12/04/2026
ለዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ፣ ለተማሪዎቻችንና ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፤
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ ይህ ታላቅ ዕለት ክርስቶስ በመስቀል ላይ በከፈለው መሥዋዕትነት የኃጢአት ዕዳን ያስወገደበት፣ በሞቱ ሞትን ድል አድርጎ የሕይወትን ብርሃን ያበሠረበትና የመዳናችን ምሥጢር የተፈጸመበት ነው።
ትንሣኤ የድል፣ የሰላምና የፍቅር በዓል ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር አንድነትን በማጠናከር፣ የተቸገሩትን በመደገፍና የበዓሉን መንፈሳዊ እሴቶች ወደ ተግባር በመለወጥ ለሀገራችን ሰላምና ወንድማማችነት መጠናከር የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል።
በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ።
መልካም በዓለ ትንሣኤ!
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ሚያዝያ 3 ቀን 2018ዓ.ም
To our University Community, our Students, and all those celebrating the Christian Resurrection:
I would like to extend my warmest wishes to you all for a peaceful Easter.
On this sacred day, through the Resurrection of Christ, we reflect on the profound transition from deep darkness to a marvelous light, from death to life, and from humiliation to glory. This great day marks the victory over death, the abolishment of the debt of sin through the sacrifice on the Cross, and the ultimate fulfillment of the mystery of salvation.
Easter is a festival of victory, peace, and love. As we celebrate, we should do so by strengthening our unity, supporting those in need, and translating the spiritual values of the season into action to contribute our part toward national peace and brotherhood.
I sincerely wish you a holiday filled with peace, health, and happiness.
Happy Easter!
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
April 11, 2026