Hadiya zone Government Communication

  • Home
  • Hadiya zone Government Communication

Hadiya zone Government Communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hadiya zone Government Communication, .

This is the offical facebook home page of Hadiya Zone Communication

‹ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተደራሽ የሆነ የመንግሥት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ሥርዓት በመገንባት መንግሥትንና ሕዝብን ተጠቃሚ በማድረግ አንድ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማኀበረሰብን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን "ከመስፈንጠር ከፍታ፤ ወደ ላቀ እምርታ"-በሚል መሪ ሀሳብ የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማና የአመራር ማጠቃለያ ምዘና መድረክ በመካሄድ ላይ ነው።ሆሳዕና...
25/07/2025

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን "ከመስፈንጠር ከፍታ፤ ወደ ላቀ እምርታ"-በሚል መሪ ሀሳብ የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማና የአመራር ማጠቃለያ ምዘና መድረክ በመካሄድ ላይ ነው።

ሆሳዕና፡ ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም በሀዲያ ዞን "ከመስፈንጠር ከፍታ፤ ወደ ላቀ እምርታ" - በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማና የአመራር ማጠቃለያ ምዘና መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

አመራሩ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በመጠበቅ የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማና የአመራር ማጠቃለያ ምዘና መድረክ በመካሄድ ላይ ሲሆን፤

በመድረኩም የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ፣ የሀዲያ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤ፣ የዞኑ አስተባባሪዎች፣ የዞኑ አመራር ፑል አባላት፣ የየመዋቅሩ አስተባባሪዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
በሰለሞን ወልዴ

ለ2018 የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ 8... ቀን ብቻ ቀረው!
24/07/2025

ለ2018 የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ 8... ቀን ብቻ ቀረው!

24/07/2025

አረንጓዴ አሻራ
በመትከል ማንሰራራት

ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 162 ቢሊዮን ብር ገቢ  ማግኘቱን አስታወቀሆሳዕና፤ ሐምሌ 17/2017 ፦ ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት 162 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግ...
24/07/2025

ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 162 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

ሆሳዕና፤ ሐምሌ 17/2017 ፦ ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት 162 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል።

ገቢው የተገኘው ከድምጽ ጥሪ፣ ከኢንተርኔት አገልግሎት፣ ከቫስ፣ ከመሠረተ ልማት ማጋራት፣ ከቴሌኮም ቁሳቁስ ሽያጭና ከሌሎች ምንጮች መሆኑንም ገልጿል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፥ የኩባንያውን የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምና መሪ የሶስት ዓመት የእድገት ስትራቴጂ ማጠቃለያ ሪፖርት ለመገናኛ ብዙኃን ይፋ አድርገዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ከሶስት ዓመት በፊት የቴሌኮም እና የዲጂታል አገልግሎትን ማሳደግ የሚያስችል መሪ የሶስት ዓመት የእድገት ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱን አስታውሰዋል።

ኩባንያው ከቴሌኮም አገልግሎት ባሻገር በዲጂታላይዜሽን በኩል አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን አመላክተዋል።

የቴሌኮም አገልግሎት አሰጣጡን ከማስፋትና ጥራቱን ከማሳደግ አኳያ ከፍተኛ እድገት መመዝገቡንም ነው ዋና ስራ አስፈጻሚዋ የገለጹት።

ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረትም ትርጉም ያለው ስራ መሠራቱን አንስተዋል።

በመሪ የሶስት ዓመት የእድገት ስትራቴጂ ደግሞ 26 ከተሞችን በ5ጂ ኔት ወርክ እንዲሁም 936 ከተሞችን በ4ጂ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

በዚህም በመላ ሀገሪቱ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን የፈጣን ኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ምህዳር መፈጠሩን ተናግረዋል።

በ2017 በጀት ዓመት 1ሺህ 683 አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች መገንባታቸውንም ነው የጠቀሱት።

በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ10ሺህ በላይ የሞባይል ጣቢያዎች ተተክለው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙም አመላክተዋል።

በበጀት ዓመቱ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፥ 162 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል።



#ኢዜአ

የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችና የዳኞችን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቀቀ ሆሳዕና፤ሐምሌ 17/2017 ፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆች እና የ...
24/07/2025

የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችና የዳኞችን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቀቀ

ሆሳዕና፤ሐምሌ 17/2017 ፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆች እና የዳኞችን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቀቀ።

ምክር ቤቱ ካፀደቃቸው አዋጆች መካከል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የቀበሌ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ስልጣን እና ተግባርን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ይገኝበታል።

የአዋጁን ረቂቅ ያቀረቡት በምክር ቤቱ የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ መሰረት ወልደሰን፥ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶቹ በእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ለሚነሱ አለመግባባቶች አፋጣኝ እልባት ለመስጠት ያስችላሉ ብለዋል።

እንዲሁም ፍትህ ለማግኘት በሚደረግ ሂደት ይባክን የነበረን የ‎ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ ለመቆጠብ እንደሚያስችሉም አንስተዋል።

በፍትሀብሔር እና ቀላል የወንጀል ጉዳዮች ሙግት ውስጥ የገቡ ወገኖችን በማግባባት ብሎም ጉዳያቸውን በእርቅ በመጨረስ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የላቀ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

ሌላው በምክር ቤቱ የጸደቀው የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የሠራተኞች መተዳደሪያ ደንብ ሲሆን የክልሉ ምክር ቤት የፋይናንስና በጀት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ታመነ ገብሬ፤ ደንቡ የኦዲት ግኝትን ለማጠናከርና ገቢን በአግባቡ ለመሰብሰብ እንደሚያስችል ለምክር ቤቱ አባላት አብራርተዋል።

በክልሉ በተለያዩ ደረጃዎች የሚያገለግሉ የ37 ዕጩ ዳኞች ሹመትም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ በኩል የቀረበ ሲሆን ዳኞቹ ያላቸው የትምህርት ዝግጅት፣ የሥራ ልምድ፣ ስነምግባርና ሌሎች ጉዳዮች ከግምት ውስጥ ገብተው ለሹመት መታጨታቸው ተገልጿል።

ምክር ቤቱም በቀረቡ ረቂቅ አዋጆችና በዳኞች ሹመት ላይ የተለያዩ ሀሳብና አስተያየቶችን ከሰጠ በኋላ ተቀብሎ አጽድቋል።

በዚህም ለከፍተኛ ፍርድ ቤት 11 እንዲሁም ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ፍርድ ቤቶች 26 ዳኞች ሹመት ጸድቋል።

ተሿሚ ዳኞችም በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለመሀላ ፈጽመዋል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት ላለፉት ሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ አዋጆችና ሹመቶችን ካጸደቀ በኋላ ማምሻውን ተጠናቋል።

#ኢዜአ

24/07/2025

ከ371ሺ በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል ...

#የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

24/07/2025

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተረጂነትን አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ

"በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጲያ ከፍታ" - በሚል መሪ ሀሳብ በሀዲያ ዞን ምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ ኢልፈታ ቀበሌ ዞናዊ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት  ተጀመረ  ።።።።።።።ሐምሌ 17፣2017።።...
24/07/2025

"በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጲያ ከፍታ" - በሚል መሪ ሀሳብ በሀዲያ ዞን ምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ ኢልፈታ ቀበሌ ዞናዊ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ

።።።።።።።ሐምሌ 17፣2017።።።።ሆሳዕና

በዞኑ በ2017 ክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ536 ሺህ 4 መቶ 13 በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጭ ወጣቶች በማሳተፍ 974 ሺህ 69 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የልማት ሥራችን በመስራት ከመንግስት ሊወጣ የሚችለውን ከ310 ሚሊየን 682 ሺህ 7 መቶ 31 ብር ወጭ ለማስቀረት ታቅደው ወደ ሥራ የተገበ ሲሆን

በዛሬው ዕለትም ዞናዊ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በሀዲያ ምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ ተካሂዷል።

በወረዳውም መጠለያ ቤት ለሌላቸው አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት ግንባታ፣ማዕድ መጋራት፣ችግኝ ተከላና የደም ልገሳ መርሐ ግብር ተከናውኗል።

ከዚህ በተጓዳኝ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውና የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ግንባታ ተጎብኝቷል።

በመርሐ ግብሩም የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤን ጨምረው የዞን/የወረዳ አስተባባሪዎች፣የአካባቢው ነዋሪዎች፣የወጣት አደረጃጀቶችና አመራሮች ተሳትፈዋል።

በምህረተአብ ዘለቀ

24/07/2025

በ 2018 ዓ.ም ክልሉ ሙሉ በሙሉ ከተረጂነት ለመላቀቅ እየሰራ እንደሚኝኘ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) አስታወቁ

ሆሳዕና፣ሐምሌ 17/2017

#ደሬቴድ

24/07/2025

በቀጣይ 3 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የክልሉ ዜጎች የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻው ጣሰው ገለፁ

ሆሳዕና፣ሐምሌ 17/207

#ደሬቴድ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የቀረበለትን ደንብና አዋጅ መርምሮ አጸደቀ ሆሳዕና: ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 4ኛ ዓመ...
24/07/2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የቀረበለትን ደንብና አዋጅ መርምሮ አጸደቀ

ሆሳዕና: ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤው የቀረቡለት ልዩ ልዪ ደንቦች እና አዋጆች መርምሮ አጸደቀ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የሠራተኞች መተዳደሪያ ደንብ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የቀበሌ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ በዝርዝር መርምሮ አፅድቋል።

በምክር ቤቱ የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ መሠረት ወልደሠንበት፥ የረቂቅ ደንቡንና አዋጁን አስፈላጊት ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

በክልሉ በሚገኙ የከተማና የገጠር ቀበሌ አስተዳደር ዉስጥ የሚኖረዉ ሕዝብ ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዉ የሚከሰቱትን ቀላል ጉዳዮች በመኖሪያ ቀበሌዉ እንዲያገኝ ለማስቻል መሆኑን አመላክተው፥ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ-መንግሥት የተቋቋሙ በመሆናቸዉ፤ ሕብረተሰቡ በዕለታዊ እንቅስቃሴዎች ምክንያት የሚነሱ አለመግባባቶች አፋጣኝ እልባት እንዲያገኝ ለማድረግ ካላስፈላጊ ውጣ ውረድና ወጪ የሚያድን መሆኑን ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ለምክር ቤቱ የቀረበው ደንብ፥ የክልሉን ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የሙያ ነፃነት በማረጋገጥ የተቋሙን አሠራርና አደረጃጀት ይበልጥ በማሻሻልና በማጠናከር ተግባሩን እንዲወጣ ለማስቻል የሚያግዝ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የሠራተኞች መተዳደሪያ ደንብ ማውጣት ተገቢነት ያለው መሆኑን አስረድተዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የቀረበውን አንድ ረቂቅ ደንብ እና ሁለት አዋጆችን መርምሮ በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ አፅድቋል።

በተያያዘ ዜና ምክር ቤቱ የቀረቡለት እጩ ዳኞች ሹመት መርምሮ አፅድቋል። ምክር ቤቱ ለከፍተኛ ፍርድ ቤቶች 11 እንዲሁም ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር ፍርድቤቶች ደግሞ 26 በድምሩ የ37 እጩ ጃኞችን ሹመት አጽድቋል።

ላለፉት ሁለት ቀናት ሲካሔድ የነበረው የነበረው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ተጠናቋል።

#ደሬቴድ

ሆስፒታሉ የአገልግሎት አሰጣጡን የተሻለና ቀልጣፋ ለማድረግ ባከናወነው  የሪፎርም ተግባራት ለውጥና መሻሻል መኖሩን ተገልጋይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናገሩበዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ህክምና ጤና ሳይንስ ...
24/07/2025

ሆስፒታሉ የአገልግሎት አሰጣጡን የተሻለና ቀልጣፋ ለማድረግ ባከናወነው የሪፎርም ተግባራት ለውጥና መሻሻል መኖሩን ተገልጋይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናገሩ

በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የንግስት እሌኒ መሃመድ መታሰቢያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ለማድረግ ባከናወነው ሪፎርም ተግባራት ለውጥና መሻሻል መኖሩን ተገልጋይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናግሩ።

ሆስፒታሉ የ 2017 በጀት ዓመት የአገልግሎት አሰጣጡ ባተኮረ የ 4 ሩብ ዓመት አፈፃፀም ከተገልጋዩ ማህበረሰብ ጋር የውይይት መድረክ ያካሄደ ሲሆን፤

በቀጣይ በሚሰጠው አገልግሎት ህብረተሰቡን በይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ከወረቀት ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጅታል ስርዓትን ለመተግበር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም የሆስፒታሉ አስተዳደር ጠቁሟል።

።።።።።ሆሳዕና፣ ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም።።።።።።

ሆስፒታሉ የወሊድ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የእናቶች ማረፊያ መሠራቱና ተያያዥ ተግባራት ተጨባጭ ለውጥ መኖሩ፣ የደም ባንክ ተደራሽነት ላይ እና የፋርማሲ አገልግሎትን ከማስፋፋት አኳያ፣ የማህበረሰብ ፋርማሲና ላይቦራቶሪ አገልግሎትን ቀልጣፋ በማድረግ ተደራሽነት ለማስፋት እንዲሁም የኦክስጅን እጥረት ችግር ለመቅረፍ በተደረገው ጥረት ተጨባጭ ለውጥ መታየቱን ጠቁመዋል።

እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ ሆፒታሎችን ለመደገፍ በተደረገው ጥረትና በሌሎችም የአገልግሎት መስኮች ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በተደረገው እንቅስቃሴ ለውጥ መኖሩ የተገለፀ ሲሆን ከዚሁ ተያይዞም ተቋሙ የአስክሬን ምርመራ አገልግሎት መጀመሩ በሪፖርቱ ቀርቧል።

ከተገልጋዩ ማህበረሰብ ክፍሎች በሆስፒታሉ እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶችን ይበልጥ ተደራሽና ውጤታማ ማድረግ እንዲቻል ለታካሚዎች የሚታዘዙ መድኀኒቶች አቅርቦት የተሟላ መሆን፣ በካርድ ክፍል የሚስተዋል መጨናነቅና የአገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ አለመሆኑ፣ የፅዳት አጠባበቅን አንስተው እነኝህና ሌሎች ክፍተቶች በቀጣይ እንዲቀረፉ የሚመለከተው ክፍል ጥብቅ ክትትል ሊያደር እንደሚገባ በማንሳት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ኤርሚያስ ሞሊቶ ዩኒቨርስቲው በሆስፒታሉ የፅዳት ተግባራትን በሚጠበቀው ልክ ማከናወን የገጠመውን የውሃ አቅርቦት እጥረት ችግርን ለመቅረፍ ጥናት በማድረግ ችግሩን ሥራ ይሠራል ብለዋል።

የዲጅታል ስርዓትን በመተግበር ከወረቀት ንክኪ ነፃ የሆነ የማህበረሰብ አገልግሎት ለመስጠት፣ የተገልጋይ ርካታ ከፍ ለማድረግና እንዲሁም የሚያጋጥመውን የሀብት ብክነት መቀነስ እንዲቻል ትኩረት ተሰጥቶ እደሚሰራና ዩኒቨርስቲውም ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

በሆስፒታሉ የገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ አልፎ አልፎ በጥቂት አካላት የሚስተዋሉ የስነ ምግባር ጉድለቶችን ለማረም የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ክትትል የሚደረግ ሲሆን ችግሩ የተስተዋለባቸው አካላትም ከአላስፈላጊ ድርጊታቸው ሊታረሙ በማሳሰብ ጉዳዩ በጥብቅ ዲስፕሊን ሊመራ እንደሚገባ ዶክተር ኤርሚያስ አሳስበው በህክም አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ማህበረሰቡ እንዳይጉላላና ጉዳይቸገር ሁሉም አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

በንግስት እሌኒ መሃመድ መታሰቢያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር ይድነቃቸው ደዳቸው በበኩላቸው ከተገልጋዩ ማህበረሰብ የተነሱ አስተያየቶችና ቅሬታዎች ለተቋሙ ግብዓትና ጥንካሬ በመሆን ክፍተቶችን በመለየት ለማረም የሚያስችሉ ናቸው በማለት፤

በተለይም በካርድ ክፍል አካባቢ ያለውን የሰልፍ ጫና፣ (altr-sound) በአልተራ-ሳውንድና (x-ray) ኤክስ ሬይ ቀጠሮና በሌሎችም የሚስተዋሉ ችግሮች ለመቅራፍ በትኩረት እንሠራለን ብለዋል።

አያይዘውም በገቢ አሰባሰብና ቁጥጥር ላይ አላስፈላጊ የሀብት ብክነትን ለመቀነስ ከወረቀት ነፃ አገልግሎት ለማህበረሰቡ ለመስጠት ዲጂታላዜሽን ሥራዓት በመዘርጋት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ዶክተር ይድነቃቸው አስረድተዋል።

በሆስፒታሉን ከውሃ አቅርቦት እጥረት ጋር ተያይዞ የሚነሱ የንጽህና እና የኦክስጅን እጥረት ችግር ለመቅረፍ በቀጣይ እንደሚሠራ አንስተው ማህበረሰቡ የፋርማሲ አገልግሎት በቅርበት እንዲያገኝ ለማስቻል ስራው አስጀምረናል ብለዋል።

የዞኑ ጤና መምሪያ ተወካይ የሆኑት አቶ ሚሻሞ ወርቅነህ በበኩላቸው በሆስፒታሉ አካባቢ ተገልጋዮችን በአግባቡ ለማስተናገድ፣ የተገልጋዮች ፍሰት ጫናን ለመቀነስ፣ ማህበረሰቡ የህክምና አገልግሎት በቅርበት እንዲያገኝ ለማስቻል በዞኑ በታችኛው መዋቅር የሚገኙ አራቱንም ሆስፒታሎች የማብቃትና አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል የማድረግ ስራ በቅንጅት እየተሠራ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።

በውይይቱም የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ኤርሚያስ ሞሊቶ፣ ንግስት እሌኒ መሃመድ መታሰቢያ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዶክተር ይድነቃቸው ደዳቸው፣ የሀዲያ ዞን አስተዳደር ተወካይ ፣ የሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ ተወካይ አቶ ሚሻሞ ወርቅነህ፣ የሆስፒታሉ ማኔጅመንት አካላትና ሲነር ሀኪሞችና ባለሙያዎች፣ የህክምና ባለሙያዎች፣ አመራሮችና ሌሎችም አካላት ተገኝተዋል።

በደገለ ባምቦሬ

Address


Telephone

+251465551908

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hadiya zone Government Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hadiya zone Government Communication:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share