
29/04/2025
አሜሪካ ሰኞ ዕለት በየመን ሰአዳ በተሰኘው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ላይ በፈፀመችው የአየር ድብደባ የአፍሪካውያን ስደተኛ ሟቾች ቁጥር ከመቶ እያለፈ መሆኑ ተሰምቷል። በቁጥር የበዙት ቁስለኞች ደግሞ ህክምና ላይ ናቸው።
ከነዚህ ውስጥ 22 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በጥቃቱ መሞ ታ ቸውን እና ከ47 በላይ የሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ተረጋግጧል።
እስካሁን የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በተመለከተ ያለው ነገር የለም። ነፍስ ይማር እያልን መክረም ስራችን ሆኗል።