Mereja Daily24

Mereja Daily24 This is official Page of Mereja Daily
Ethiopia's Information & Entertainment
Website.

30/08/2026

🇪🇹 Hidden Wonder of Ethiopia: Abune Yemata Guh ⛰️

High above the rugged cliffs of Tigray lies one of the most breathtaking and spiritual places on Earth — Abune Yemata Guh.

Carved into a vertical rock face, this ancient church is not just a destination… it’s an adventure. To reach it, you must climb steep cliffs, walk along narrow ledges, and overcome your fears. But at the top, a reward beyond imagination awaits.

Inside, centuries-old paintings still glow with vibrant colors — untouched by time, telling stories of faith, courage, and devotion. The silence, the view, the history… it all feels unreal.

This is not just a church.
This is a journey of belief, strength, and discovery.

✨ Would you dare to climb it?

ድህነት የአእምሮን መጠን ያሳንሳል፤ እርጅናንም ያፋጥናል ተባለ‼️​የረዥም ጊዜ ሳይንሳዊ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ዝቅተኛ ገቢና ስር የሰደደ የገንዘብ እጥረት የአእምሮን መጠን ለማሳነስና የአ...
30/08/2026

ድህነት የአእምሮን መጠን ያሳንሳል፤ እርጅናንም ያፋጥናል ተባለ‼️

​የረዥም ጊዜ ሳይንሳዊ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ዝቅተኛ ገቢና ስር የሰደደ የገንዘብ እጥረት የአእምሮን መጠን ለማሳነስና የአስተሳሰብ ብቃትን ለመቀነስ ምክንያት ይሆናሉ።

​በለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ (UCL) ተመራማሪዎች የተካሄደ አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው፣ በወጣትነት እና በጎልማሳነት እድሜ የሚከሰት ዘላቂ የገንዘብ እጥረት ወይም ዝቅተኛ ገቢ በዕድሜ መግፋት ወቅት የአእምሮ ህመም እና የማስታወስ ችሎታ መቀነስ አደጋን ያፋጥናል።

​በኢኖቬሽን ኢን ኤጅንግ ጆርናል ላይ የታተመው ይህ ጥናት በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ 2,759 ሰዎችን መረጃ መሠረት ያደረገ ነው።

ተመራማሪዎቹ የረጅም ጊዜ የገንዘብ ችግር ያጋጠማቸው ሰዎች በ53 ዓመታቸው ባደረጉት የአእምሮ ብቃት ምርመራ ዝቅተኛ ውጤት ማምጣታቸውን አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም ከ69 እስከ 71 ባለው እድሜ ውስጥ በኤምአርአይ (MRI) ስካን ከተመረመሩት መካከል፣ ለረጅም ጊዜ ዝቅተኛ ገቢ የነበራቸው ሰዎች ከፍተኛ የአእምሮ መንጠፋጠፍ ታይቶባቸዋል።

​ችግሩ በተለይም በወንዶች፣ በልጅነታቸው ችግር ውስጥ ባደጉ እና በአልዛይመር በሽታ የመያዝ አደጋን በሚጨምረው 'APOE-ε4' ጄን ተሸካሚዎች ላይ የጎላ ሆኖ ተገኝቷል።

በገንዘብ ጭንቀት የሚፈጠር የረጅም ጊዜ ውጥረት (chronic stress) ለአእምሮ እርጅና መፋጠን ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።

​በጥናቱ የተሳተፉ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች፣ ምንም እንኳ የትምህርት ደረጃቸውና የአእምሮ ብልህነት (IQ) ምጣኔያቸው ግምት ውስጥ ቢገባም፣ በትውስታና መረጃ የመተንተን ፍጥነት ፈተናዎች ላይ ዝቅተኛ ውጤት አስመዝግበዋል።

​የኤም.አር.አይ ምስል ምርመራዎች ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሰዎች ላይ ከፍተኛ የአእምሮ ሴሎች መኮማተር (Brain Atrophy) ታይቶባቸዋል።

​ስለ ገንዘብ ሁልጊዜ መጨነቅ በሰውነት ውስጥ እብጠትን (Inflammation) በመጨመር የሰውነትን የእርጅና ሂደት እንደሚያፋጥነው በጥናቱ ተገልፇል።

24/08/2026

#ኢትዮጵያ #አማርኛ #የኢትዮጵያ

 😂😂 ቡቺም መሪጌታ ጋር መሄድ ጀመረ ወይስ ጅቢቷን በፍቅር ጠብ አድርጓት ነው!🤔 ቡቺ ግን ምን ብሎ ቢያሳምናት ነው ጅቢቷን!
24/08/2026

😂

😂 ቡቺም መሪጌታ ጋር መሄድ ጀመረ ወይስ ጅቢቷን በፍቅር ጠብ አድርጓት ነው!

🤔 ቡቺ ግን ምን ብሎ ቢያሳምናት ነው ጅቢቷን!

    🙏💋
24/08/2026


🙏💋

😂 ፍርሀት መልክ ቢኖረው!😂😍
24/08/2026

😂 ፍርሀት መልክ ቢኖረው!😂😍

🤔ከዓመተ ምህረት➡ ወደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር‼️ዉድ ኢትዮጵያን በዚህ ጉዳየ ላይ የተሰማቸውን ነገር Comment ላይ ያስቀምጡ🙏🤔ዓመተ ምህርት (ዓ.ም) የሚለው የዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ አቆጣ...
24/08/2026

🤔ከዓመተ ምህረት➡ ወደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር‼️

ዉድ ኢትዮጵያን በዚህ ጉዳየ ላይ የተሰማቸውን ነገር Comment ላይ ያስቀምጡ🙏🤔

ዓመተ ምህርት (ዓ.ም) የሚለው የዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ አቆጣጠር (ኢ.አ) እንዲባል ስምምነት መደረሱ ተገለጸ‼️
ዓመት ምሕረት (ዓ.ም) የሚለው የዘመን አቆጣጠር እንዲቀር የተለያዩ ምክረ ሀሳቦች ሲቀርቡ የነበረ ሲሆን፣ ለ4ሺሕ ጉባያተኞች ተነቦ ኮሚሽኑ በተረከበው ሰነድ፣ ዓ.ም የሚለው ቀርቶ የኢትዮጵያ አቆጣጠር (ኢ.አ) እንዲባል ስምምነት መደረሱን ተመካካሪዎች ገልጸዋል። ሒጅራ እንደ ካላንደር ይካተት ተብሎ መያዙም ተገልጿል።

_ Ayu Zehabesha

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ምን አሉ ?(የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መግለጫ)- የዘንድሮው ውጤት ከአምናው በጥሩ ደረጃ ተሻሽሏል። - ተማሪዎችን ወደ ዩኒ...
24/08/2026

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ምን አሉ ?

(የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መግለጫ)

- የዘንድሮው ውጤት ከአምናው በጥሩ ደረጃ ተሻሽሏል።

- ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርስቲ አስገብቶ ማስፈተን በተጀመረበት የመጀመሪያ አመት ያለፉ 3.2% ፣ በሁለተኛው 2.9% ፣ በሶስተኛው 5.2% ፣ በአምናው አራተኛው ዓመት 8.9% ደረሰ አሁን በአምስተኛው ዓመት 12.8% ነው ያለፉት።

- ዘንድሮ በ2018 ብሔራዊ ፈተና የተመዘገበው ተማሪ ቁጥር 563,960 ሲሆን 550,210 ተማሪ ነው የተፈተነው።

- ፈተናውን ያለፈው ተማሪ ብዛት 70,544 ነው።

- ከተፈጥሮ ሳይንስ 16.6% አልፈዋል። ከማህበራዊ ሳንይስ 8.3% አልፈዋል።

#በፐርሰንት - ክልሎች ካስፈተኗቸው ተማሪዎች ምን ያህል ተማሪ አሳለፉ ? (ያሰፈተኗቸው ተማሪዎች ቁጥር ይለያያል)

1. አዲስ አበባ 32.3%
2. ሀረሪ 22.67%
3. አፋር 15.6%
4. አማራ 15.56%
5. ድሬዳዋ 11.29%
6. ትግራይ 11.2%
7. ኦሮሚያ 10.53%
8. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 9.23%
9. ሶማሌ 9.2%
10. ሲዳማ 6.95%
11. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 6.12%
12. ደቡብ ኢትዮጵያ 5.82%
13. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 4.92%
14. ጋምቤላ 3.74%

በቁጥር ምን ያህል ተማሪ ከየክልሉ አለፉ ? (ያስፈተኑት ቁጥር ይለያያል)

1. ኦሮሚያ ➡ 20,807 ተማሪዎች
2. አዲስ አበባ ➡ 18,646 ተማሪዎች
3. አማራ ➡ 15,225 ተማሪዎች
4. ትግራይ ➡ 3,146 ተማሪዎች
5. ደቡብ ኢትዮጵያ ➡ 3,011 ተማሪዎች
6. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ➡ 2,800 ተማሪዎች
7. ሲዳማ ➡ 1,827 ተማሪዎች
8. ሶማሌ ➡ 1,616 ተማሪዎች
9. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ➡ 835 ተማሪዎች
10. አፋር ➡ 705 ተማሪዎች
11. ሀረሪ ➡ 599 ተማሪዎች
12. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ➡ 457 ተማሪዎች
13. ድሬዳዋ ➡ 410 ተማሪዎች
14. ጋምቤላ ➡ 280 ተማሪዎች

- ባለፈው ዓመት ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች 1,232 ነበሩ ዘንድሮ ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 565 ናቸው።

- ከዚህ ቀደም ምንም ተማሪ ካላሳለፉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በኮፒዩተር ፈተና ወደ 4,500 ተማሪዎች አልፈዋል።

ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች በክልል ምን ያህል ናቸው ?

• ኦሮሚያ 156
• አማራ 98
• ደቡብ ኢትዮጵያ 86
• ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 69
• ትግራይ 48
• ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 29
• ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 22
• አፋር 21
• ሲዳማ 16
• ሶማሌ 9
• ድሬዳዋ 5
• ሀረሪ 3
• ጋምቤላ 2
• አዲስ አበባ 1

- ሁሉንም ያስፈተኑትን ተማሪዎች ያሳለፉ 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ባለፈው አመት 62 ነበሩ ዘንድሮ 88 ሆነዋል።

በክልሎች ምንም ያህል ትምህርት ቤቶች 100% አሳለፉ ?

• ኦሮሚያ 37
• አዲስ አበባ 24
• አማራ 8
• ደቡብ ኢትዮጵያ 4
• ትግራይ 4
• ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 3
• ሲዳማ 2
• አፋር 1
• ድሬዳዋ 1
• ሀረሪ 1
• ሶማሌ 1
• ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 1

- በኮምፕዩተር እና በወረቀት በተፈተኑ ተማሪዎች መካከል ያለው የማለፍ ምጣኔ ትልቅ ልዩነት አለው። ኦንላይ የተፈተኑ 18.3% አልፈዋል። በወረቀት የወሰዱ 4.2% ናቸው ያለፉት። አንዱ ቶሎ በወረቀት ከመፈተን መውጥቶ ኦላይን ለመስጠት እቅድ አለው 60% ነው ዘንድሮ ቀጣይ አመት 100% ኦንላይን ሁሉንም።

- የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት ስንት ነው ?

• በተፈጥሮ ሳይንስ •
🥇 ከወንድ 👉 591/600 ኦዳ ስፔሻል ቦርንዲግ ትምህርት ቤት አዳማ
🥇 ከሴት 👉 583/600 ከአገው ምድር ትምህርት ቤት እንጅባራ

• በማህበራዊ ሳንይንስ •
🥇 ከወንድ 👉 576/600 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት
🥇 ከሴት 👉 569/600 አዲስ አበባ ቦሌ ሱፐርሆሊሴቪየር ትምህርት ቤት

- ስልክ ይዘው የገቡ 265 ተማሪዎች ከፈተናው ተሰርዘዋል።

- ኮምፒዩተር ላይ ባለ " ኢሬጉላተሪ " ተብለው ጉዳያቸው እየተጣራ ያለ አለ።

- ከዚህ በፊት ከነበረው መሻሻል እየታየ ስለሆነ በጣም ደስተኞች ነን።

- ዘንድሮም ወደ ሬሜዲያል የሚገቡ ተማሪዎች ይኖራሉ።

- ሬሜዲያል ሁሌ የሚኖር አይደለም። በሚያልፈው ተማሪ ብዛት ነው የሚወሰነው። ዘንድሮ 70 ሺህ ተማሪ ስላለፈ ዘንድሮ ሬሜዲያል የሚገባው ይቀንሳል።

📌 ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ሰኞ ወይም ከነገ ወዲያ ማክሰኞ ጀምሮ ውጤታቸው ማየት ይችላሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዎች ውጤት የሚመለከቱባቸውን አማራጮች ተከታትሎ ያቀርባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም

20/08/2026

ሞጣ ይለያል የምንለው በምክንያት ነዉ😂😭
ማድረግ እንዳይረሳ ተናግሬለዉ💋🙏😂

Address

Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mereja Daily24 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mereja Daily24:

Shortcuts

Share