
10/09/2025
ኢትዮጵያ 6.6 ጊጋዋት (6,600 ሜጋዋት) የኤሌክትሪክ ሃይል የሚያመነጭ የኑክሌር ሃይል ማመንጫ¹ ለመገንባት በመጨረሻው የዝግጅት ምእራፍ ላይ ትገኛለች።
ፕሮጀክቱ እያንዳንዳቸው 1,100 ሜጋዋት የሚያመነጩ ስድስት የኑክሌር ሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ሲኖሩት በሰባት ዓመት ለማጠናቀቅ ታቅዷል። የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ወጪ $33.7 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ሲሆን 35,000 ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል።
የፕሮጀክቱ የግንባታ ቦታ፣ የኑክሌር ሃይል ማመንጫ ጣቢያውን የሚገነባው ሃገርና ካምፓኒ፣ የፋይናንስ ምንጭ፣ የኑክሌር ነዳጅ (nuclear fuel) አቅርቦት ሥምምነት እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች በሚመለከተው አካል በቅርቡ ይፋ ይደረጋሉ።
☢️
¹-የኑክሌር ጣቢያው ምስል ከጎግል የተወሰደ ነው።