በወንጌል አላፍርም

  • Home
  • በወንጌል አላፍርም

በወንጌል አላፍርም የመጽሐፍ ቅዱስ እውነታዎችን በመግለጥ ሰዎች ከስህተት መንገድ እንዲወጡ ማስቻል ስራችን ነው ።

16/09/2025
29/12/2024

በሲዳማ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ71 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን ቦና ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ71 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ፣ አደጋው አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ሰርገኞችን ጭኖ ሲጓዝ በቦና ዙሪያ ወረዳ ጋላና ወንዝ ድልድዩን ስቶ ወደ ወንዝ በመግባቱ ነው የተከሰተው።

በዚህም እስካሁን የ71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸው ፥ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ ነው ብለዋል ።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ኮሚሽነሩ አመልክተዋል።

በመላኩ ገድፍ

Lowo qoropho assino! Albillite hawadi xeenni kaajje sufanno daafira huluullo noo qarqarira lowo qoropho assa hasiissano.
05/08/2024

Lowo qoropho assino! Albillite hawadi xeenni kaajje sufanno daafira huluullo noo qarqarira lowo qoropho assa hasiissano.

ሲዳሚኛ ቋንቋ የሚችል
28/07/2024

ሲዳሚኛ ቋንቋ የሚችል

26/01/2024
23/01/2024

ባለስልጣኑ ደኅንነታቸው ሳይረጋገጥ ገበያ ላይ የዋሉ ምርቶችን ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የገላጭ ጽሑፍና የኢትዮጵያን አስገዳጅ ደረጃ ሳያሟሉ እንዲሁም ደኅንነታቸውና ጥራታቸው ሳይረጋገጥ ገበያ ላይ የዋሉ 83 ምርቶችን ኽብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው አሳስቧል፡፡

44 ዓይነት የምግብ ዘይት ምርት እና 39 ዓይነት በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው ምርት ደኅንነታቸውና ጥራታቸው ያልተረጋገጡ መሆናቸውን ባለስልጣኑ በገበያ ቅኝት ሥራ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

በተጨማሪም የሀገሪቱን አስገዳጅ ደረጃ እና የገላጭ ጽሑፍ ደረጃ ሳያሟሉና ሳይለጥፉ መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ከታች በምስልና በስም የተጠቀሱት ምርቶች ደኅንነታቸውና ጥራታቸው ያልተረጋገጡና የሀገሪቱን አስገዳጅ ደረጃ የማያሟሉ በመሆናቸው ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡

በዚህም አስገዳጅ የሀገሪቱን ደረጃና የገላጭ ጽሁፍ ደረጃን ሳያሟሉ ገበያ ላይ የተገኙ የምግብ ዘይት ምርቶች፡-

ሰመር ንፁህ የምግብ ዘይት፣ ማሚ የተጣራንፁህ የምግብ ዘይት፣ እስካይ /Sky Sun flower oil፣ ሳኒ /SANI Edible Cooking Oil)፣አዚማር/Azimar Sunflower Oil፣ኑራ ንፁህ የምግብ ዘይት፣ አበባ ንፁህ የምግብ፣ ዘይት፣አደይ ንፁህ የምግብ ዘይት፣ዘቢብ/Zebib Sunflower oil፣አስሊ ንፁህ የምግብ ዘይት፣ ሪል (Real Pure Food Oil)፣ዙፋን ንፁህ የምግብ ዘይት፣ ሀኒ(Hani Sunflower Oil)፣ዲና ንፁህ የምግብ ዘይት

ሊና ንፁህ የምግብ ዘይት፣ማማ የተጣራ የምግብ ዘይት፣አል ኑር Al-Nur Sunflowor Oil፣ዋሪዳ Warida sunflower Oil፣ዜድ ንፁህ የምግብ ዘይት፣ደሴት ንፁህ የምግብ ዘይት፣ከፍታ ንፁህ የምግብ ዘይት Pure Food Oil፣ንግስት ንፁህ የምግብ ዘይት Nigist pure Food oil፣ሸገር Sheger pure Edible Oil፣አሪፍ Arif የኑግ የምግብ ዘይት ፣አመለ AMEL Edible Oil

ብሉ የኑግ ዘይት፣ንፁህ Nitsuh Food Oil፣ ኡማ ንፁህ የምግብ ዘይት ፣ማዕድ Maed ንፁህ የምግብ ዘይት፣ ሀያት የተጣራ የምግብ ዘይት ፣የምስራች ንፁህ የምግብ ዘይት፣ ህብረት ንፁህ የምግብ ዘይት፣ጎንደር የምግብ ዘይት Gonder Food Oil፣ ዜማ Zema pure Edible Oil ፣ፋና fana ፣ናና የኑግና የለውዝ የምግብ ዘይት፣ሪም ንፁህ የምግብ ዘይት

አንድነት ANDNET፣ሲያም ንፁህ የምግብ ዘይት፣ቤላ የምግብ ዘይት፣ሐሊማ የምግብ ዘይት፣ወሲላ ንፁህ የምግብ ዘይት Wesila፣ዝና ንጹህ የምግብ ዘይት፣ሰነዓ ንጹህ የምግብ ዘይት ናቸው፡፡

አስገዳጅ የሀገሪቱን ደረጃና የገላጭ ጽሁፍ ደረጃን ሳያሟሉ ገበያ ላይ የተገኙ የምግብ ጨው ደግሞ፡-

አርኪ የገበታ ጨው ARKY IODIZED SALT፣ኢኮ አዮዳይዝድ ጨው EKKO IODIZED SALT፣ስጦታ ጨው SITOTA Iodized Salt፣መስቱራ ባለ አዮዲን የተፈጨ ጨው MESTURA REFIND & IODIZED SALT፣ አስቤዛ የገበታ ጨው Asbeza Iodized salt፣ዘሀራ የገበታ ጨው ZAHARA IODIZED SALT፣መነስ ጨው MENES IODIZED SALT፣ግዩን አዮዲን ጨው Ghion Iodin Salt

አርዲ የገበታ ጨው ARDI IODIZED SALT፣ሳሊህ የገበታ ጨው SLIHA IODIZED SALT፣ናና ጨው NANA SALT፣ቤስት የገበታ ጨው Best Iodized Salt፣ቅመም የገበታ ጨው Iodized Salt፣ረሃ የገበታ ጨው REHA

ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች ይፋ ሆኑአዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚሰጡ የት...
21/01/2024

ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶችን ይፋ አድርጓል፡፡

በሚኒስቴሩ የሥርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ (ዶ/ር) እንዳሉት ÷ በተያዘው በጀት ዓመት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት መሠረት እየተተገበረ ነው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ በ2016 ዓ.ም በ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶችን መወሰን ማስፈለጉን አስረድተዋል፡፡

ይህን ተከትሎም በ2016 ዓ.ም ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሁለቱም ዘርፎች ስድስት ስድስት የትምህርት ዓይነቶች እንዲሰጡ መወሰኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጠዋል፡፡

በዚህ መሰረትም የተፈጥሮ ሣይንስ ተማሪዎች እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት እንዲወስዱ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ የማህበራዊ ሣይንስ ተማሪዎች እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት የሚፈተኑ ይሆናል ነው ያሉት፡፡

የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ የሚዘጋጅ መሆኑን ጠቁመው ÷ሌሎች የትምህርት ዓይነቶች ከ9 እስከ 11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ትምህርት ቢሮዎችም የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለመምህራን እና ለትምህርት ማህበረሰቡ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወዲሁ እንዲያሳውቁ አመላክተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

https://video-earn.yachts/5349271153820275/ sign up to get a 10 US Dollar newcomer bonus! I made more than 200 US Dollar...
01/01/2024

https://video-earn.yachts/5349271153820275/ sign up to get a 10 US Dollar newcomer bonus! I made more than 200 US Dollars by watching the video here, so you can try it.

No one knows yet, this is the easiest way to make money in 2023!

08/12/2023
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነአዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ገብተው በተለያዩ የሙያ ...
16/11/2023

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ገብተው በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠና የሚወስዱ ተማሪዎች የመግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል÷ ዜጎች ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚመጡት መሄጃ ስላጡ ሳይሆን ያላቸውን እምቅ አቅም አውጥተው መጠቀም እንዲችሉ ነው ብለዋል፡፡

ይህም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለዜጎች ዕድል ፈጣሪ አቅሞች እና ተጨማሪ አማራጭ የሚሰጡ ተቋማት ያደርጋቸዋል ነው ያሉት፡፡

ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ባለው አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ መሰረት ከዚህ ቀደም እስከ ደረጃ 5 ብቻ ተገድቦ የነበረው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የእድገት መሰላል እስከ ደረጃ 8 ድረስ እዲሆን መደረጉ ጠቁመዋል፡፡

ይህም ፖሊሲው ደረጃ ስድስትን ከመጀመሪያ ዲግሪ፣ ደረጃ ሰባትን ከማስተርስ እንዲሁም ደረጃ ስምንትን ከዶክትሬት ዲግሪ ትይዩ እንዲሆን አድርጓል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ስለሆነም በዚህ ዓመት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ መግባት ቢፈልጉ በደረጃ 6 ገብተው መሰልጠን እንደሚያስችላቸው አመላክተዋል፡፡

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በደረጃ 6 የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች እንደሚስተናገዱ ጠቁመው÷ በዚህ ዓመት በተቀመጠው መስፈርት መሰረት በክልሎች አማካኝነት የሰልጣኞች ምደባ ይካሄዳል ብለዋል፡፡

በዚህም በተያዘው የሥልጠና ዘመን 632 ሺህ በላይ ተማሪዎች የሥራ ገበያውን የሰው ሃይል ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5 እንደ ውጤታቸው ተመድበው እንደሚሰለጥኑም ጠቅሰዋል፡፡

በወጣው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ደረጃ አንድ እና ሁለት 110 ሺህ 15 ፣ በደረጃ ሦሰት እና አራት 412 ሺህ 557 እንዲሁም በደረጃ አምስት 110 ሺህ 15 ሰልጣኞች እንደሚሳተፉ አንስተዋል፡፡

በደረጃ ስድስት ደግሞ 2 ሺህ የሚሆኑ ሰልጣኞችን ለቀመበል ዝግጅት እንደተደረገ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የ2016 የስልጠና ዘመን የተዘጋጀው መቁረጫ ነጥብ የ2015 ትምህርት እና የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናልም ብለዋል፡፡

ከ2014 ዓ.ም በፊት ለነበሩ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ደግሞ በስልጠና ዘመኑ በነበረው መቁረጫ ነጥብ መሰረት እንደሚስተናገዱ ተጠቁሟል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ያዘጋጀው የመግቢያ ነጥብ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ቀርቧል፡-

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በወንጌል አላፍርም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share