
26/08/2025
በሀድያ ዞን ምሻ ወረዳ ሲኮ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ 4 ሰዎች ህይወት አለፈ
በሀድያ ዞን ምሻ ወረዳ ሲኮ ቀበሌ በደረሰ ከባድ ትራፊክ አደጋ የ 4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሌሎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
።።።።።።ሆሳዕና፣ ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም።።።።።።
በሀድያ ዞን ከሆሳዕና ወደ ሶዳ ኦሞጮራ ሲጓዝ ሰው ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ምሻ ወረዳ ሲኮ ቀበሌ ኤገዳ በሚባል ቦታ ላይ ከቀኑ 5:30 አካባቢ የመገልበጥ አደጋ ደርሶበታል ።
በተከሰተው የተሽከርካሪ አደጋ የ 3 ሰዎች ህይወት አደጋው በደረሰበት ቦታ ሲያልፍ 1 ሰው ደግሞ በሞርሲጦ ጤና ጣቢያ በህክምና እየተረዳ እያለ ህይወቱ አልፏል ።
ሌሎች በተሽከርካሪው ውስጥ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መካከል ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው በሞርሲጦ ጤና ጣቢያ ህክም እየተደረገላቸው ሲሆን ከባድ ጉዳት የደረባቸው ሰዎች ለህክምና ወደ ሆሳዕና ንግስት ኢሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስደዋል ።
የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ የምሻ ወረዳ ፕሊስ ጽ/ቤት የትራፊክ ቡድን አስተባባሪ ገልጸዋል ሲል የወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ዘግቧል ።
የሟቾችን ነፍስ እግዚአብሔር ይማርልን 😭😭😭