23/07/2026
የትውልድ መጥፍያ ምክኛት የነበሩ መንትያዎች!!
ኢህአፓ «መንግሥት በትግራይ ጦርነት ሊቀሰቅስ ነው» በማለት የሚያሰማው የሰላም ተቆርቋሪነት ጩኸት፣ ከህወሓት ጋር ያለውን አጥፊና የሴራ ፖለቲካ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ሁለቱም ቡድኖች በታሪካቸው በጽንፈኝነት፣ በዜሮ ድምር እሳቤ እና በኃይል መንገድ የተጠመቁ የትርምስ ምንጮች ናቸው። ትናንት ትውልድ ያስፈጀው ኢህአፓ ዛሬ ሀገር ካደማው ህወሓት ጋር ተሻርኮ የሚያሰማው የግብዝነት አቋም፣ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሽፋን በማድረግ ሀገርን ዳግም ወደ ግጭት ለመክተት የተሸረበ የፖለቲካ ሸፍጥ ነው።