
02/05/2025
ሰበር ዜና
በመጅሊሱ ጉዳይ የሀገር አቀፍ ቅሬታ አቅራቢ ግብረሀይል የመንግስት ተወካዮች ባሉበት በመጅሊስ ግቢ ድርድር አካሂደናል
እንደሚታወቀዉ አሁን ያለዉ መጅሊስ የመጅሊስን መንበረ ስልጣን ከተቆናጠጠ ጀምሮ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የሚደርሱ በደሎች ጭቆናዎች ፣ ማሣደድ የመጅሊሱ መዋቅር አካታች አለመሆን አስመልክቶ ለሰላም ሚኒሰተር ጨምሮ ለተለያዩ ለሚመለከታቸዉ የመንግስት ተቋማት ማስገባታቸዉ ይታወቃል
ሀገር አቀፍ ግብረሀይሉ ይህንን የአህለ ሱና ወል ጀምዓ (የሱፍያ) ህዝበ ሙስሊም ጥያቄ በተመለከተ ለመጀመሪያ ግዜ በመንግስት አመቻችነት ከሰላም ሚኒስተር ጋር ዉይይት ማካሄዱ በቀጣይነት ቀጠሮ መያዙ መግለፃችንም ይታወሳል
በዚህ መሠረት ትላንት ሐሙስ ሚያዝያ 23/8/17 በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፅ/ቤት በመንግስት አዘጋጅነት ከሀገር አቀፍ ግብረሀይሉ ከተለያየ ክልል የተወጣጡ ዑለሞች ፣የሀሪማ ባለቤቶች ፣ወጣቶች እና ምሁራን በመገኘት የሰላም ሚኒስተር ተወካዮች ባሉበት የድርድሩ የዉይይት ሀሳቦች ቀርበዉ ዉይይት ተካሂዶባቸዋል
የሀገር አቀፉ ታስክ ፎርስ ግብረ ሀይል(ኮሚቴ) መጅሊሱ አካታች ባለመሆኑ ሁሉን አካታች እንዲሆን ፣ ቀድመዉ የተሰሩ የዑለማእ መግባቢያ ሰነዶች ፣የመጅሊሱ መተዳደሪያ ደንብ ፣እንዲሁም የመጅሊስ የምርጫ ደንብ በድጋሚ ታይተዉ ተፈትሸዉ ሁሉን ባማከለ መልኩ ተስተካክለዉ እንዲከለሱ ፣ በየመስጂዱ ፣በየ መድረሳዉ ፣በኢማሞች ፣ በሙአዚኖች በሰራተኞች ላይ ሆን ተብሎ የተፈፀሙ በደሎች ጭቆናዎች የመጅሊሱ አሳሳሪነት ራሱንም አስፈቺ እንደሆነ ባጠቃላይ መጅሊሱ ከመጣ ወዲህ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተፈፀሙ ወንጀሎች በዝርዝር ቀርቧል
ተወካዮቻችን ከመጅሊስ ከተወከሉ አካላት ጋር ዉይይቶች የመንግስት ተወካይ አካላት በተገኙበት ዉይይት ከተካሄደ በሗላ ቀጣይ ቀጠሮዎች ይዘዉ ተለያይተዋል
ኢንሻአላህ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚገኘዉ መላዉ አህለ ሱና ወል ጀምዓ(ሱፍያ) ህዝባችን በመረጋጋት በንቃት ጥያቄያችን እስኪመለስ ከዳር እስክናደርሰዉ ከጎኑ በመሆን እንድትከታተሉና እንድትደግፉ አደራ እንላለን
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሀገር አቀፍ ታስክ ፎርሱ (ግብረ ሀይል) በቅርቡ ሂደቱን አስመልክቶ በዝርዝር መግለጫ የሚሠጥ ይሆናልና ህዝበ ሙስሊሙ በመላው ሀገሪቷ ነቅቶ ሊዘጋጅ ሊደራጅ ይገባል
የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማሕበር