Mohammed Redwan Mume

Mohammed Redwan Mume Agriculture is a key for development, thus late joint together & promote the success, achivement & efforts made in agricultural sectors as a whole.

03/07/2025
02/07/2025

በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የአገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ-ኢንስቲትዩቱ

አዲስ አበባ፤ሰኔ 25/2017(ኢዜአ):-በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የአገሪቱ አካባቢዎች ብዙ ቦታዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በሚቀጥሉት አስር ቀናት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ይበልጥ እየተስፋፉና እየተጠናከሩ ይቀጥላሉ።

በደቡብ ምዕራብ፣ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ሰሜን፣ መካከለኛው እና ሰሜን ምስራቅ የአገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ሥርጭት እንደሚኖር አሃዛዊ የትንበያ መርጃዎች እንደሚያሳዩ ተጠቁሟል።

በተለይ በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብና መካከለኛ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ብለዋል።

አልፎ አልፎ በውሃ አካላትና አካባቢ በምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና መካከለኛው የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖራቸው እንደሚችል ገልጸዋል።

በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ነጎድጓዳማና በረዶ አዘል ዝናብ እና የዝናቡ ጥንካሬም ለረጅም ሰዓታት ያለማቋረጥ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል በመግለጫው ተመላክቷል።

በክረምቱ ወቅት የሚዘንበው ዝናብ በአመዘኙ አዎንታዊ ሚና የሚኖረው መሆኑ ተገልጿል።

ይህም አስቀድሞ ለተዘሩ ሰብሎች፣ ለመኽር ሰብሎች፣ ለቋሚ ተክሎችና የጓሮ አትክልት የውሃ ፍላጎት ለማሟላት በኩል መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።

አብዛኛው የአገሪቱ ተፋሰሶች ላይ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ የገጸ ምድር የውሃ ፍሰት ይኖራቸዋል፤ነገር ግን አልፎ አልፎ የሚኖረው ከባድ ዝናብ ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል በመጪው አስር ቀናት የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር፣ በምስራቅ አማራ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ምዕራብ እና ደቡብ ምስራቅ የአገሪቱ ሥፍራዎች ላይ ከ26 እስከ 41 ዲግሪ ሴልሺዬስ በላይ ሙቀት እንደሚኖራቸው ትንበያው ያሳያል።

#ኢትዮጵያ
#ኢዜአ

በሀረሪ ክልል በድሬ ጠያራ በወረዳ 150 ሄክታር መሬት በቃሪያ ክስተር እየለማ መሆኑ ተገለፀ። *****************************በወረዳው የሚገኙ አርሶ አደሮች አነስተኛ ማሳቸውን...
02/07/2025

በሀረሪ ክልል በድሬ ጠያራ በወረዳ 150 ሄክታር መሬት በቃሪያ ክስተር እየለማ መሆኑ ተገለፀ።
*****************************

በወረዳው የሚገኙ አርሶ አደሮች አነስተኛ ማሳቸውን ተጠቅመው ምርትና ምርታማነታቸውን በማሳደግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን የድሬ ጠያራ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት አስታወቀ።

የድሬ ጠያራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ ናዊ ዳውድ ከሀረሪ ብዙሃን መገናኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ አነስተኛ ማሳ ያላቸው አርሶ አደሮች ባላቸው መሬት ላይ የተለያዩ አይነት ዘሮችን በማምረት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በወረዳው በአሁኑ ወቅት 150 ሄክታር መሬት በቃሪያ ክላስተር እየለማ መሆኑን ገልጸው በዚህም ከ650 አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡

ለቃሪያ ምርቱም የገበያ ትስስር በመፍጠር በአካባቢ ለሚገኙ ከተሞች የማቅረብ ስራ እየተሰራ ነው ሲሉም አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡

የቃሪያ ክላስተር ተጠቃሚ የሆኑ አርሶ አደሮች በበኩላቸው ከዚህ ቀደም በማሳቸው አንድ አይነት ምርት ብቻ ሲያመርቱ እንደነበሩ ገልጸው አሁን ግን ባገኙት ተሞክሮ የተለያዩ ምርቶችን እያመረትን ተጠቃሚ ሆነናል ብለዋል።

የወረዳ ግብርና ጽ/ቤትም የተለያዩ ምርጥ ዘሮችና ግብአቶችን እያቀረበላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አርሶ አደሮች በአነስተኛ ማሳቸው የተለያዩ ምርቶችን በማምረት ተጠቃሚ እንዲሆኑም አቶ ናዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ሙህየዲን ሙክታር
25/11/17

ለተጨማሪ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከታተሉን።

ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/

ዩቲዩብ : https://www.youtube.com/

ቴሌግራም: https://t.me/hararimassmediaagency

02/07/2025
01/07/2025
የተሻሻለው የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ የአርሶ አደሮችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ የሚያረጋግጥ ነው- የሀረሪ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመር (አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24 ቀን ...
01/07/2025

የተሻሻለው የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ የአርሶ አደሮችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ የሚያረጋግጥ ነው- የሀረሪ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመር

(አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)

የተሻሻለው የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ የገጠር ልማት ተግዳሮቶችን በመቅረፍ እንደ ሀገር የግብርናውን ዘርፍ ከሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር የበለጠ ለማስተሳሰር የሚያስችል መሆኑን የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሮዛ ኡመር ገለጹ።

ፖሊሲው የተፈጥሮ ሀብትን በመጠበቅና በዘላቂነት ለመጠቀም፣ የግብርና ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን በማረጋገጥ በአጠቃላይ የዘርፉን እድገት ለማረጋገጥ ጉልህ ድርሻ እንዳለው አብራርተዋል።

የፖሊሲው አተገባበር እንደ የአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ የሚቃኝ በመሆኑ በክልሉም በሚመች መልኩ መመሪያን በማዘጋጀትና ደንብና አዋጅን አጸድቆ ተግባራዊ ለማድረግ በሂደት ላይ መሆናቸውን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ ጠቁመዋል።

እንደ ወ/ሮ ሮዛ ገለጻ ፖሊሲው ሙሉ በሙሉ ሲተገበር የክልሉን አርሶ አደሮች ምርቶቻቸውን ድንበር ተሻግረው ጭምር በቀጥታ የመሸጥ እንዲሁም የተለያዩ የግብርና ግብአቶችን ከቀረጥ ነጻ የማስገባት አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር ነው ብለዋል።

ፓሊሲው የአርሶ አደሩን ኑሮ በማሻሻል ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ከማረጋገጡም ባሻገር ምርቶቹን በቀጥታ ለኢንዱስትሪ ግብአት እንዲያቀርቡ ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም አርሶ አደሩ ኢንዱስትሪውን በመቀላቀልም ጭምር ከውጭ የሚገቡ የተቀነባበሩ የታሸጉ ምርቶችን በሀገር ውስጥ እንዲተኩ እንዲሁም ትንንሽ ኢንዱስትሪዎችን በመፍጠር የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችልበትን አቅም እንደሚፈጥር አስገንዝበዋል።

ፖሊሲውን ለአርሶ አደሩና ለግብርናው ዘርፍ ያለውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳና ተጠቃሚነት የማስተዋወቅ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመር መናገራቸውን የሐረሪ ክልል መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቦታል።

#ከማምረትበላይ

#አረንጓዴአሻራ


----------------
ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፦
ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
ዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs

Address

Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mohammed Redwan Mume posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share