Abdella Aliye

Abdella Aliye ለፈጣን፤ወቅታዊ እና እዉነተኛ የኢትዮጵያ መረጃ/odeeffannoo waaqtawaa fi dhugaa Itiyoophiyaatiif.

ሀገራዊ ምክክራችን ለሀገረ መንግስት ግንባታችን የራሱን አስተዋህጾ በማበርከት ተጠናቋል!!!የሀገራችን ዜጎችን በአንድ ቦታ በማሰባሰበድ እዲተዋወቁና እዲመካከሩ እድል ሰጥቶል፤ከአራቱም የሀገራች...
26/08/2026

ሀገራዊ ምክክራችን ለሀገረ መንግስት ግንባታችን የራሱን አስተዋህጾ በማበርከት ተጠናቋል!!!

የሀገራችን ዜጎችን በአንድ ቦታ በማሰባሰበድ እዲተዋወቁና እዲመካከሩ እድል ሰጥቶል፤ከአራቱም የሀገራችን መዕዘናት እንዲሁም በዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ጭምሮ 4ሺ የሚሆኑ ምናልባትም በአይነ-ቁራኛ የሚተያዩ ሰዎችን በማሰባሰብ በሀገራቸዉ ጉዳይ እዲወያዩና ምክረ-ሃሳብ እንዲሰጡ ማድረጉ በራሱ አዲስ የባሀል-ለዉጥ/ግንባታ ሲሆን ሁሉን ነገር በሀገራችን በግልም ይሁን በቡድን አብዛኛዉን ግዜ እንደለመድነዉ በጉልበት፤በነፍጥና ሌላዉን በማበርከክ የመፍታት አባዜያችን ተላቀን በዉይይትና በምክክር የመፍታትን ባህል በአዲስ መልክ ማለማመድ ማስጀመሩ ትልቅ እምርታ ነዉ፡፡

ለዉይይትና ለምክክር ከቀረቡት 8ቱ አጀንዳዎችና በሌሎች የተሰጡት ምክረ-ሃሳቦች ለሀገራችን ፖሊሲ አዉጭዎች፤ፖሊቲከኞች፤ህግ አዉጭዎች፤የሚዲያ ባለሙያዎች፤ለምሁራኖችና ተመራማሪዎች ከፍተኛ ግብአት በመሆን የሚያገለግል ሲሆን ይህም ፖሊሲና ህጎችን ለማዉጣትና ተጨማሪ ጥናትና ምርምር ለሚፈልጉ ጉዳዮችን ለማከናወን ጥሩ የመነሻ ሃብት ሁኖ የሚያገለግል ጉዳይ ነዉ ብሎ መዉሰድ ይቻላል፡፡

ምንም እንኳን በሁሉም አጀንዳዎች ላይ መስማማት ላይ ባይደረሰም መድረኩ ላይ የተገኙ ሰዎች የተለያዩ የኢትዮጵያዊያን ያለቸዉን አመለካከት፤ህመምና ፈላጎት ብዙ መሆኑን እዲገነዘቡና የኛ ሀገር ጉዳይ ከርቀት ወሬና በማህበራዊ ሚዲያዉ አንደሚናፈሱ ሳይሆን ከፍተኛ የሆነ ማስተዋልን፤እዉቀትን፤ጥበብና በስለት የሚፈልግ መሆኑን ሁሉም ተሳታፊዎች የተማሩበት መድረክ ነበረ ማለት ይቻላል፡፡

ስለሆነም ሁላችንም ኢትዮጵያዊያን መደረኩን እንደ የሁሉም ነገር መነሻ በማድረግ የጋራ ሀገራችንን ለመገምባት መደማመጥን፤ሆደ ሰፊነትን፤መከባበርንና መተባበርን ከመቼዉም በላይ ልናስብበት የሚገባን ጉዳይ ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት መከላከያን በማዘመን የዜጎችን ደህንነትና የሀገርን ህልውና ለማስከበር እየወሰዳቸው የሚገኘ እርምጃዎች የሀገራችንን የአየር ሎአላዊነት በአስተማማኝነት ሁኔታ ለመጠበቅ መከላ...
26/08/2026

የኢትዮጵያ መንግስት መከላከያን በማዘመን የዜጎችን ደህንነትና የሀገርን ህልውና ለማስከበር እየወሰዳቸው የሚገኘ እርምጃዎች
የሀገራችንን የአየር ሎአላዊነት በአስተማማኝነት ሁኔታ ለመጠበቅ መከላከያ ሰራዊታችን የሩሲያ Sukhoi Su-35 ተዋጊዎችን፣በሰው አልባ ድሮኖች (Drones)ና ሌሎችንም በጥሩ ሁኔታ ታጥቃለች፡፡

ወታደራዊ መሳሪያዎችን በተለይም የተለያዩ አይነት ድሮኖች፤ጥይቶችና ሌሎች በማምረት በ ሌሎች ሀገራት ላይ ጥገኛ ሳትሆን የሀገርን ደህንነት ለመጠበቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ተገኛለች፡፡

በእግረኛ ወታደርም በኩል ሀገራችን የተለያዩ አይነት የዕዝ፤የሰዉ ሃይል አደረጃጀትና ስምሪቶች እያደረገች የምትገኝ ሲሆን ከዝህ በፊት ያለነበሩት እንደነ ሪፐብሊካን ጋርድና ልዩ ኦፕሬሽንስ እዞችን በማደረጃት እየተጠቀመችበት ነዉ፡፡

በተጨማሪም ሀገራችን ከተለያዩ የአለም ሀገራትና ተቋማት ጋር ወታደራዊ ስምምነቶችን በማድረግ ተቋሙን በሰዉ ሃይልና በመሳሪያ እያዘመች ትገኛለች ለምሳሌ ከአሜሪካ ፔንታጎን(በ2018ዓ.ም)ና ከህንድ(በ2017ዓ.ም) ሀገር ጋር የተደረገ ወታደራዊ ስምምነቶችና ወይይቶች የዝህ ጉደይ ማሳያ ናቸዉ፡፡

24/08/2026
ኢትዮጵያ ድንበር ተሸጋሪ ወንዞቿን ለመጠቀም የአለምን ህግ ታከበራለች እንጂ የሀገራት ይሉኝታ አያስፈልጋትም!!ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን በነጻነትና በፍትሃዊነት እድትጠቀም የሚረዷት አንቀጾች፤...
24/08/2026

ኢትዮጵያ ድንበር ተሸጋሪ ወንዞቿን ለመጠቀም የአለምን ህግ ታከበራለች እንጂ የሀገራት ይሉኝታ አያስፈልጋትም!!

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን በነጻነትና በፍትሃዊነት እድትጠቀም የሚረዷት አንቀጾች፤-
በተመድ የድንበር ተሻጋሪ የውሃ አካላት አጠቃቀም ስምምነት/ (UNCNNIWC) መሰረት እነዝህን ዉሃ ሀብቶች አንቀጽ 5፣6ና 7 በፍትሃዊነትና ምክንያታዊነት ሊጠቀሙ ይገባል በማት ይደነግጋል፡፡

በተመድ ቻርተር ምዕራፍ 1 አንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 1 (Article 2(1) መሰረት ሀገራት የተፈጥሮ ሀብታቸዉን በማልማት እራሳቸዉን ሌላዉን ሳይጎዱ ማሳደግ ይችላሉ በማለት ይገልጻል፡፡
የአፍሪካ የሰብአዊና የህዝቦች መብቶች ቻርተር አንቀጽ 21 ደግሞ ሁሉም ሕዝቦች የራሳቸውን ሀብትና የተፈጥሮ ሀብት በነፃ የማልማትና የመጠቀም መብት አላቸው በማለት ደንግጓል፤፤

በየናይል ወንዝ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት አንቀጽ 4 በበኩል የተፋሰስ ሀገራት የናይልን ውሃ በፍትሃዊነትና ምክንያታዊነት መጠቀም እንዳለባቸው ይደነግጋል።

በአጠቃላይ ሀገራችን የአባይን/የሞርሞርን ወንዝ ለመጠቀም በሎአላዊ በግዛታ ዉስጥ ከላይ በተጠቀሱት የተመድና የአፍሪካ ህብረት ድንጋጌዎች የሚደገፍ ሲሆን የሌሎች ሃገራትን የመልማት መብት በማጎዳ መልኩ የጨረስነዉን ህዳሴ ይቅርና ሌለዉንም የምንደግም መሆኑን መታወቅ አለበት፡፡

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበርና የቀጠናዉን ዘላቂ ሰላም ለማመጠበቅ አያሌ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች!!በአንድ በኩል ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጋር ለምሳሌ ከኬንያ ጋር በተለያዩ የ...
24/08/2026

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበርና የቀጠናዉን ዘላቂ ሰላም ለማመጠበቅ አያሌ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች!!

በአንድ በኩል ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጋር ለምሳሌ ከኬንያ ጋር በተለያዩ የጋራ የደህንነት የቀጠናዉ ስጋቶችና በጋራ ሊሰሩባቸዉ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ የሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ተቋማት ከዓመት በፊት ከስምምነት የደረሱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አብረዉም በተጨባጭ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

በሌላ በኩል ሀገራችን የራሷን እና የአፍሪካን ቀንድ ሰላምን ለመጠበቅና የልማት ቀጠና የማድረግ እየሰራች መሆኗን የምድራችን ቁንጮዋ ሀገር ሀገረ አሜሪካ በሂደትም በሆንም እየተረዳች በመምጣቷ ከሀገራችን ጋር ለመስራት ፍላጎት አሳይታለች፤
ለዝህም አመልካች የሚሆነዉ ደግሞ ከአሜሪካ ጋር በነሃሴ 13-14 ዓ.ም ሀገራችን መከላከያን የወከሉ ሃላፊዎች በዋሽንግተን ከተማ በተለይም በመከላከያ ሚኒስቴራቸዉ በመባል የሚታወቀዉ በፔንታጎን በመገኘት በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመስራት የተደረገዉ ስምምነት ነዉ፡፡

ይህ ስምምነት ለዉስጥ ባንዳዎችና ለዉጭ ባዳዎች በጣም አስደንጋጭ የሚባል ዜና ነዉ ምክንያቱም ህወሃትና ሌሎች የሷ ተላላኪዎች የአሜሪካን የማድረግ አቅም ጠንቅቀዉ ስለሚያቁትና ከዝህ በፊትም በዝህ ቡድን ላይ ማዕቀብ በመጣል ወደ አሜሪካ መግባት እንደማችሉ የገደበቻቸዉ ሲሆን፤ለኤርትራ መንግስትም የማስጠንቀቂያ ደወል መሆኑን ማወቅ አለበት፤
ለኢትዮጵያ ግን የብስራት ዜና ሲሆን የወታደራዊ አመራሮቿ በፔንታጎን ከነ ዩኒፎርማቸዉ በመገኘት ዉይይት ያደረጉ መሆኑ ደግሞ የሀገራችንን የዲፕሎማሲያዊ ድል ማሳያ ነዉ፡፡

በድምሩ በአሜሪካ የተገኘዉ ቡድን ሀገረ አሜሪካ ስለ ህዳሴ ግድባችን ያላትን የተሳሳተ ግንዛቤም እድታጠራና ከእዉነት ጎን እድትሆን ስለሚያደረጋት ግብጽም በተላላኪዎቿ ኤርትራና የዉስጥ ባንደዎች(ህወሃትና ሌሎችም) የምኪታደረገዉን የማሸበር ሴራ እድታጤነዉ የሚያመላክታት ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ በአንድ አመት ማለትም በ2018ዓ.ም ብቻ የሳካችዉ ሶስቱ ትላልቅ/ሜጋ ድሎች!!1ኛሀገር አቀፍ ምርጫን በተመለከተ፤በአንጸራዊነት ሰላማዊ፤ነጻና ፍትሃዊ ምርጫን በማድረግ በስኬት አጠናቃ...
24/08/2026

ኢትዮጵያ በአንድ አመት ማለትም በ2018ዓ.ም ብቻ የሳካችዉ ሶስቱ ትላልቅ/ሜጋ ድሎች!!

1ኛሀገር አቀፍ ምርጫን በተመለከተ፤በአንጸራዊነት ሰላማዊ፤ነጻና ፍትሃዊ ምርጫን በማድረግ በስኬት አጠናቃለች
2ኛ በአንድ ጀምበር 805ሚሊዮን ችግኞችን በሃምሌ 27/2018ዓ.ም በመትከል ለመጭዉ ትዉልድ አሻራዋን አስወምጣለች
3ኛ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤዋን በስኬት አጠናቃለች፤ከ2014 ጀምሮ ሲሰራበትና ሲለፋበት የቆየን አንድ ታላቅ ሀገራዊ ጉዳያችን አብዛኛዉን ጉዳይ በመግባባትና በጣም ጥቂቱን ደግሞ በሂደት ለመፍታት በታላቅ ተግባቦት ለ46 ቀናት ሲካሄድ የነበረዉ በስኬት ተጠናቋል፡፡

ድሉ የጋራችን ነዉና እንኳን ደስ አለን የሀገራችን ህዝቦች፤ሀገራችን ተስፋዋና መለወጦ ይቀጥላል ግን አይምሮና ሆደ ሰፊነት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

23/08/2026

#ኢትዮጵያዊን የሚጠይቀው ነገር ቢኖር...

Address

Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abdella Aliye posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share