Molalegn Haile

Molalegn Haile Where is justice? ???

10/03/2026
ሚያዚያ 19/2017   👉በስመ   አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን   በዳግም ትንሣኤ ለምናከብርበት ለመልአኩ   ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን           እ...
27/04/2025

ሚያዚያ 19/2017

👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን በዳግም ትንሣኤ ለምናከብርበት ለመልአኩ ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን

እኔ #በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው #ገብርኤል ነኝ
ሉቃ.1፥19
👉ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ዘመኑ ጣኦት የሚመለክበት ንጉስ ናቡከደነፆር በባቢሎን ምርኮ የወሰዳቸው #የእግዚአብሔር ሰዎች አናንያ፤ አዛርያ፤ ሚሣኤል እጅግ ይወዳቸው ነበር

👉ከባቢሎናውይን ይልቅ በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ሦስት ሰፍሮ በምናገኘው ታሪካቸው እንደሚግረን ንጉሱ የጣኦት ምስል አሰራ በገሊላ አውራጃ ያለውን ሕዝብ ጠርቶ ለጣኦቴ ያልሰገደ ወደ እሳት ውስጥ ይጣላል ብሎ አወጀ የንጉስ ትዕዛዝ ነውና ሕዝቡ ሁሉ ለጣዖቱ ሲንበረከክ እነርሱ ግን ቆመው ያዩ ነበር

👉ናቡከደነፆር እርሱ ላስቆመው ጣኦት አለመስገዳቸውን ሲሰማ ተናደደ፤ ተበሳጨም እሳቱን 7 እጥፍ እንዲነድ አስደረገ ሦስቱንም አስሮ እሣቱን እያሳየ "ከመቃጠል ወይስ ለእኔ ጣኦት መስገድ የቱ ይሻላል?" ቢላቸውም #የእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምንም ነገር አያስፈራውምና የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶን ሊያድነን ይችላል ባያድነንም ግን አንተ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም አሉት

👉በዚህ ጊዜ ጉልበት ያላቸው ሠዎች ተፈልገው ሦስቱን ወጣቶች አስረው ወደ እሳት ቶን ውስጥ ጣሏቸው አስረው የጣሉቸው ወታደሮች የእሳቱ ወላፈን አቃጠላቸው ግን መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አበረደላቸው አጠፋላቸው

👉በዚህም ጊዜ ንጉስ ናቡከደነፆር እንዲህ በማለት መሰከረ "እኛ አስረን የጣልናቸው ሦስት ነበሩ አሁን ግን አራተኛው ሰው በእሳቱ ሲመላለስ ይታየኛል የአራተኛው መልክ ደግሞ #የአማልክትን መልክ ይመስላል አለ #የእግዚአብሔር የማዳኑ ስራ ሲገለጥ ቅዱስ ገብርኤል ሲታይ አዋጁ ሁሉ ተሻረ ጉልበት ሁሉ ለጣኦት ይስገድ ተብሎ የነበረው አዋጅ ተሽሮ ጉልበት ሁሉ ለሠለስቱ ደቂቅ አምላክ የሚል አዋጅ ታወጀ

👉የስሙ ትርጓሜ ታማኝ አገልጋይ የሆነው በዘመናችንም ለበርካቶች ታላቅ ተአምራት ሰርቷል ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ጥበቃው ረድኤት በረከቱ አይለየንና ገዳማውያን አባቶችና እናቶች እንደ ባቢሎን እሳት በነደደው ስጋዊ ፍላጎት ውስጥ አሸናፊ እንዲሆኑ የሚረዳቸውም ነው ገዳማውያኑ ሲሉትም በረከታቸው አብሮን እንዲሆን ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናፅና

👉ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ
141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

👉ሰለሞን የገብርኤል ሚያዚያ 19/2017

ለጊዮርጊስ ወዳጆች.....
25/04/2025

ለጊዮርጊስ ወዳጆች.....

 #አስቸኳይ መረጃ ባህር ዳር‼️የኦህዴድ መራሹ የብልፅግና ፋሽት ስርዓት በመሪያችን ፣በምልክታችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ላይ ጥቃት ሊፈፅም እንደሆነ መረጃ ደርሶናል ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር ...
01/08/2023

#አስቸኳይ መረጃ ባህር ዳር‼️
የኦህዴድ መራሹ የብልፅግና ፋሽት ስርዓት በመሪያችን ፣በምልክታችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ላይ ጥቃት ሊፈፅም እንደሆነ መረጃ ደርሶናል ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር አስታወቀ‼

ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
አሻራ ሚዲያ ፣

በአማራ ክልል በጦርነት በተነኮሳቸው አካባቢዎች መራራ ሽንፈትን እየተጎነጨ የሚገኘወው ታዛዢ ሰራዊት ምልክታችን አርበኛ ዘመነ ካሴ እና ሌሎች የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ለመግደል ተልኮ ተሰጦት በዛሬው ዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሆኑ ከታማኝ ምንጭ ማረጋገጥ ችለናል ።

በመሆኑም መላው የባህር ዳር ከተማና አካባቢው ወጣቶች ፣የጎጃም ቀጠና ፋኖ እንዲሁም መላው ህዝብ ከዚህ ደቂቃ ጀምሮ የምናደርገውን ጥሪ በንቃት ፣በአይነ ቁራኛ ሁሉንም ነገር እንዲከታተል የአማራ ወጣቶች ማህበር ጥሪውን ያስተላልፋል ።

ድል ለአማራ ፋኖ ‼️
ድል ለአማራ ህዝብ‼️

ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-
//
Youtube:- Ashara Tv - https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng

//
https://www.facebook.com/asharamedia24
//
ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

ከቤተ አምሓራ ፋኖ የተሰጠ ማስጠንቀቂያቤተ አምሓራ ፋኖ በደሴየአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ በተደቀነበት በዚህ ፈታኝ ወቅት ጥቂት የነቁ ወጣቶች ብቻ አያደረጉት ባለው እልህ አስጨራሽ ትግል እዚ...
01/08/2023

ከቤተ አምሓራ ፋኖ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ

ቤተ አምሓራ ፋኖ በደሴ

የአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ በተደቀነበት በዚህ ፈታኝ ወቅት ጥቂት የነቁ ወጣቶች ብቻ አያደረጉት ባለው እልህ አስጨራሽ ትግል እዚህ ደርስናል።ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣት ደግሞ በሱስ ተጠምዶ ይገኛል። ስለዚህ በዚህ ታሪካዊ ትግል ላይ እድሜው የሚፈቅድለት የአማራ ህዝብ መታገል እንዳለበት ስለምናምን ህዝቡ በተለይም ወጣቱ የመጣበትን የህልውና አደጋ ተገንዝቦ በአንድ ሀይል ነቅቶና ተግቶ መልስ እንዳይሰጥ የግል ጥቅማችሁን በማሰብ

* በቤቲንግ ቁማር

★ በጫት መቃሚያ ቤቶች

★ በሺሻ ማጨሻ ቤቶች

★ በጭፈራ ቤቶች

★ በጃንቦ ቤቶች

ተጠቃሚና አስጠቃሚዎች ላይ የቤተ አምሓራ ፋኖ በደሴ የማይቋረጥ ተከታታይ እርምጃ ስለ- ሚወስድ በዚህ የማደንዘዝ እና የመደንዘዝ ተግባር ላይ ለምትሳተፉ አካላት ለሚወሰድባችሁ ማንኛውም እርምጃ ሃላፊነቱን እራሳችሁ እንደምትወስዱ እየገለፅን ይሄንን ማስጠንቀቂያ ከዛሬ ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን እናሳስባለን።

ቤተ አምሓራ ፋኖ በደሴ

 #🔥 በነበልባሉ ሻለቃ እሱባለው ሲሳይ የሚመራው አንድ አማራ ፋኖ አንችን ብርጌድ መቄትን ተቆጣጠረ‼ሐምሌ 21 ቀን 2015 ዓ.ምአሻራ ሚዲያ ፣በሻለቃ እሱባለው ሲሳይ የሚመራው አንድ አማራ ፋ...
28/07/2023

#🔥 በነበልባሉ ሻለቃ እሱባለው ሲሳይ የሚመራው አንድ አማራ ፋኖ አንችን ብርጌድ መቄትን ተቆጣጠረ‼

ሐምሌ 21 ቀን 2015 ዓ.ም
አሻራ ሚዲያ ፣

በሻለቃ እሱባለው ሲሳይ የሚመራው አንድ አማራ ፋኖ አንችን ብርጌድ የሰሜን ወሎ ኮከቦች ፥መቄት ላይ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ነፃነት የራበው ፣ጭቆና የበዛበት ህዝባችን በነቂስ ወጥቶ የቁርጥ ቀን ልጆቹን(ፋኖ) በዚህ መልኩ ተቀብሏል ።

በዛሬው ዕለት በሰሜን ወሎ ዞን የመቄት ወረዳ ፣ የገረገራ ከተማ በአማራ ፋኖ ቁጥጥር ስር ገብተዋል ።የአማራ ፋኖ ገረገራ ክተማ ሲገባ በገረገራ ከተማ የአማራ ህዝብ ደማቅ አቀባበል ሲደረግለት ህዝቡም ይለያል! ይለያል! ይለያል !ዘንድሮ የብልጽግና ኑሮ በማለት እየጨፈረ ፋኖን መቀበሉን ታውቋል ።

በዚህም የህዝቡን ድጋፍና ስሜቱን ያየው የከተማው ፖሊስ እና ሚኒሻ በመበሳጨት ወደ ህዝቡ ለመተኮስ በህንጻወች አናት ላይ ተሰግስገው መቀመጣቸውን የህዝብ ልጅ ለሆነው ፣ለመከታችን ፣አለኝታችን ፣የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ ( ፋኖ) መረጃው ቀድሞ በመድረሱ አናብስቱ ፣ቅንድም የማይስተው ፋኖ ተከታታይ ተኩስ ሲተኩስባቸው ሁሉም ተበታትነው እምጥ ይግቡ ስምጥ አልታወቀም።

የአማራ ፋኖ አሁንም እንደዚህ የምታደርጉ የገዥው ስርዓት ታዛዥ የፀጥታ አካላት አደብ ግዙ !
ብትችሉ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነውን (ፋኖን) ተቀላቀሉ ፣ካልቻላችሁ አርፋችሁ ቁጭ በሉ በማለት የመጨረሻ ጥሪያችን እናስተላልፋለን ።

በመቄት ወረዳ በፋኖ ላይ ይሄን ያክል ሴራ እያሴረ ያለው የከተማው የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው አቶ መካሽ መሆኑ ታውቋል ።ሆኖም ግን በአስተዋይነቱ የሚታወቀው የአማራ ፋኖ አደረጃጀት
የሰውየውን ክፋት በምክር መልክ እዳለፈው አውቀናል ።ብታርፍ ይሻላል!!

በዛሬው ዕለትም በምስራቅ አማራ ፋኖ ስር የመቄት ወረዳ አንችም ፋኖ ብሎ ተደራጅቶ ታላቅ ተግባራትን እየሰራ ይገኛል ።

ድል ለአማራ ፋኖ‼️
ድል ለአማራ ህዝብ‼️

"ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።"

ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-
//
Youtube:- Ashara Tv - https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng

//
https://www.facebook.com/asharamedia24
//
ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

ብአዴን እየተመናመነ ነው!የወልድያ ከተማ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ዋና ኃላፊ ኮማንደር አሻግሬ ተስፋው በራሳቸው ፈቃድ የሥራ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተው ከስራ ለቀዋል፡፡ኮማንደሩ በብዙ የኃላፊ...
28/07/2023

ብአዴን እየተመናመነ ነው!

የወልድያ ከተማ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ዋና ኃላፊ ኮማንደር አሻግሬ ተስፋው በራሳቸው ፈቃድ የሥራ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተው ከስራ ለቀዋል፡፡

ኮማንደሩ በብዙ የኃላፊነት ቦታወች ከህዝብ ጎን ሆነው የሠሩ እና በህወሀት ወረራ ጊዜም ግንባር ድረስ በመግባት እስከ መቁሠል ድረስ ዋጋ የከፈሉ ጀግና ናቸው፡፡ የከተማዋ ዲክታተር ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ "በፋኖ ላይ ዝመቱ፤ ከፋኖ ጎን ናችሁ፤ እንዲሁም የፋኖ አሸናፊ አለሙ ቤተሠብ ነህ" እያለ ሲያቀረሽ ከዋለ በኋላ ቆራጡ ሰው ወደፋኖ አልዘምትም ከቻልኩ እደግፋለሁ ብለው በኩራት ጥለውት ወጥተዋል፡፡

Address

Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Molalegn Haile posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Molalegn Haile:

Share