28/03/2026
በነዳጅ እጥረት ምክንያት የመንግሥት ሠራተኞች የዓመት ዕረፍት እንዲወጡ ታዘዘ‼
በሀገሪቱ ያጋጠመውን የነዳጅ አቅርቦት እጥረትና የትራንስፖርት ጫና ለመቀነስ፣ መሠረታዊ ባልሆኑ የሥራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የመንግሥት ሠራተኞች የዓመት ዕረፍታቸውን እንዲጠቀሙ መመሪያ ተላለፈ።
📌 ውስን የሆነውን የነዳጅ ክምችት በአግባቡ ለመጠቀምና እንደ ቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላሉ ግዙፍ አገራዊ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ ለመስጠት ታስቦ የተወሰነ ነው።
📌 መመሪያው ሁሉንም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶችን የሚመለከት ሲሆን፣ እንደ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ያሉ ተቋማት ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል።
📌 በሥራ ገበታቸው ላይ የሚገኙ "ቁልፍ" ሠራተኞች የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን እንዲጠቀሙ ተነግሯቸዋል።
የቀጠናው ፖለቲካዊ ውጥረት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ ለዚህ ውሳኔ መነሻ መሆኑ ተገልጿል።
Wasu Mohammed - Mereja