Daato News

Daato News የህብረተሰብን የልማትና የመልካም አስተዳደር እጦት ጥያቄን ያነገበ ፣ሌላ ምንም አይነት ግላዊ ወይም ቡድናዊ ፍላጎት የለለው ገጽ ነው!

መንግስታ[ችን] እየጣለብን ያለዉ ማዕቀብም ከሆነ በግልፅ  ቋንቋ  ያስረዳን ''ጂ ብልፅግናን እንደ  የግላችንና ብቸኛ  አሻጋሪያችን  አድርገን ለመኖር ስንል እንቀበላለን
08/05/2025

መንግስታ[ችን] እየጣለብን ያለዉ ማዕቀብም ከሆነ በግልፅ ቋንቋ ያስረዳን ''ጂ ብልፅግናን እንደ የግላችንና ብቸኛ አሻጋሪያችን አድርገን ለመኖር ስንል እንቀበላለን

28/12/2024
ጥንቃቄ  ሼር በማድረግ ለሁሉም ያድርሱ #በሀዋሳ ከተማ የጀሶ እንጀራ ሻጮች ከተለያዩ ቦታ የመጡ ወጣቶች ስሆኑ እንጀራ ነው በማለት ሊጡን ከጀሶ ጋር በመደባለቅ  ለባለሱቆች 10 ብር እና 12...
27/12/2024

ጥንቃቄ

ሼር በማድረግ ለሁሉም ያድርሱ

#በሀዋሳ ከተማ

የጀሶ እንጀራ ሻጮች ከተለያዩ ቦታ የመጡ ወጣቶች ስሆኑ እንጀራ ነው በማለት ሊጡን ከጀሶ ጋር በመደባለቅ ለባለሱቆች 10 ብር እና 12 ብር ያስረክባሉ እሄን እርካሽ እንጀራ አገኘሁ ብሎ ሆድ አደር ባለሱቆችም የጀሶ እንጀራ መሆኑን እያወቁ ለራሳቸው ንፁ ጠፍ አስፈጭተው እየተጠቀሙ ለህብረተሰቡ የጀሶ እንጀራ ያቀርባሉ ።

በዚህ የጀሶ እንጀራ የተነሳ ብዙ የከተማው ነዋሪ በሽተኛ ሆኖ የበሽታው መንስኤ ሳይታወቅ በበሽታው እየማቀቁ ይገኛል።

ስለዚህም የምመለከተው አካል ተገብውን ክትትልና ፍተሻ በማድረግ እነዚህን ለህዝብ የማይጨነቁ ሆድ አደር የጀሶ እንጀራ አቅራብዮችንም ባለሱቆችንም ተጠያቂ እንድያደርግ ሼር በማድረግ ድምፃችንን እናሰማ

06/06/2024
 ። (ተጻፈ በ  Kalaa Gaam)  #ይነበብ  #ሼር=======================✒️ባለስልጣን ይሄዳል ባለስልጣን ይመጣል። በአመታት መሃከል አንድም እንኳን ለውጥ ማየት ተስኖት የሚ...
07/11/2023

። (ተጻፈ በ Kalaa Gaam) #ይነበብ #ሼር
=======================
✒️ባለስልጣን ይሄዳል ባለስልጣን ይመጣል። በአመታት መሃከል አንድም እንኳን ለውጥ ማየት ተስኖት የሚዳክረው #የሀዋሳና የአከባቢው ነዋሪ ማህበረሰብ አጅግ በጣም ያሳዝነኛል።

እንደምታውቀው ከተማዋ የቀድሞ ከንቲባ አስራ በአድስ ከንቲባ
እየተመራች ነው። በርግጥ አመራር በብልሹ አሰራር ወይም በክራይ ሰብሳብነትና በመሰል ወንጀል ብቻ አይደለም የሚጠየቀው። ነገሮችን የመከወን የአቅም ውስንነት እና የህዝብ ሃብት አለገባብ ብያባክንም ልጠየቅ ይችላል ።

እነሱ ይሻሩ፥ ይሾሙ ይታሰሩ ፥ይፈቱ ይጣሉ፥ ይታረቁ ፤ነገር ግን እኛ ህዝባችን ላይ የምደርሰውን በደል የመታገል ግደታ ይኖርብናል። ህዝብ በመረጠው ፓርቲ እና በፓርቲው አይድኦሎጂ ብሎም መርህ መገልገል አለበት ብየ አምናለሁ።

😢 ያ ካለመሆኑ ተነስቶ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ህዝባችንን የ''ልማት ተነሽ'' ብሎ አንዳንዱን አስነስቶ አንዳንዱን እንዳይሰራ እንዳይለወጥ የ ''X'' ምልክት አድርጎ ነገር ግን ለቤቱ ማስነሻ ካሳ ግምት አውጥቶ እንደነበር የሚታወቅ ብሆንም፣unfortunately ከአመታት በፊት የተገመተውንም የካሳ ገንዘብ ብሎም የምትክ ቦታ #የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለህብረተሰቡ ማስረከብ ወይም መስጠት አልቻለም።

''በዝሆኖች ጥል የሚጎዳው ሳሩ ነው'' እንደሚባለው እነሱ እዛ ስሾሙ፥ስሻሩ እየታሰሩ እየተፈቱ ህዝባችን ከስር ይንገላተታል።

✒️በነገራችን ላይ present value of money after a years (future value ) በሆነ fraction of number ተባዝቶ እንደምጨምር ይታወቃል ለማለት የፈለኩት በሰአቱ ግማሸ ሚልዮን የተገመተለት ሰው ዛሬ ላይ ያ ግማሽ ሚልዮን ምናልባት እንኳን ቤቱን ልሰራ ይቅርና የጣራ ወጪ ላይሸፍንለት ይችላል።

ከ 4 እና 5 አመት በላይ ህዝባችን የከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤቱን አገልግሎት ለማግኘት ተንከራቷል በየክልል ቢሮ ዞሯል።
እስካሁን ድረስ ማታለልና ማሸማቀቅ ለህዝባችን መልስ እየሆነ እያይን ነው:: ነገር ግን አሁን በቃችሁ ልንል እንፈልጋለን።

የዛሬ አያድርገውና የዛኔ ዘመን ህዝባችን ሆነ አብዛኛው ወጣት ከተማ አስተዳደሩ በሚያመቻቸው የስራ እድልና አገልግሎት ጠቃሚ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ከቅርብ ግዜ ወድህ ግን ህዝባችን ላይ እና የከተማው ወጣት ላይ strategic በሆነ መንገድ በደሎች እየተፈፀመ እያየን እየታገስን ቆይተናል፥ አሁን ግን መቆምና መብቃት አለበት ።

ዛሬ ነገ ሳይል ለዳቶ ለጨፈ ለቱሎ ለህጣታ እና ለአከባቢው ሰው የንብረት ማስነሻ የገንዘብ ካሳና የምትክ ቦታ ነገ ዛሬ ሳይል ይስጠን!! አሻጥሩና ህዝብን ማንገላታቱ ይብቃ!! ህዝቡ መረጠው በብልፅግና ፓርቲ መርህ መሰረት መገልገል አለበት፤የናንተን ኪስ ለማፈርጠም የድሃውን ህይወት አታጎሳቁሉ።

ለሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት ሀዋሳጉዳዩ :- ሁሉን አቀፍ መፍትሄ ስለመጠየቅ ይሆናልከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሀዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ ስር ካሉት ቀበሌያት አንዷ የሆነ...
02/09/2023

ለሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት
ሀዋሳ
ጉዳዩ :- ሁሉን አቀፍ መፍትሄ ስለመጠየቅ ይሆናል

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሀዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ ስር ካሉት ቀበሌያት አንዷ የሆነችው ዳቶ ኦዳሄ ቀበሌ በእናንተ ዘንድ የታወቀ መሆኑን እንገነዘባለን። ግዴታችንን እየተወጣን መብታችን ያልተከበረልን ህብረተሰብ ነን ብንል ማጋነን አይሆንም ። ግዴታችንን ተወጥን መብታችን እንድከበር ማፈናፈኛ አሳጥተን ስልጡን በሆነና በሰከነ አካሄድ የትግል ስልታችንን አጠናክረን ስንቀጥል ፣ እናንተ የሾማችኋቸው ስራ አስፈጻሚዎቻችን እንደ ውሃ ሽታ የሆነውን ተግባር የለሽ ንግግር አብዝተው ፣ ከንቱ ተስፋ አሰንቀው እንደወረዱ ለእናንተ ግልጽ ነው። እናንተ ተታለላችሁ፤ እነርሱ አታለሏችሁ። እኛ ከልማት ሳንሆን ቀረን።
ማሳያ:- ስራውን መሰራት ባለበት ጊዜ ሳይሰሩ ፣ የእናንተ ስብሰባ ሊካሄድ አንድ ሳምንት ሲቀር የፎቶ ትዕይንት ለማሳየት ፣ በፎቶ አስጀምረው በፎቶ አስጨርሰው ባቀረቡት ሪፖርት ያለ ልክ ተታለላችሁ፤ እነርሱም አታለሏችሁ። የወከላችሁን ህብረተሰብ መብት ማስከበር ስላልቻላችሁ እናንተም ተወቃሽ ናችሁ። እነርሱ በቀደዱት ቦይ ብቻ መፍሰስን መርጣችሁ እውነተኛውን የህዝብ ጩኸት አልሰማ ስላላችሁ። ደግመን እንላለን አዎን ተወቃሽ ናችሁ። ቢሆንም ግን አሁንም ያልተዘጋ የማስተካከል ዕድል አላችሁ።
ስለሆነም እኛ አሁን እናንተን የምንጠይቀው፣ የምናሳስበው:-
፩/ የባለፈውን ስህተት እንዳትደግሙ - ተግባር የለሽ ትወናን ፈጽሞ እንዳትሞክሩ
፪/ ቃል ተገብቶ ፣ የመሰረት ድንጋይ ተጥሎ ያሉ ፕሮጀክቶችን በሚገባ እንድታስፈጽሙ
፫/ ፍትሃዊ ያልሆነውን ፣ ለብዙ እንግልት የዳረገውን በሀዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ ስር ተዋቅሮ መቆየትን ገላግሉን።
፬ / Daato Keelli በሙሉ ኃይሉ ህጋዊ እውቅና ተሰጥቶት ወደ ስራ እንድገባ ይደረግ፣
የስራ ዕድል ፈጠራም ለዳቶ ስራአጥ ልጆች ይመቻች።

፭/ ብቃትን መሰረት ያላደረገ የቅብብሎሽ ሹሜት ያሳዝነናል ፤ አይፈይድምና።

፮/ ሀዋሳ የመሯት አመራሮቿ እስካሁን ሀዋሳን
የዳቶ፣ ጨፌ፣ ሂጣታ፣ ጥልቴ፣ ቱሎ--- ወዘተ ባለ ዕዳ አድርገዋት አልፈዋል። ሞልቶም ተርፏል። ዕዳቸውን ከመመለስም ያለፈ ዳጎስ ባለ ካሳ ልትሸልሟቸው ይገባል።

ይህ እንዲሆን ህዝቡን ወክላችሁ የተቀመጣችሁ ክቡራን የምክር ቤት አካላትና አባላት በሙሉ የአዳሬ ህብረተሰብ ችግርና ሰቆቃ እንድገዳችሁ ማሳሰብን ወደድን።
ማሳሰቢያውም:-
፩/ ሁሉን አቀፍ የሆነ ችግር ፈቺ መመሪያና ደንብ እንድዘጋጅ ወይም እንድጸድቅ የበኩላችሁን ብርቱ ጥረትና ትግል እንድታደርጉ፤ በማስፈጸምም እንድታሳርፉን እንፈልጋለን
፪/ ስብዕናው የበሰበሰ ፣ በሞራል የላሸቀ( Moral decay) አመራር ወደፊት አታውጡ፣ ብቃትን መሰረት ያላደረገ በደም ቆጠራ የሚላክ ፣ ህዝብን ሳይሆን ሊያገለግላቸው የሚሰዱትን በብርቱ ትግላችሁ እንድታርቁት።
የህዝብ ውግንና ያለውን ፣ የማይስገበገበውን ራሱን የገዛውን ሞዴል አመራር ብቻ እንድትመረጥ
፫/ ዳቶን ከልማት ገለል አድርጋችሁ ሌላ አስተዳደር እንዳላት እንዳትስመስሉ ብቻ ሳይሆን ልዩ ትኩረት ከሚሹ ቀበሌያት ውስጥ ቀዳሚዋ ናትና ልዩ ጉብኝታችሁ ካሁን በኋላ እንዳይለየን አደራ እንላለን።

ቀሪ ዘመናችሁ በተግባር የታጀበ ብቻ ይህንም
Daato News
27/12/2015
Daato

Ga'a Soodo guto guurate 11:30 Daato ollii giddo mitto ikkinohu baxxino bayichira   tullichi aana Chigginyete kaayishshi ...
25/07/2023

Ga'a Soodo guto guurate 11:30 Daato ollii giddo mitto ikkinohu baxxino bayichira tullichi aana Chigginyete kaayishshi amuurate Ayirradu Kalaa Abraham Marshaallohu massagaanchimmanni ikkitanno daafira baalunku yinoonni dargira leellino.
Keerunni.

የዓመቱ ማጠቃለያ ሪፖርት ዳቶ ኦዳሔ ቀበሌ ላይ ስላልተከናወኑት ፣  በ 16/09/2013 የመሰረት ድንጋይ በሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጸጋዬ ቱኬ (ረ/ፕሮ) ተጥሎ፣ የጉድጓድ ቁፋሮው ተጀምሮ፣ መደም...
18/07/2023

የዓመቱ ማጠቃለያ ሪፖርት ዳቶ ኦዳሔ ቀበሌ ላይ ስላልተከናወኑት ፣
በ 16/09/2013 የመሰረት ድንጋይ በሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጸጋዬ ቱኬ (ረ/ፕሮ) ተጥሎ፣ የጉድጓድ ቁፋሮው ተጀምሮ፣ መደምደሚያ ማግኘት የተሳነው ፕሮጀክት ያለበት ሁኔታ ታች ፎቶ ላይ ይመልከቱና ካብኔዎቹም ይወቁት። ሌላውም ይገንዘብ።
መረጃው ለሌላችሁ የሀይስኩል ት/ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ከተከናወነበት ሁለት ዓመት ሙሉና ሩብ አመት ሆኖታል። ሳብ ተስፋና በተግባር የታጀበ ክንውን ይሆናል " የማንጨርሰውን አንጀምርም፤ፍትሃዊ ተጠቃሚነታችሁ ከአሁን በኋላ ይረጋገጣል " ብሎ ብዙሃኑ ባለበት ተናግሮ የሄደውን ሳይፈጽም እነሆ ሁለት ዓመት በላይ ተቆጠረ።በተቆፈረው ጉድጓድ ውስጥም አረም በቀለበት። ይዘራበት የነበረው በቆሎም ቀረ። ለሌላ ክፉ ድርጊት መፈጸሚያነት ምቾት እንደሰጠ መረጃዎችም እየወጡ ነው።
ችግሩን በችግኝ በመቅረፍ ጊዜውንም ለመለካት ምስክር ይሆነን ዘንድ ችግር ተከልን።

ማጠቃለያውና የሪፖርቱ መደምደሚያ ፣ ተግባር የለሽ ና ተፈጻሚነቱ አዝጋሚ የሆነ ፕሮጀክት መሆኑን በሙሉ ድምጽ አጽድቀናል።
ታማኝነት የአንቺ መለኪያ መሆኑን አመራሮቻችን ከዘነጉ ዓመታት መቆጠሩን አላወቁም ለካ!?

አረንጓዴ አሻራችንን በሀዋሳ ሚልኒዬም ፓርክና በዳቶ ኦዳሄ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ህብረተሰቡን በማስተባበር ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።🌿☘️🌿☘️🌿ሀምሌ 10|2015ዓም   ዳቶ|ሀዋሳ
17/07/2023

አረንጓዴ አሻራችንን በሀዋሳ ሚልኒዬም ፓርክና በዳቶ ኦዳሄ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ህብረተሰቡን በማስተባበር ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
🌿☘️🌿☘️🌿
ሀምሌ 10|2015ዓም
ዳቶ|ሀዋሳ

አፈር ማዳበሪያ ዝርፊያ በሀዌላ ቱላ ❗በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ አስተዳደሪ የሀዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ በመንግስት ድጎማ የምመጣዉ የአፈር ማዳበሪያ ከመንግሰት መጋዝን በማዉጣት በአህያ ጋሪ የ...
25/06/2023

አፈር ማዳበሪያ ዝርፊያ በሀዌላ ቱላ ❗

በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ አስተዳደሪ የሀዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ በመንግስት ድጎማ የምመጣዉ የአፈር ማዳበሪያ ከመንግሰት መጋዝን በማዉጣት በአህያ ጋሪ የነጋዴዎች መጋዝን እያስገቡ የምያሳይ ምስል ከቱላ ደርሶናል

መንግስት ለገበሬዎች በድጎማ ብዙ ቢሊዮን በጀትን መድቦ የምያስገባዉ የአርሶ አደሩ የመኖር ዋስትናዉ ጋር የማያያዘዉ አፈር ማዳበሪያ በቀን በአደባባይ ለዛዉም በሀዋሳ ምድር እንደዚህ ስዘረፍ ማየት ምንዓይነት ጨካኝ ሰዎች እጅ እንደወደቅን የምያሳይ ነዉ።

ከመንግሰት መጋዝን ከ3,200 እያወጡ ነጋዴዎች ከ7,500 ብር በላይ እንደምሸጡ ምንጮቻችን ገልጿል።

ፍትህ ለሲዳማ አርሶ አደሮች!

ዘገባው
የዜና ሲዳማ ነው
ሰኔ 2015 ዓ

በሐዌላ ቱላ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የዳቶ ኦዳሄ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት የሶስተኛ ሩብ ዓመት የአባላት ኮንፍራንስ በዛሬዉ ዕለት አካህዷል።በዉይይቱም በበጀት ዓመቱ በሊጉ የተከናወኑ...
14/06/2023

በሐዌላ ቱላ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የዳቶ ኦዳሄ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት የሶስተኛ ሩብ ዓመት የአባላት ኮንፍራንስ በዛሬዉ ዕለት አካህዷል።

በዉይይቱም በበጀት ዓመቱ በሊጉ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም የቀጣይ ወራት ዕቅዶች ዙሪያም እንድሁም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዙሪያም በመወያየት በመግባባት ላይ በመድረስ ወደ ተግባር እንደምገባም የታመነበት መሆኑን ተገልጿል።

ዉይይቱም የሊጉን ተቋም ለማጠናርም ሆነ ጠንካራ ፓርቲን ለመፍጠር የታለመ ሲሆን በሁሉ ሕዋሳት ውስጥ ያሉ የወጣቶች ሊግ አባላት የተሳተፉበት ሲሆን አባላቱም የነቃ ተሣትፎ የሚያደርበትና ለቀጣይ ዕቅዶች ዙሪያም የጋራ መግባባት ላይ የሚደርሱበት መሆኑን ተገልጿል።

:ቱላ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት
ሰኔ-8-2015 ዓ.ም
ቱላ

 !!እንዲህ አይነት በደል በሰራተኛ ላይ የሚያደርሱ ግለሰቦች ልታረሙ ይገባቸዋል!!***************** #አቶ መለሠ ዲካሌ እባላለሁ ፤የሚኖረውም  በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ አስተዳደ...
09/06/2023

!!
እንዲህ አይነት በደል በሰራተኛ ላይ የሚያደርሱ ግለሰቦች ልታረሙ ይገባቸዋል!!
*****************
#አቶ መለሠ ዲካሌ እባላለሁ ፤የሚኖረውም በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፤ በሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ በተለምዶ ዳቶ ኦዳሄ ቀበሌ የሚባልበት ነው።የመንግስት ሠራተኛ ሲሆን በሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ አስተዳደር ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ሠራተኛ ነኝ።

እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሠርቼ የመለወጥ ፤ የማደግ ህልም ያለኝ ሰው ነኝ።ይህ ሆኖ እያለ እኔ በግሌ የደረሰብኝን በደል/አፈና ለህዝቡ ለማጋራት እፈልጋለሁ ።ይህም ማለት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ እኔ በሚሠራበት መ/ቤት አድስ መደብ/መዋቅር መተው ማለትም በክልል ደረጃ መንግሥት ሙስና ለመቀነስ ያግዘኛል በሚል እሳቤ የሥነ-ምግባር መደብ የሚባል በክልሉ በተወሰኑ እርከን ብቻ የነበሩትን እስከ ታችኛው እርከን ይበልጥ ለሙስና ተጋላጭ ይሆናሉ የሚባሉ ተቋማትን ትኩረት በማድረግ ሰው መመደብ ያስፈልጋል በማለት ጥናት ተጠንተው መዋቅሩ እንድወርድ ይደረጋል ።

ትንሽ ነገሩን ግልጽ ለማድረግ የሥነ-ምግባር መደብ እንደሌላ መደብ ውድድር ውስጥ ሳይገባ ይመደባል ።ይህም ማለት የጽ/ቤቱ ኃላፍ የማኔጅመንት አባላትን ሰብስበው ከሠራተኞች ውስጥ በሥነ-ምግባር የተሻለ ፣ ጠንካራ የሚሉትን መርጠው ይመድባሉ ።

ስለዚህም እኔንም በዚህ አኳህን መስፈርቱን ያሟላል ፤ እርሱ ይመደብ ብሎ መስኖ ተመደብኩኝ።የመደቡን ደብዳቤ ተቀብዬ ወደ ሥራ ገባሁኝ ። የጽ/ቤቱ ኃላፊው አንዳንድ ያልተገቡ ተግባራት መፈፀም ጀመረ ከሙስና ጋር ግንኙነት ያላቸውን ተግባራት መፈፀም ይጀምራል ፤ እኔም ተግባረ ስለሆነ ለሚን ማለት ጀመርኩና በዚህ ደስተኛ ያልሆነ የጽ/ቤቱ ኃላፊው አቶ ሻምበል ዱካሞ ቱለ ይባላል ቅም ይዘውብኝ መከታተል ጀመረኝ።

አንድ ቀን ሆድ አደሮቹን ሰብስበው በውሸት የለሌ ሥም ሰተውኝ አቶ መለሠ አድሱ የሲዳማ ፌደራልስት ፓርቲ አባል ሆነዋል ብሎ ታርጋ ለጠፈኝ።በጽ/ቤት ውስጥ ሌላ ሠራተኛ አጀራጅተው ወዘኛው ህገወጥ/አሸባሪ ፓርቲ ከብልጽግና እየወሰደብን ነው በማለት አሳሚኖ ዕገዳ ፃፈብኝ። እኔ ሚን አጠፋሁ ብዬ በሚጠይቅበት ጊዜ የማጣራው ጉዳይ አለ እያለ ቆየ።

እኔም አጣርተህ መልስልኝ ብየው ተውኩኝ።ከዛም ቦኃላ ከተወሰነ ቀናት በኃላ ከሰራተኞች ውስጥ ዘመድ የሚሆንለት ሰው መርጦ በሙስና ስለታወረ 5,000 ብር ጉቦ ተቀብሎ መደቡ ላይ ለእኔም ደብዳቤ የሰጠኝ አርሱ ለዛኛው ዘመዱ አቶ ሌጣ ቃቾ ኦቶዎ የሚባለውን መደቡ ላይ ደርበው ይመድባል።እኔም ይህን አደረገ የሚባል መረጃ ስደርሰኝ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚላቸውን ግለሰቦችና ተቋማት ቅሬታ አቀረብኩኝ እርሱም እኔን እየተከታተለ እልህ ውስጥ ገብተው ዘመድም ስላለው በገንዘብም ጭምር ሥልጣኑን እየተጠቀመ ተከታትለው መልስ እንዳይሰጠኝ እያስደረገ አስቸገረኝ ።

በክ/ከተማ እርስ በርስ በዘመድም ሆነ በሙስና የተጨማለቁ ስለሆኑ ተገቢ ዕልባት ልሰጡኝ አልቻሉም።በክ/ከተማ ተስፋ በመቁረጥ ቀጥታ ክልል ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚላቸውን ተቋማት ቅሬታ አስገባሁኝ። ክልሉም ባለሙያ ልኮ እንድያጣራ አስደረገ ። እስከ ቦታ ድረስ ሄዶ ባለሙያ ስያጣራ ትክክል ስላልሆነ በፍጥነት ወደ ቦታ ይመለስ ብሎ ይወስናል ።

የጽ/ቤቱ ኃላፊው አቶ ሻምበል ዱካሞ ቱለ እሺ ስህት ነው አስተካክላለሁኝ ብሎ ተቀብሎ እነሱን ከሸኜ በኃላ እያጭበረበረ የክልል አካላት ስልክ ይደውላሉ አስተካከልክ ? ይሉታል እርሱም አንድ ጊዜ ስብሰባ ሌላ ጊዜ ሥልጠና እያለ ጊዜ ይወስዳል።

በዚህ ብቻ ሳያበቃ ይባስ ብሎ አቶ ሌጣ ቃቾ ኦቶዎ የሚባል ግለሰብ በመደቡ ላይ ደርበው የመደበውን ዘመዱን በውጥ በትውውቅና በዝምድና በመጠቀም ደመወዝ እንድበላ ያደርጋል ። እኔም ይሄን መረጃ ስደረሰ ለክልል ነግሬያቸው በድጋም ደብዳቤ ይጽፋሉ ያኛውን ደመወዙን አግደ አስተካክል ይሉታል።

አሁንም ሳያስተካክል እርሱን ከማስተካክል ሥልጣኔን እለቃለሁ እያለ ይቆይና እንደምንም መ/ቤት እንድቀይሩት ያስደርጋል።ጽ/ቤቱ አድስ ኃላፍ ይመጣ አቶ ያዕቆብ ሆባሳ ለእርሱም ጉዳዩን እንደ አድስ ከመጀመሪያው ጀምሮ ተነገረለት እኔ ብቻ ሳልሆን የክልሉ ባለሙያ መጀመሪያ መተው ጉዳዩን ያጣሩ ይነግሩታል ።

አድሱ ኃላፍ ነገሩን ከመጀመሪያ ጀምሮ ከተረዱ ቦኃላ አስተካክላለሁ እያለ ይቆይና ቅድም እንደለጽኩ ነገሩ እርስ በርስ የተሳሰረ ነው መጨረሻ ላይ አምጥተው አቶ ሌጣ ደመወዝ ስለበላ ምንም ማድረግ አልችልም ይለኛል ደመወዝ መስቆም አልችም ብሎ ይመልስልኛል ። ክልሉ አቅም ያጣ ይመስልኛል።

በክልል ደረጃ ያለ ኃላፍ የጻፈውን ደብዳቤ ተቀብሎ አንድ የክ/ከተማ ለዝያውም የአንድ ጽ/ቤት ኃላፍ ምን ብተማመን ነው? አሁን የት ልህድ? የሲዳማ ህዝብ ጉዳዩ የሚመለከተው እንድያውቅልኝ ፤ ሥልጣን ህዝብን የሚታገለግልበት መሳሪያ እንጅ ሰው የሚታሰቃይበት አይደለም።ፍትህ እፈልጋለሁኝ ።

Address

At The Entrance Of City Of Hawassa From Addis
Hawassa
2154

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daato News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share