Libo Tv News

Libo Tv News "Passionate digital creator sharing creativity through videos, designs, and unique content. Here to inspire, entertain, and connect with fellow creatives!

Let’s make something amazing together ✨"

Feel free to tweak it according to your style!

04/06/2025
29/05/2025

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አነጋጋሪ መልዕክት አስተላለፉ || በኢትዮጵያ የዶላር 128 በመቶ ጭማሪ || ኢላን መስክ ከትራምፕ አስተዳደር ራሱን አገለለ

ወጣት ቱርካዊያን ተማሪዎች የኤርዶዋን አገዛዝ በቃን ብለው ጎዳና የወጡት ለምንድነው?ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ወጣት ቱርካዊያን ተማሪዎች የፎቶው ባለመብት29 መጋቢት 2025የቱርኩ ፕሬዝደንት ...
30/03/2025

ወጣት ቱርካዊያን ተማሪዎች የኤርዶዋን አገዛዝ በቃን ብለው ጎዳና የወጡት ለምንድነው?
ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ወጣት ቱርካዊያን ተማሪዎች የፎቶው ባለመብት
29 መጋቢት 2025
የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶዋን ቀንደኛ ተቃዋሚ የሆኑት የኢስታንቡል ከንቲባ የሆኑት ኢማሞግሉ መታሰራቸውን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ ቢያንስ 2 ሺህ ያክል ሰዎች ታስረዋል።

አብዛኛዎቹ ታሳሪዎች ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው። ተማሪዎች ድምፃቸውን ለማሰማት አደባባይ ወጥተዋል።

ምንም እንኳን በሀገሪቱ ትልቋ ከተማ በሆነችው ኢስታንቡል ውስጥ ተቃውሞ ማድረግ ቢከለከልም ተማሪዎች ግን ይህ እግድ ሳያቆማቸው በየቀኑ ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

የሚገናኙት የከተማዋ ንዑስ አደባባይ በሆነው ሳራቼን ፓርክ ነው።

አመሻሹን ተገናኝተው የሚያሰሙት ተቃውሞ በፖሊስ አስለቃሽ ጭስ፣ የፕላስቲክ ጥይት እና ግፊት ያለው ውሀ የታጀበ ነው።

የኢማሞግሉ ሪፐብሊካን ፒፕልስ ፓርቲ አሊያም ሲኤችፒ ከሰሞኑ ስትራቴጂውን የቀየረ ይመስላል። በአደባባይ መሰባሰቡ እንደማያዋጣ ለደጋፊዎቹ አሳውቋል።

በምትኩ የፓርቲው ደጋፊዎች ከቤታቸው ሆነው በማጨብጨብ፣ የመኪና ጥሩንባ በማሰማት እና በመስኮታቸው በኩል ባንዲራ በማውለብለብ ተቃውሞቸውን እንዲገልፁ ጠይቋል።

ፓርቲው ቅዳሜ ታላቅ ያለውን የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ አቅዷል። ምንም እንኳ በኢስታንቡል የተቃውሞ ሰልፍ ቢከለከልም ቅስቀሳ ማድረግ ግን ይቻላል።

ተማሪዎቹ ግን ምንም የሚያግዳቸው አይመስልም።

መሐል ኢስታንቡል ማካ ፓርክ የተሰባሰቡ ተማሪዎች ማንነታቸው እንዳይለይ የፊት ጭምብል አጥልቀዋል። ፎቶ መነሳት አይፈልጉም። ለሚያናግራቸው ሰውም ትክክለኛ ማንነታቸውን አይገልጡም።

"ሕልማችን ተቃውሞ ስናሰማ ፊታችንን የማንሸፍንበት ሀገር እንደትኖረን ነው" ሲል አንድ ተማሪ ለቢቢሲ ይናገራል።

ፕሬዝደንት ኤርዶዋን ጭምብል ያጠለቁ ሰልፈኞችን "አሸባሪዎች ናቸው" ሲል ገልፀዋቸዋል።

'የተመረጠ ፍትሕ'
ኢማሞግሉ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በአውሮፓውኑ መጋቢት 19 ነው። በይፋ የቀረረባቸው ክስ ሙስና ሰርተዋል ይላል።

የሲኤችፒ ፓርቲ ዕጩ ሆነው በተመረጡ ቀን ነው ክስ ተመስርቶባቸው የፍርድ ሒደቱ እስኪጀመር ድረስ በቁጥጥር ሥር እንዲቆይ የተደረገው።

ተቃውሚ ፓርቲው ኢማሞግሉ ላይ የቀረበው ክስ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ነው ብሎ የከንቲባው መታሰር "መፈንቅለ መንግሥት ነው" ሲል ይከሳል። ኤርዶዋን ይህን ወቀሳ አይቀበሉትም።
ምንም እንኳ በማካ ፓርክ ለተቃውሞ የወጡ ተማሪዎች ከየትኛውም ፓርቲ ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ቢገልፁም "መብት፣ ሕግ እና ፍትሕ" የተሰኘውን የተቃውሚ ፓርቲ መፈክር ሲያሰሙ ታይተዋል።

"ያለንበት ሁኔታ ተመልከቱት እስቲ" የአንድ ተማሪ ድምፅ ነው። "ሰዎች ፍርድ ቤት እንኳ ሳይቀርቡ ነው ለእስር እየተዳረጉ ያሉት።"

ሌላኛው ተማሪ ደግሞ የተመረጠ ፍትሕ አለ ሲል ያማራል።

"ይሄ የኢማሞግሉ መታሰር ጉዳይ ብቻ አይደለም። ሌሎች [በሙስና የተጠረጠሩ] ለምን ምርመራ አይደረግባቸውም" ይላል።

አብዛኛዎቹ ተማሪዎች የፍትሕ ሥርዓቱ ገለልተኛ አይደለም ባይ ናቸው።

"ፍርድ ቤት ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ እንዲሆን እንፈልጋለን" የሚሉ ተማሪዎች አሉ። የቱርክ መንግሥት ፍርድ ቤቶች ገለልተኛ በሆነ መንገድ ነው የሚያገለግሉት የሚል ምላሽ አለው።

ከፍርድ ቤት ገለልተኛነት በተጨማሪ ምጣኔ ሀብታዊ አለመረጋጋት፣ ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መጨመር እና የወደፊት ዕጣቸው ምን ሊሆን እንደሚችል አለማወቃቸው ተማሪዎቹ አደባባይ እንዲወጡ እንዳደረጋቸው ይናገራሉ።

ኢማሞግሉ ከዩኒቨርሲቲ ያገኙት ዲፕሎማ እንዲሰረዝ መደረጉ ተሰምቷል። ይህ ማለት ለፕሬዝደንታዊ ምርጫ ዕጩ ሆነው መቅረብ አይችሉም ማለት ነው።

"የእሱን ዲፕሎማ ነጠቁ ማለት የኛንም ላለመንጠቃቸው ምንም ማረጋገጫ የለውም ማለት ነው" ሲል አንድ ተማሪ ይጠይቃል።

ምንም እንኳ በቱርክ ያለው ሁኔታ አስተማማኝ ባይሆንም ሁሉም ወጣቶች ሀገሪቱን ጥለው ለመሄድ ፈቃደኛ አይደሉም።

"አብዛኛዎቹ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጓደኞቼ ወደ ውጭ ሀገር ሄደዋል። እኔ ግን መውጣት አልፈልግም። ወጣት ቱርካዊ ነኝ። ወደፊት መኖር የምፈልገው እዚህ ነው።"

ነፃ ንቅናቄ
ሲኤችፒ ፓርቲ ማታ ማታ በሳራቼን ፓርክ እንዲቋረጥ ቢያደርግም ተቃውሞው ግን የተቋረጠ አይመስልም።

ፓርቲው በአዳዲስ መሰባሰቢያ ቦታዎች ቅስቀሳ ለማድረግ ሐሳብ እንዳለው አሳውቋል። ወጣቶቹ ግን አደባባይ ወጥተው ሰልፍ ማድረግ ይሻሉ።

"ለኢማሞግሉ ስንል ብቻ አይደለም ወደ አደባባይ የወጣነው። ለዲሞክራሲም ጭምር ነው። ተቃውሞ የምንወጣባቸው በርካታ አደባባዮች አሉን" የአንድ ተማሪ አስተያየት ነው።

ሌላ ተማሪ ደግሞ ፓርቲው ስትራቴጂውን መቀየሩን ተቃውሞ ንቅናቄው ገለልተኛ እንዲሆን ይጠይቃል።

"የፓርቲው መሪ የሚሉት ነገር እኛን አይመለከተንም። የራሳችንን ውሳኔ መወሰን እንችላለን። በነፃ ንቅናቄ ሁኔታዎችን መቀየር እንችላለን። የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አያስፈልገንም።"
ተማሪዎቹ ጎዳና በመውጣት እና ምጣኔ ሀብታዊ አድማ በመምታት በተቃውሟቸው ለመቀጠል ቆርጠዋል።

ሕዝቡ "ፖለቲካዊ ዕውቀት እንዲጨብጥ" እንሻለን የሚሉት ተማሪዎች የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን እውነታውን ሸሽገዋል ሲሉ ይወቅሳሉ።

"ከሚድያ የምናገኘው ዜና ከመንግሥት እውቅና የተሰጠው ነው። መንገድ ላይ ያለውን ስንመለከት ግን እውነታው ሌላ ነው። ፖሊስ ምን ኃይል እየተጠቀመ እንዳለ እና ተቃዋሚዎቹ ተንኳሽ ናቸው ወይ የሚለውን መመልከት ይቻላል።"

የቱርክ ሚዲያ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን የተቃውሞው ዘገባ ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር አጥብቋል። በያዝነው ሳምንት መባቻ ከተቃውሚ ፓርቲ ጋር ግንኙነት ያላቸውና ገለልተኛ መገናኛ ብዙኃን ሊታገዱ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል።

ተቃውሞን ሲዘግብ የነበረውን የቢቢሲ ሪፖርተር ማርክ ሎዌን "የሕዝብ ሰላም ይበጠብጣል" በማለት ቱርክ ከሃገር እንዲወጣ ማድረጓን ቢቢሲ ተናግሯል።

ሎዌን ኢስታንቡል ከሚገኝ ሆቴል ተወስዶ እንደነበር የቢቢሲ ኒውስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዴቦራህ ተርነስ አሳውቀዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የታሰሩ እስኪፈቱ ድረስ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንደማይመለሱ ቃል ገብተዋል።

ተማሪዎች በመላ ሀገሪቱ ተቃውሞ እንዲፋፋም ጥሪ ያቀርባሉ።

"ሁሉም ሠራተኞች፣ ፕሮፌሽናል ድርጅቶች እንዲቀላቀሉን ጥሪ እናቀርባለን። ሕዝባዊ ተቃውሞ ያሻል። ሁሉም ነገር ፀጥ ረጭ እንዲል ማድረግ አለብን" ይላል አንድ ተማሪ።

በትራምፕ አስተዳደር ምክንያት የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሥራ ለቀቁየጋዛን ጦርነት ለመቃወም አደባባይ የወጡ ሰዎችየፎቶው ባለመብት29 መጋቢት 2025የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ጊዜያዊ ፕሬዝዳ...
30/03/2025

በትራምፕ አስተዳደር ምክንያት የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሥራ ለቀቁ
የጋዛን ጦርነት ለመቃወም አደባባይ የወጡ ሰዎችየፎቶው ባለመብት
29 መጋቢት 2025
የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት በትራምፕ አስተዳደር ምክንያት ከሥራቸው ለቀቁ።

ዩኒቨርስቲውን ከነሐሴ ጀምሮ እየመሩ ያሉት ካትሪና አርምስትሮንግ በዩኒቨርስቲው እየተደረገ ባለው ለውጥ ምክንያት ነው ከሥራቸው ለመልቀቅ የወሰኑት።

ከሳቸው ቀድመው የነበሩት ፕሬዝዳንት የተማሪዎችን የጋዛ ጦርነት ተቃውሞ በተመለከተ በተከተሉት አሠራር ምክንያት ነበር ከሥልጣን የወረዱት።

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን አስተዳደር ለማስደሰት በሚል ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ የፖሊሲ ለውጦች ለማድረግ ከአንድ ሳምንት በፊት ተስማምቷል።

ይህንን ስምምነት ተከትሎም ጊዜያዊ ፕሬዝዳንቷ ለመልቀቅ ወስነዋል።

ትራምፕ ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ እና ሌሎችም ዩኒቨርስቲዎች "ፀረ ሴማዊነትን እና አይሁዳውያን ተማሪዎች ላይ የሚደርስ ጥቃትን ታግሰዋል" ብለው ሲተቹ ነበር።

የጋዛ ጦርነት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የተካሄደባቸውን ዩኒቨርስቲዎች ዒላማ ያደረጉት ትራምፕ፣ ለዩኒቨርስቲው ወደ 400 ሚሊዮን ዶላር የፌደራል መንግሥት በጀት እንደማይለቁም ሲዝቱ ተደምጠዋል።

ከፕሬዝዳንትነት የለቀቁት ካትሪና ቀድሞ ወደነበራቸው የዩኒቨርስቲው የሕክምና ክፍል ኃላፊነት የሚመለሱ ይሆናል።

የዩኒቨርስቲው የቦርድ አጋር ሊቀ መንበር ክሌር ሺፕማን ይተኳቸዋል ተብሏል።
ትራምፕ ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ እና ሌሎችም ዩኒቨርስቲዎች "ፀረ ሴማዊነትን እና አይሁዳውያን ተማሪዎች ላይ የሚደርስ ጥቃትን ታግሰዋል" ብለው ሲተቹ ነበር።

የጋዛ ጦርነት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የተካሄደባቸውን ዩኒቨርስቲዎች ዒላማ ያደረጉት ትራምፕ፣ ለዩኒቨርስቲው ወደ 400 ሚሊዮን ዶላር የፌደራል መንግሥት በጀት እንደማይለቁም ሲዝቱ ተደምጠዋል።

ከፕሬዝዳንትነት የለቀቁት ካትሪና ቀድሞ ወደነበራቸው የዩኒቨርስቲው የሕክምና ክፍል ኃላፊነት የሚመለሱ ይሆናል።

የዩኒቨርስቲው የቦርድ አጋር ሊቀ መንበር ክሌር ሺፕማን ይተኳቸዋል።

"ኃላፊነቱን የምቀበለው ከባድ ጊዜ እንደሚጠብቀን በመረዳት ነው። የዩኒቨርስቲውን ዓላማ ለማሳካትና አስፈላጊ ለውጥ ለማምጣት እሠራለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

የዩኒቨርስቲው የቦርድ ባለ አደራ ኃላፊ ዴቪድ ጄ ግሪንዋልድ "ዶ/ር ካትሪና አርምስትሮንግ ኃላፊነቱን የወሰደችው በዩኒቨርስቲው ታሪክ ፈታኝ በሆነ ወቅት ነው። ያለመታከትም አገልግላለች" ብለዋል።

ዩኒቨርስቲው በትራምፕ አስተዳደር ጫና ምክንያት ተቃውሞዎች ሲካሄዱ ተማሪዎች የፊት ጭምብል እንዳያጠልቁ ለመከልከል ተስማምቷል።

የተወሰኑ የትምህርት ክፍሎች ላይም ለውጥ ለማድረስ ከስምምነት ደርሷል።

የጋዛን ጦርነትና አሜሪካ ለእስራኤል የምታደርገውን ድጋፍ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፎች መካሄድ የጀመሩት ከኒው ዮርክ ኮሌጅ ነው።

ከኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ በተጨማሪ 60 ዩኒቨርስቲዎች የፌደራል መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እንደሚቋረጥባቸው ትራምፕ አስታውቀዋል።

የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ተመራቂው የመብት ተሟጋች ማሕሙድ ካሊል በፌደራል መንግሥቱ በቁጥጥር ሥር መዋሉ አይዘነጋም።

አሜሪካ ለመኖር ሕጋዊ ፈቃድ ቢኖረውም ትራምፕ ማሕሙድና ሌሎችም ፍልስጤምን የሚደግፉ የመብት ተሟጋቾች "ሐማስን ይደግፋሉ" ብለው ፈርጀዋል።

የ30 ዓመቱ ማሕሙድ ጠበቃ እንዳሉት፣ ማሕሙድ የነጻ ንግግር መብቱን ተጠቅሞ ለፍልስጤም ድምጽ በመሆን የጋዛን ጦርነትና አሜሪካ የምታደርገውን ድጋፍ ተቃውሟል።

በሚያንማር በተከሰተው ርዕደ መሬት ቢያንስ 1002 ሰዎች ሞቱየሚያንማር ርዕደ መሬትየፎቶው ባለመብት29 መጋቢት 2025በሚያንማር በተከሰተው ርዕደ መሬት እስካሁን ድረስ ብቻ ቢያንስ 1002 ሰ...
30/03/2025

በሚያንማር በተከሰተው ርዕደ መሬት ቢያንስ 1002 ሰዎች ሞቱ
የሚያንማር ርዕደ መሬትየፎቶው ባለመብት
29 መጋቢት 2025
በሚያንማር በተከሰተው ርዕደ መሬት እስካሁን ድረስ ብቻ ቢያንስ 1002 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 2,376 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

30 ሰዎች ደግሞ መጥፋታቸው ተገልጿል።

ትናንት በ7.7 ማግኒትዩድ የተለካ ርዕደ መሬት የተከሰተ ሲሆን ከሚያንማር አልፎ በአጎራባች አገራትም ንዝረቱ ተሰምቷል።

የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የሰዎችን ሕይወት ለማዳን እየተተረባረቡ ቢሆንም የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው።

"በእጃችን እየቆፈርን ሰዎች ለማዳን እየሞከርን ነው" ሲል አንድ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ቡድን ለቢቢሲ ገልጿል።

በባንኮክ በግንባታ ላይ በነበረ ሕንጻ ውስጥ ይሠሩ የነበሩ 100 ሠራተኞች እስካሁል አልተገኙም። ከመካከላቸው ስድስቱ መሞታቸው ተገልጿል።

የሚያንማር ወታደራዊ መንግሥት ዓለም አቀፍ እርዳታ ጠይቋል።

ሚያንማር ራሷን አግልላ የምትኖር አገር ብትሆንም የርዕደ መሬቱ ስፋት ወታደራዊ መንግሥቱ ድጋፍ እንዲጠይቅ አስገድዶታል።

ወታደራዊ መንግሥቱ በሰጠው መረጃ መሠረት 694 ሰዎች የሞቱት ማንዳላይ በተባለው ከተማ ሲሆን በሌሎች አካባቢዎች ያለው የተጎጂዎች ቁጥር 1,002 ደርሷል።

ማንዳላይ የሚያንማር ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ስትሆን በርዕደ መሬቱ ክፉኛም ተጎድታለች።

የሚያንማር ርዕደ መሬትየፎቶው ባለመብት
ሕንድ ለሚያንማር እርዳታ ከላኩ አገራት አንዷ ናት። በሚያንማር ለሚገኙ የርዕደ መሬት ተጎጂዎች ድጋፍ መስጫ ማዕከላት መገልገያዎችን አድርሳለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ንሬንድራ ሞዲ "ድጋፍ ለመስጠት በተጠንቀቅ እየተጠባበቅን ነው" ብለዋል።

የሚያንማር ርዕደ መሬት ተጎጂዎችየፎቶው ባለመብት
የ45 ዓመት ባለቤቷን ለማግኘት እየሞከረች ያለችው ናርሞል ከፍተኛ ጭንቅ ውስጥ መሆኗን ትናገራለች።

እስካሁን ድረስ ካልተገኙ የግንባታ ባለሙያዎች አንዱ ባለቤቷ ነው።

ናርሞል የእምባ ሳግ እየተናነቃት ባለቤቷ ያለበትን ማወቅ አለመቻሉት ትገልጻለች።

የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ተጎጂዎችን በሕይወት ለማግኘት ሙከራቸውን ቀጥለዋል።

የሚያንማር ርዕደ መሬት ተጎጂዎችየፎቶው ባለመብት
በማንዳሊ የሚኖር አንድ ግለሰብ ለቢቢሲ በርሚዝ እንደተናገረው ድንገት ርዕደ መሬቱ ሲነሳ መሬቱ በአንድ ጊዜ ተናውጧል።

ወደ 10 ሰከንድ መሬቱ ከተንቀጠቀጠ በኋላ መላው ቤቱ መናዱን ገልጿል።

"ሙሉ ቤታችን እያየሁት ተናደ። ላዬ ላይ ሊወድቅ ስል ለማምለጥ ስሞክር ተደናቅፌ ወደቅኩ። መተንፈስ አልቻልኩም። በጩኸት ሰዎች እንዲረዱኝ ተጣራሁ። አባቴና አጎቴ ደረሱልኝ። ከሌሎች ስድስት ሰዎች ጋር ተባብረው ከቤቱ አወጡኝ" ይላል።

የመጀመሪያውን ዙር ርዕደ መሬት ተከትሎ ሰዎች ከቤታቸው ለመውጣት ሲሞክሩ በድጋሚ ርዕደ መሬቱ ተከስቷል።

የማንዳሊው ነዋሪ ቢተርፍም አንድ አክስቱ ሞታለች፤ ሌላዋ አክስቱ ደግሞ ተጎድታ ሆስፒታል ገብታለች።
የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቪስ እንዳለው ርዕደ መሬቱ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎችን ሊገድል ይችላል።

ይህ ግምት የተቀመጠው ከርዕደ መሬቱ የንዝረት መጠን አንጻር ነው። ከርዕደ መሬት በኋላ ሊነሱ የሚችሉ እንደ መሬት መንሸራተት ያሉ አደጋዎችን ከግምት ውስጥ ሳያስገባ ነው ግምቱን ያስቀመጠው።

የሚያንማር ርዕደ መሬትየፎቶው ባለመብት
ቻይና 37 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን ወደ ሚያንማር ልካለች። ሌላ ርዕደ መሬት ሊከሰት እንደሆነ የሚጠቁም መሣሪያ፣ ሰው አልባ አውሮፕላን እንዲሁም የሳተላይት መሣሪያዎችን እየተጠቀሙ ነው።

የሚያንማር ርዕደ መሬት ተጎጂዎችየፎቶው ባለመብት
በቻይና የሚገኘው ዩናን ግዛት ውስጥ የርዕደ መሬቱ ንዝረት ይሰማ እንደነበር ተገልጿል።

ዩክሬን በጊዜያዊነት በተባበሩት መንግሥታት ስር እንድትሆን ፑቲን ሃሳብ አቀረቡየሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንየፎቶው ባለመብት29 መጋቢት 2025ዩክሬን ብቁ የሆነ መንግሥት እስክትመርጥ ድ...
30/03/2025

ዩክሬን በጊዜያዊነት በተባበሩት መንግሥታት ስር እንድትሆን ፑቲን ሃሳብ አቀረቡ
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንየፎቶው ባለመብት
29 መጋቢት 2025
ዩክሬን ብቁ የሆነ መንግሥት እስክትመርጥ ድረስ በጊዜያዊነት በተባበሩት መንግሥታት አመራር ስር እንድትሆን የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሃሳብ አቀረቡ።

በኪዬቭ ተቀማጭ ያደረገውን የዩክሬንን አስተዳደር በህገወጥነት የሚፈርጁት የሩሲያው ፕሬዚዳንት አመራሩ እንዲቀየር በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይደመጣሉ።

ዩክሬን የፑቲንን ይህንን ሃሳብ "እብደት" ስትል የጠራችው ሲሆን፤ በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መሪነት የሚደገፈውን የሰላም ስምምነት ለማዘግየት የሚደረግ ስትራቴጂ ነው ብላለች።

ዋይት ሃውስ በበኩሉ የዩክሬን አስተዳደር በህገ መንግሥቱ እና በህዝቡ እንደሚወሰን አጽንኦት ሰጥቷል።

የፑቲን አስተያየት የተሰማው አራተኛ አመት ያስቆጠረውን የዩክሬን ጦርነት ሰላማዊ እልባት እንዲያገኝ አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ በዋነኝነት እያሸማገለች ባለችበት ወቅት ነው።

ሩሲያ እና ዩክሬን ጥቁር ባሕር ላይ የሚያደርጉትን ጦርነት የሚያስቆም የተኩስ አቁም ስምምነት መፈረማቸውን ዋይት ሃውስ አረጋግጧል።

ሀገራቱ ሳዑዲ አራቢያ ውስጥ በየግላቸው ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ባደረጉት ስምምነት ነው የተኩስ አቁም ለማድረግ የወሰኑት።

ነገር ግን ሩሲያ የጥቁር ባህር የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ የሚሆነው ምዕራባውን የጣሉት ማዕቀብ ሲነሳ መሆኑን አጽንኦት በመስጠት ቅድመ ሁኔታዎቿን አስቀምጣለች።

ይህም ሩሲያ የተኩስ አቁሙን ለማደናቀፍ እየሞከረች ነው የሚል ስጋትን አጭሯል።

ፑቲን በሰሜን ሩሲያ በምትገኘው ሙርማንስክ ከተማ የባህር ሰርጓጅ መርከብ ሰራተኞችን ባነጋገሩበት ወቅት በተባበሩት መንግሥታት ጥላ ስር የሚመራ ጊዜያዊ አስተዳደርን "ከአሜሪካ፣ ከአውሮፓ አገራት እና ከአጋሮቻችን እና ከጓደኞችን ጋር የምንወያይበት ነው" ብለዋል።
"ይህም ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ፤ በህዝብ አመኔታ ያለው ብቁ መንግሥት ወደ ስልጣን ለማምጣት እንዲሁም የሰላም ስምምነትን ለመነጋገር እና ህጋዊ ሰነዶችን ለመፈረም ነው" ሲሉም ነው የተናገሩት።

ሩሲያ፣ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ የስልጣን ዘመኑን ስለጨረሰ ህገ ወጥ መንግሥት ነው በማለት የፈረጀችው ሲሆን በዚህም የሰላም ድርድር ለመሳተፍ ህጋዊ መሰረት የለውም ትላለች።

ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ በበኩላቸው አገራቸው በጦርነት ውስጥ ስለሆነች ምርጫው በህጋዊ መንገድ በወታደራዊ ህግ እንዲዘገይ ተደርጓል ይላሉ።

በጦርነቱ ምክንያት ከአምስት ሚሊዮን በላይ የዩክሬን ዜጎች በውጭ አገራት ከመፈናቀላቸው ጋር ተያይዞ፤ እንዲሁም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በጦር ግንባሮች ተሰልፈው ባሉበት ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ ፈጽሞ የማይቻል ነገር ነው።

ፑቲን ምርጫውን አጀንዳ በማድረግ ዜሌንሰኪ በሰላም ድርድሩ ለመሳተፍ ህጋዊ መሰረት የላቸውም የሚለውን እያንጸባረቁ ይገኛሉ።

ዋይት ሃውስም ከዚህ ቀደም ይህንኑ ሃሳብ ሲያስተጋባ ተሰምቷል።

ፑቲን ምርጫ እንዲካሄድ የማስገደዱ ሁኔታ ከተሳካላቸው ዩክሬንን በጦር ግንባር በማዘናጋት ድልን እንዲቀናጁ ያደርጋቻዋል ተብሏል።

ጠ/ሚ ዐቢይ በትራምፕ ከተሾሙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ተወያዩጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ማርኮ ሩቢዮ የፎቶው ባለመብት28 መጋቢት 2025ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትራ...
30/03/2025

ጠ/ሚ ዐቢይ በትራምፕ ከተሾሙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ማርኮ ሩቢዮ የፎቶው ባለመብት
28 መጋቢት 2025
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትራምፕ አስተዳደር ከተሾሙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር መጋቢት 18/ 2017 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ በሆነ መልኩ መወያየታቸው ተገለጸ።

ማርኮ ሩቢዮ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር አክሎ በጋራ ቅድሚያ በሚሰጧቸው ጉዳዮች ላይ በስልክ መነጋገራቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ ያስረዳል።

አገራቱ በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋትን ማምጣት አንድ የውይይታቸው ርዕስ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ታሚ ብሩስን ዋቢ ያደረገው መግለጫ አትቷል።

በሪፐብሊካኑ የትራምፕ አስተዳደር የተሾሙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አገራቸው ለሰላማዊ እና የበለጸገች ኢትዮጵያ ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠውላቸዋል ተብሏል።

ትራምፕ በመጀመሪያ አስተዳደራቸው ወቅት ግብጽ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች ማለታቸው የኢትዮጵያ መንግሥትን ያሳዘነ ነበር።

በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ተቀማጭ የሆኑትን የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሬይኖርን ጠርተው ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሰጡት አስተያየት ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቀው ነበር።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥቅምት 13፣ 2013 ዓ.ም ሱዳን እና እስራኤል ግንኙነታቸውን ለማደስ የደረሱበትን ስምምነት አስመልክቶ ከሱዳን ጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ እና ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ በተነጋገሩበት ወቅትም ነው የህዳሴ ግድብን ጉዳይን ያነሱት።

"ግብፅ በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማትችል ሁኔታው አደገኛ ነው። ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች፤ አሁንም በግልፅ እናገረዋለሁ ግብፅ በድጋሚ ታፈነዳዋለች" በማለት በተደጋጋሚ የተናገሩት ትራምፕ

"ስምምነት ለአገራቱ ባቀርብም ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። አንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም ይህ ትልቅ ስህተት ነው። በዚህም ምክንያት የምንሰጣቸውን ብድር አቁመናል። ስምምነቱን ካልተቀበለች በስተቀር ኢትዮጵያ ያንን ገንዘብ አታየውም " ማለታቸው የሚታወስ ነው።

አቶ ገዱ አክለውም በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል እንዲህ ጦርነት የሚያጭር ነገር ከተቀማጭ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት መሰማቱ የሁለቱን አገራት የቆየ ግንኙነትና ጥምረት አያሳይም እንዲሁም አገራቱን በሚገዛው የአለም አቀፍ ህግም ተቀባይነት የለውም ማለታቸውንም በወቅቱ የወጣው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አመላክቷል።

ከአራት ዓመታት በፊት በሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የአፍሪካ አገራትን በማንቋሸሽ እና በጸያፍ ዘለፋዎች በመንቀፍ ይታወቃሉ ትራምፕ።

"የአሜሪካን ታላቅነት በድጋሚ ለማምጣት" በተደጋጋሚ የሚምሉት ትራምፕ ፀረ-ስደተኝነት፣ፀረ- ሙስሊም የሆኑ ንግግራቸው እና አቋማቸውን ደጋግመው አንጸባርቀዋል።

ከሥልጣን ወርደው ለሁለተኛ ጊዜ በመመረጥ ታሪክ የሠሩት ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዐቢይ ለሪፐብሊካኑ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የአሜሪካ የምርጫ ውጤት በይፋ ሳይገለጽ ነበር።
"በምርጫ ድልዎት እና ወደ ሥልጣን በመለለስዎ እንኳን ደስ አለዎት ማለት እፈልጋለሁ" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኤክስ ገጻቸው ላይ መልዕክታቸውን አስፍረው ነበር።

አክለውም "በእርስዎ የሥልጣን ዘመን የሁለቱን አገራት ግንኙነት በበለጠ ለማጠናከር በጋራ የምንሠራበትን ጊዜ እጠብቃለሁ" ሲሉም በዚሁ መልዕክታቸው ላይ አትተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሥልጣን የቆዩባቸው የባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ አራቱ በዲሞክራቶች የሥልጣን ዘመን ነው።

ለሁለት ዓመታት በዘለቀው ደም አፋሳሹ የትግራይ ጦርነት ምክንያት በተፈጸሙ ጥሰቶች በርካታ ማዕቀቦች በአሜሪካ መጣላቸው ከዴሞክራቶች ጋር ያለው ግንኙነት እንዲሻክር አድርጎታል።

ከእነዚህም ውስጥ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በትግራይ ጦርነት ላይ ጥሰቶችን ፈጽመዋል የተባሉ አካላት ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ ለመጣል የሚያስችል ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ መፈረማቸው ይታወሳል።

ማዕቀቡ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የኤርትራ መንግሥት፣ የአማራ ክልል አስተዳደር እና የህወሓት አመራሮችን ተጠያቂ የሚያደርግ እንደሆነም ተገልጿል።

ዕቀባው ግጭቱ እንዲራዘም አስተዋጽኦ ያደረጉ፣ ሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነትን ያደናቀፉ፣ ተኩስ አቁሙን የተከላከሉ በቀጥታ ተጠያቂ የሆኑ ወይም ተባባሪዎቻቸው ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ባይደን በጊዜው አስታውቀው ነበር።

የምጣኔ ሀብት እና የደኅንነት እገዛ እንዲቋረጥ፣ ወደ ኢትዮጵያ በሚገቡ የመከላከያ ወታደራዊ ንግዶች ላይ ገደብን አሜሪካ የጣለች ሲሆን፣ በተጨማሪም በባለሥልጣናት ላይ የጉዞ እቀባ ተጥሎ ነበር።

ባለፈው ዓመት ጳጉሜ ወርም ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ መጣል የሚያስችለውን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲራዘም መወሰናቸው አስታውቀዋል።

ሌላኛው የአሜሪካ መንግሥት ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገራት የዘረጋው ከቀረጥ ነጻ ዕድል (አጎዋ) ተጠቃሚ የነበረችው ኢትዮጵያ እየተካሄደ በነበረው ጦርነት ሳቢያ ከተጠቃሚነት ውጪ እንድትሆን መደረጓ ይታወሳል።

በጦርነቱ ወቅት የሁለቱ አገራት ግንኙነት ሻክሮ የነበረ ሲሆን፣ አሜሪካም በጦርነቱ የተፈጸሙ የጦር ወንጀሎችን በመንቀስ ስታወግዝ ቆይታለች።

በዚህም ምክንያት የዲሞክራቶች ከዋይት ሐውስ መውጣት እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገራት አዲስ መስመር ወይም አዲስ ዕድል የሚያመጣ ሊሆን ይችላል ብለው ሊያስቡ እንደሚችሉ ተንታኞች ይናገራሉ።

የትግራይ ጦርነት ቢቋጭም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ውስጥ ያሉ ግጭቶች የቀጠሉ ሲሆን፣ የትራምፕ ፖሊሲ ይህንን አስመልክቶ ምን ሊሆን ይችላል? የሚለው የሚታይ ይሆናል።

ሶማሊያ፣አሜሪካ በብቸኝነት የምትቆጣጠራቸው ወደቦችን እና የጦር ሰፈሮችን እሰጣለሁ አለችየሶማሊያው ፕሬዚዳን ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ የፎቶው ባለመብት29 መጋቢት 2025የአፍሪካ ቀንድ አገሯ ሶማሊያ...
30/03/2025

ሶማሊያ፣አሜሪካ በብቸኝነት የምትቆጣጠራቸው ወደቦችን እና የጦር ሰፈሮችን እሰጣለሁ አለች
የሶማሊያው ፕሬዚዳን ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ የፎቶው ባለመብት
29 መጋቢት 2025
የአፍሪካ ቀንድ አገሯ ሶማሊያ አሜሪካ በብቸኝነት የምትቆጣጠራቸው ስልታዊ ወደቦችን እና የጦር ሰፈሮችን ለመስጠት ሃሳብ ማቅረቧን ሮይተርስ ዘገበ።
የሶማሊያው ፕሬዚዳን ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ለአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ በጻፉት እና ሮይተርስ መመልከቱን በገለጸበት ደብዳቤ ላይ ነው አሜሪካ በብቸኝት ልትቆጣጠራቸው የሚችሉ የጦር ሰፈሮች እና ወደቦች አማራጮች የቀረቡት።
ጉዳዩን በሚያውቁ የቀጣናው ዲፕሎማት ትክክለኛነቱ መረጋገጡን የዜና ወኪሉ የገለጸው ደብዳቤ የተጻፈው መጋቢት 7/ 2017 ዓ. ም. ነው።
እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ ፕሬዚዳንቱ አሜሪካ በብቸኝነት እንድትቆጣጠራቸው ያቀረቡላቸው ባሊዶግሉ እና በርበራን በጦር ሰፈርነት እንዲሁም የበርበራ እና ቦሳሶ ወደቦችን ነው።
አሜሪካ በሶማሊያ እና በቀጣናው የሚገኙ ጽንፈኛ ታጣቂዎችን ስጋት ለመመከት በአፍሪካ ቀንድ ጠንካራ ወታደራዊ ይዞታን ያስገኝላታል ተብሏል።
"እነዚህ ስልታዊ ይዞታዎች አሜሪካ በቀጣናው የምታደርገውን ተሳትፎ የማጠናከር እድል ይሰጣሉ። የማይቋረጥ ወታደራዊ እና ሎጂስቲክ መዳረሻዎችን [ለአሜሪካ] በማረጋገጥ ሌሎች የውጭ ተወዳዳሪዎች በዚህ ወሳኝ ኮሪደር ውስጥ እንዳይገኙ ይከላከላሉ" ሲል ደብዳቤውን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ አስነብቧል።
ባሊዶግል ከዋና ከተማይቱ ሞቃዲሾ በስተሰሜን ምዕራብ በ90 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ የቦሳሶ ወደብ ከፊል ራስ ገዝ በሆነችው ፑንትላንድ ትገኛለች።

ሶማሊያ ለአሜሪካ በብቸኝነት እንደ ጦር ሰፈር እንድትጠቀምበት እና በወደብነት እንድትቆጣጠር ካቀረበችው ውስጥ የበርበራ ወደብ አንዱ ነው።

በርበራ ራሷን በነጻ አገርነት ባወጀችው ሶማሊላንድ የሚገኝ ሲሆን፤ የሶማሊያ እርምጃ ሁኔታውን ወደ ግጭት ሊያመራ ሊያደርገው እንደሚችል ይጠበቃል።

ይህንን የበርበራ ወደብን አስመልክቶ ሮይተርስ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዲራህም ዳሂር አደን "የምን ትብብር ነው? አሜሪካ ይህንን ሶማሊያ የተባለ የተበላሸ አገዛዝን ተስፋ ቆርጣበታለች። አሜሪካ ለዓለም ሰላማዊ፣ የተረጋጋና ዲሞክራሲ የሰፈነባት አገር መሆኗን ካሳየችው ሶማሊላንድ ጋር ለመደራደር ዝግጁ ናት" የሚል ምላሽ ሰጥተተዋል።

"አሜሪካ ደደብ አይደለችም። በርበራ ወደብን በተመለከተ ከማን ጋር መነጋገር እንዳለባቸው ያውቃሉ" ሲሉ አክለዋል።

በባይደን አስተዳደር ወቅት የዩኤስኤ አፍሪካ ኮማንድ (አፍሪካ) አዛዥን ጨምሮ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት የበርበራ ወደብን ጎብኝተዋል።

በኋላ ላይ ለአሜሪካ የጠፈር መንኮራኩሮች ድንገተኛ ማረፊያ ተብሎ መለየቱም ተነግሯል።

ከሦስት ዓመታት በፊት የአሜሪካ የመከላከያ 'አውቶራይዜሽን አክት' ተብሎ የሚጠራው የፀጥታ ትብብርን በማጎልበት ለጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት መንገድ ይከፍታል በሚል ሶማሊላንድ እንድትካተት ተሻሸሏል።

ሶማሊላንድን እንደ አንድ የግዛቷ አካል አድርጋ የምታየው ሶማሊያ ከሶማሊላንድ ጋር የሚደረግ ስምምነትንም ሆነ እውቅናን እንደማትቀበለው በተደጋጋሚ ትናገራለች።

ኢትዮጵያ ራሷን እንደ ነጻ አገር ካወጀችው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ካላገኘችው ሶማሊላንድ ጋር 20 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የባሕር ጠረፍ ለማግኘት የፈረመችው የመግባቢያ ሰነድ ሶማሊያን በእጅጉ አስቆጥቶ በቀጣናው ከፍተኛ ውጥረትን ያስከተለ መሆኑ ይታወሳል።

በምላሹም ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ ዕውቅና ለመስጠት እንዲሁም ከልማት ተቋማቷ ድርሻ ይኖራታል የሚል ነው።

ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ያቋረጠ ቁርሾ ውስጥ ከገቡ በኋላ በቱርክ አደራዳሪነት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶዋን አደራዳሪነት ታኅሣሥ 2/2017 ዓ.ም. የተደረሰው የአንካራ ስምምነት ለአንድ ዓመት ያህል በቃላት ጦርነት ሲወዛገቡ የነበሩት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ልዩነታቸውን በድርድር ጠረጴዛ ለመፍታት እንዲቀመጡ ያደረገ ነው።

ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር በተደረሰው የባሕር በር መግባቢያ ስምምነት ለመጀመሪያ ጊዜ ዕውቅና አገኛለሁ የሚል ተስፋ ነበራት። ሆኖም በዚህ የመግባባቢያ ስምምነት ቁርሾ ውስጥ የገቡት ኢትዮጵያና ሶማሊያ ልዩነታቸውን ለመፍታት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ የመግባቢያ ስምምነቱ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።

ከሶማሊያ ባለሥልጣናት በኩል ይህ የመግባቢያ ስምምነት እንደተሻረ ቢናገሩም ኢትዮጵያ በይፋ ያለችው ነገር የለም።

ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ሶማሊላንድ በአሜሪካ ዕውቅና ልታገኝ ነው የሚለው መነጋገሪያ ሆኗል።

ኃያላን እና ተደማጭነት ያላቸው ሪፐብሊካኖች የሶማሊላንድን ዕውቅና የማግኘት ፍላጎት በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ አጀንዳ አድርገውታል።

ከጥቂት ወራት በፊት የአሜሪካ የምክር ቤት አባል ስኮት ፔሪ አሜሪካ ለሶማሊላንድ መደበኛ እውቅና እንድትሰጥ ረቂቅ ሕግ አቅርበዋል።

ይህ ረቂቅ በአውሮፓውያኑ ሚያዝያ 2023 ሁለተኛውን የትራምፕ የፕሬዚዳንትነት የሥልጣን ዘመንን በማስመልከት የወጣውን ፍኖተ ካርታ የተከተለ ነው።

'ፕሮጀክት 2025' የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ፍኖተ ካርታ በቀኝ አክራሪው ሄሪቴጅ ፋውንዴሽን በተሰኘው እና ከ100 በላይ ወግ አጥባቂ ድርጅቶች የተነደፈ ነው።

ሰነዱ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ሁለት አገራትን ብቻ ይጠቅሳል፣ ሶማሊላንድ እና ጂቡቲን። "አሜሪካ በጂቡቲ ያላትን ተጽእኖ ማሽቆልቆል ለመቋቋም ሶማሊላንድን እንደ አገርነት ዕውቅና መስጠት" የሚል ነው።

በትራምፕ የቀድሞ አስተዳደር ወቅት በአፍሪካ ጉዳዮች የቀድሞ ረዳት ፀሐፊ እና በኢትዮጵያ በአምባሳደርነት ያገለገሉት ቲቦር ናዥ እና የአፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ ፒተር ፋም የሶማሊላንድን ነጻነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚያቀነቅኑ ናቸው።

በአሁኑ ወቅት ሶማሊያ ከትራምፕ አስተዳደር ጋር ያለው ግንኙነት ስላሳሰባት አንድ ወትዋች (ሎቢ) ቡድን ቀጥራለች። ሶማሊያ በዋሺንግተን መቀመጫውን ላደረገው ቢጂአር ለተሰኘው የሎቢ ድርጅት 600 ሺህ ዶላር ለመክፈል ተስማምታለች።

23 ኢትዮጵያዊያንን በህገ ወጥ መንገድ ለማሳለፍ የሞከሩ 8 የሀራሬ አየር መንገድ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ የእነዚህን 23 ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ባለፈው ሳምንት መዘገባችን የሚታወስ ነው...
28/03/2025

23 ኢትዮጵያዊያንን በህገ ወጥ መንገድ ለማሳለፍ የሞከሩ 8 የሀራሬ አየር መንገድ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ የእነዚህን 23 ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ባለፈው ሳምንት መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ወደዚያው የተጓዙት በተለያየ ቀን እንደነበር የቀረበባቸው ክስ ያስረዳል፡፡ በመጀመሪያ አምስት ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ኢቲ 873 ተሳፍረው ሮበርት ገብርኤል ሙጋቤ አለም አቀፍ አየር መንገድ የደረሱት ማርች 15 ቀን ነበር፡፡
እዚያ የገቡትም በቀጣይነት ወደስዋትኒ ለመጓዝ በማቀድ እንደነበር ተገልጿል፡፡ ይሁንና በሀራሬ የሚገኘው አየር ማረፊያው ሰራተኞች እነዚህን ኢትዮጵያዊያን በቪአይቪ ክፍል ውስጥ እንዲቀመጡ ወይንም እንዲደበቁ ማድረጋቸውን የጠቀሰው ክሱ በነጋታው 19 ተጨማሪ ኢትዮጵያዊያን ደርሰው መቀላቀላቸውን አስረድቷል፡፡ ሁሉም ወደስዋትኒ ቀጣይ ጉዞ ለማድረግ የሚያስችል ቪዛ የሌላቸው በመሆኑ በተደረገው ፍተሻ መረጋገጡን የጠቀሰው ክሱ ኢትዮጵያዊያኑ ወደእስር ቤት እንዲገቡ መደረጋቸውን ጠቅሷል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በዚህ ድርጊት ተሳትፎ ያደረጉት 8 የአየር መንገዱ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለው ትላንት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ኒው ዚምባቡዌ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የታሰሩት 23ቱ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ፍርድ ቤት ቀርበው የሶስት ወር እስራትና አንድ መቶ ዶላር ቅጣት እንደተጣለባቸው ዘገባው አስረድቷል፡፡

Address

Harar
3200

Telephone

+251968924212

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Libo Tv News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Libo Tv News:

Share