
15/07/2025
ኑ ና ጎብኙልን 😮🙏
በማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል በሀዲያ ዞን ከሚገኙ ተፈጥሯዊ መስህቦች አንዱ የቦዮ ሐይቅ ሲሆን የሚገኘውም በሻሾጎ ወረዳ ነው፡፡
ሐይቁ 18 ቀበሌያትን የሚያዋስን ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ በ232 ኪ/ሜ ፣ ከሀዋሳ በ125 ኪ/ሜ፣ ከሆሳዕና ከተማ በ62 ኪ/ሜ እና ከቦኖሻ ከተማ በ4 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ቦዮ ሐይቅ ከወረዳው አጠቃላይ የቆዳ ስፋት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም በተደረገው የልኬት መረጃ መሰረት 2,392.1 ሄክታር እንደሚሸፍን ያሳያል፡፡
በሐይቁ ውስጥ ጉማሬ እና ሌሎች የተለያዩ የአዕዋፋት ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡ ከአዕዋፋቱም ውሰጥ አንዳንዶቾ ወቅቱን ጠብቀው ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡና የሚሄዱ ብርቅዬዎች እንደሆኑ ስለ ሐይቁ የተጻፉ መረጀዎች ያመላክታሉ፡፡
ሐይቁ ስፋትና ጥልቀት ስንመለከት በዞኑ ከሚገኙ ሐይቆች በስፋት ትልቁ ሐይቅ ነው፡፡ ሐይቁ የሻሾጎ ወረዳ 18 ቀበሌያትን የሚያዋስን ሲሆን በክረምት ወራትና በበጋ ወራት ተለዋዋጭ የሆነ ስፋት እንዳለው ይነገራል፡፡
በክረምት ወራት 6500 ሄ/ር በለይ መሬት ሽፋን ሲኖረው ጥልቀቱ ከ 4-8 ሜትር እንደሆነ ይገመታል፡፡
ከስልጤ፣ ከምባታና በዙሪያው ከሚገኙ ወረዳዎች የሚነሱ ትልልቅ ወንዞችን ጨምሮ የገጸ ምድር ውሃ ወደ ሐይቁ ስለሚገባ ውሃው ጨዋማነት የለውም ።
ከዚህ አኳያ ውሃው ቢታከም ለንጹህ መጠጥ ውሃነት መዋል የሚችል እንዲሁም ማራኪ ምቹና ሳቢ በመሆኑ መጥታችሁ እንድትጎበኙት ግብዣችን ነው፡፡
Via Hundoro Getahun Ertiro ከስፍራው
😮😮😮
🌴🌴🌴