11/07/2022
ሀምሌ 5
********************
የህዋሃት ውድቀት የተጠነሰሰበት
ሀምሌ 5/ 2008 ከሌሊቱ 10 ሰዓት "የወልቃይት
የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ" አባላትን ለማፈንና ወደ
ማሰቃያ ካምፖች በሰላም ባስ ጭኖ ለመውሰድ ከመቀሌ
የተላከ አፋኝ ቡድን ጎንደር የኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ቤት
ደረሰ።
➢ አፋኝ ቡድኑ:- የኮሎኔል ደመቀን የግቢ በር ቆፈቆፈ
➢ ኮሌኔል ደመቀ:- ''ማን ልበል?''...ብሎ ጠየቀ
➢ አፋኝ ቡድኑ :- '' እኛ ከመንግሥት ተልከን የመጣን
ፖሊሶች ነን ክፈት በሩን''..አሉት
➢ ኮለኔል ደመቀ:- "የመንግስት መልዕክኞች ከሆናችሁ
ለምን በቀን አትመጡም አሁን ምን ትሰራላቹህ ?? ዙሮ ዙሮ
አሁን ጨለማ ስለሆነ አልከፍታቹህም ተመለሱ አላቸው
➢ አፋኝ ቡድኑ :- ይህን ሲላቸው በኃይል እንገባለን ብለው
ለመግባት ሲሞክሩ በመካከል አትገቡም በማለት
ወዲያውኑ አፋኝ ቡድኑ ተኩስ ከፈተ ፣ መትረጊስ ፣ ድሽቃ
የታጠቀው ይህ ቡድን በኮሎኔሉ ቤት የጥይት ናዳ ያወርድ
ጀመር
➢ በዚህ ሰዓት ኮለኔል ደመቀ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ጥግ
ይዞ ጥይቶቹን በቁጥር ደርድሮ ሚስትና ልጆቹን ወደ ጎን
አድርጎ ጠላ*ን መጠባበቅ ጀመረ , ወዲያው በአጥር ዘለው
የገቡትን 2 የአፋኝ ቡድኑን ታጣቂዎች አስተኛቸው ።ነገሩ
ሁሉ በቅፅበት በድፍን ጎንደር ተሰማ።
➢ የአማራ የነፃነት አርበኞች እነ አበራ ጎባው፣ እነ
መሳፍንት እና ሌሎችም የጎንደር ጀግኖች ለፍልሚያው
ጎንደር ከተማ ገቡ
➢ ደንቢያ ፣ላይ አርማጭሆ እስከ ሶሮቃ ድረስ የአማራ
አርበኞች ተጠራርተው
መጡ።
➢ አሁን ጎንደር ቀውጢ ሆነች ፣ በጥይት አረር ተቆላች ፣
የጎንደር አርበኞች ሁሉ < ቃላችን ለሰማይና ለምድር ይሁን
> እኛ ሳንሞት ኮሌኔሉን እዚች ምድር ማንም ንቅንቅ
አያደርገውም በማለት ጠላትን አሳፈሩ
➢ አንድ ግዜ ብቻ ከ30 በላይ ሆኖ ከመጣው የህዋወት
ታጣቂ ውስጥ 11ዱ እስከ ወዲያኛው ተሸኙ፤12ቱ ክፉኛ
ቆሰሉ፤ የተቀሩት "አድኑን" ብለው የአማራ ልዩ ሀይልን
ተማፀኑ
➢ በመጨረሻም አፍኖ ሊወስድ የመጣ ወንበዴ ሙትና
ቁስለኛ ሆኖ ፣ ሽንፈትን ተከናንቦ በአማራ ልዩ ሀይል ታጅቦ
ተመለሰ
የሺ አለቃ ደጀኔ ማሩ ጀግንነት ግንባር ቀደም ነው።
ይች ቀን በየአመቱ '' ለመላው አማራ ብሎም
ለኢትዮጵያውያን የነፃነት ቀን ናት።
ደርበው አመሸ