰጥህ ምን ታደርጋለህ?
እሺ እሱም ካነሰ
10 ሚሊየን ብር ቢሰጥህ ምን ታደርጋለህ?
የገንዘብ ችግር ውስጥ ያለ ብዙ ሰው ገንዘብ ሲያገኝ መኪና፣ ቤትና የቤት ዕቃ ከመግዛት ያለፈ ነገር አያደርግም። ቤት/ኮንዶምኒየም መግዛት፣ መኪና መግዛት፣ የቤት ዕቃ መገዛዛት፣ ውጭ ሀገር መሄድ፣ ድግስ መደገስ፣ መዝናናት፣ ... ይኸው ነው። ገንዘቡ በአጭር ጊዜ ይወድምና ችግሩ ይቀጥላል። ገንዘብ አጠፋፋቸው ከህጻናቱ የሚለየው በዕቃዎቹ ዓይነት ነው። ለህጻናቱ ብስኩት፣ ለአዋቂዎቹ መኪና ነው። ችግሩ ተመሳሳይ ነው።
ታድያ ችግሩ የምንድን ነው?
ችግሩ የሀሳብ እጦት ነው! የራዕይ አለመኖር ነው! የዝግጅት ማነስ ነው! የInspiration አለመኖር ነው።
ራዕይ ለሌለው ሰው የትኛውም የኑሮ መንገድ ያስኬደዋል፣ አቅጣጫ የለውም።
እስኪ የማን ህይወት ይማርክሃል? የማን አኗኗር ሞዴል ይሆንሃል?
የኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ የክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ የደራርቱ ቱሉ፣ የቴዲ አፍሮ፣ የዳንኤል ክብረት፣ የወርቁ አይተነው፣ የዮናታን አክሊሉ፣ የአስቴር አወቀ፣ የመስከረም ጌቱ፣ የቢንያም በለጠ፣ የኤለን መስክ፣ የዶናልድ ትራምፕ፣ የቢል ጌትስ፣ ... እኮ የማን ህይወት ምሳሌ ይሆንሃል?
በየትኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ብትሆን ራዕይ ሊኖርህ ያስፈልጋል። ራዕይ ከሌለህ ገንዘብ በህይወትህ ላይ ጠቃሚ ለውጥ አያመጣም፤ ምናልባትም ሊያጠፋህ ይችላል።
ገንዘብ እንደ እሳት ነው። እሳት ያጠፋልም፣ ያለማልም። እሳት ብረት ያቀልጣል፣ ብረት አቅልጦም ብዙ ጥሩ መሳሪያ ይሠራበታል። እሳት በአግባቡ ካልተያዘ ግን ህንጻን ያህል ነገር በፍጥነት ያወድማል። ገንዘብም እንደዚያው ነው።
ወዳጄ :- ብር ይዘህ ሀሳብ ከመፈለግ፣ ሀሳብ ይዘህ ለሀሳብህ ማሳኪያ ብር ብትፈልግ ይሻልሃል። ብር ከማሳደድ ይልቅ ሀሳብ አሳድድ።
ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች ባንክ ቤት አታጣቸውም። ሀሳብ ሳይኖርህ ባንክ ቤት ብትሄድ ከንቱ ልፋት ነው።
በቀጣይ 6 ወራት ውስጥ ተምረህ፣ ለምደህ እና ተለማምደህ የምታሳካውን የሥራ ዘርፍ ምረጥ። ከዚያ ለዚያ ሥራ ገንዘብ ፈልግ። እመነኝ አዲሱን ዓመት በአዲስ ሥራ ብቅ ትላለህ።
ልብስ መስፋት ይሁን ብረት መበየድ፣ ሞባይል መጠገን ይሁን ኮድ መጻፍ፣ የኢኮመርስ ፕላትፎርም መፍጠር ይሁን ዳቦ ቤት መክፈት፣ ቀለም ይሁን